29
Dec
ያሜንት ኢቬንትስ ጥንዶችን ለመሞሸር የያዘውን ፕሮጀከት አላማ ለማሳወቅ እና ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በቀጣይ አብሮ በትብብር ለመስራት የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ ያሜንት ኢቭንትስ በዚህ ጊዜ እንዳለው "ቤተሰብን መመስረት ሀገርን መገንባት ነው" በሚል መርህ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም አንድ ሺህ ጥንድ ተጋቢዎችን በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ጋብቻ እንዲመሰርቱ የሰርግ ሁነት አዘጋጅቷል። በባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና በያሜንት ኢቬንትስ መካከል ዛሬ የተፈረመው የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ የየሺህ ጋብቻ እንደ ሀገር አቀፍ የቤተሰብ ፕሮጀክት እንዲዘልቅ በማድረግ ከቤተሰብ አመሰራረት ጋር የሚገጥሙ ችግሮችን ለማቃለል አላማው ያደረገ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ የጋራ ጋብቻ ሁነት አመታዊ ካርኒቫል የህዝብ ለህዝብ ትስስርንና መተማመንን ከማጠናከር ባሻገር ኢትዮጵያ የምትታወቅበትን ጎብኚዎችን እንዲስብ ለማድረግ መታሰቡም…