03
Jan
ላለፉት ሶስት ዓመት የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረው የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ከአማራ ክልል አስተዳድር ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረመ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የንቅናቄው አመራሮች በተለያዩ የአመራር ቦታዎች ላይ ሹመት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል፡፡ የአገው ዴሞክራሲ ንቅናቄ (አዴን) የጥቅምት 2013ቱን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተከትሎ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በተለይም በአበርገሌና ፃግብጂ ወረዳዎች ትጥቅ ትግል ሲያካሄድ ቆይቷል፡፡ ታጣቂ ኃይሉ በሁለቱ ወረዳዎች ቆላማ አካባቢዎች እስከ 19 የሚሆኑ ቀበሌዎችን ሲቆጣጠር እንደነበረም ንቅናቄውና የመንግስት አካላት አመልክተዋል፡፡ የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ የመንግሰትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ ታህሳስ 13 ቀን 2016 ዓ ም በአዲስ አበባ ከተማ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ማድረጉንና ትናንት ደግሞ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ማዕከል ሰቆጣ ከተማ…