መነሻ ገፅ

የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተከፈተ

የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተከፈተ

ከ30 ሀገራት በላይ የተውጣጡ ከ250 በላይ የፋሽን፣ ጨርቃጨርቅ እና ቆዳ ኢንዱስትሪዎችዎቸን በአንድ ጣራ ስር የሚያሰባስበው የአፍሪካ ሶርሲንግና ፋሽን ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ፡፡ በአፍሪካ አህጉር ትልቁ የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን የሆነው "10ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግ እና ፋሽን ሳምንት(10th AFRICA SOURCING AND FASHION WEEK  ASFW ) በአዲስ አበባ  ስካይ ላይት ሆቴል ከዛሬ ጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም ይካሄዳል። የፋሽን ሳምንቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስት አቶ መላኩ አለበል፣ ክብርት ሌንሳ መኮንን፣ በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ እና ሌሎች በርካታ አንግዶች ከፍተውታል፡፡ ዝግጅቱ አለም አቀፍ ብራንዶችን፣ የኢንዱስትሪ መሪዎችን እና ፈጣሪዎችን በአንድ ጣሪያ ስር በማሰብሰብ እስካሁን  ከተደረጉት ዝግጅቶች ሁሉ ትልቁ  ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የአፍሪካ ሶርሲንግና…
Read More
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለዶናልድ ትራምፕ እነኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለዶናልድ ትራምፕ እነኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እየመሩ ገኛሉ፡፡ ትራምፕ እስካሁን በተረጋገጡ የወኪል መራጮች ምርጫ አማካኝነት 267 በ224 ድምጽ እየመሩ ይገኛሉ፡፡ አስቀድሞ 270 የወኪል መራጮችን ድምጽ ያገኘ እጩ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ይሆናል በሚለው ህግ መሰረት ዶናልድ ትራምፕ በይፋ ማሸነፋቸውን ለማወጅ ሶስት ድምጽ ብቻ መቅረቱን ተከትሎ በርካታ የዓለማችን ሀገራት አስቀድመው እንኳን ደስ አለዎት መልዕክታቸውን እያስተላለፉ ናቸው፡፡ ከነዚህ መካከልም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) አንዱ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ስላሸነፉ እንኳን ደስ አለዎት፣ ወደ መሪነት እንኳን ድጋሚ መጡ አብረን እንደምንሰራ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል፡፡ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው ለዶናልድ ትራምፕ እና ባለቤታቸው እንኳን ወደ…
Read More
የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ባንኮች ወደ የኢትዮጵያ ለመግባት እያሰቡ ነው ተባለ

የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ባንኮች ወደ የኢትዮጵያ ለመግባት እያሰቡ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ እስካሁን በሯን ለውጭ ባንኮች ዝግ አድርጋ የቆየች ሲሆን አሁን ላይ የፖሊሲ ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ የውጭ ሀገራት ባንኮች እንዲገቡ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በፊት መግለጹ ይታወሳል፡፡ ለዚህም ሲባል የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከአንድ ዓመት በፊት የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫውን በደቡብ አፍሪካ ያደረገው ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ ለመግባት ከስድስት ወራት በፊት አመልክቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የሞሮኮ፣ የኬንያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ባንኮች በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ማሞ ምህረቱ ተናግረዋ፡፡ ዋና ገዢው አክለውም የውጭ ሀገራት ባንኮች በኢትዮጵያ እንዲሰሩ የሚፈቅደው ህግ በቀጣዮቹ ሳምንታት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚጸድቅ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንክ ፍቃድ ለማግኘት የሚፈልጉ…
Read More
አሜሪካ በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት አሳስቦኛል አለች

አሜሪካ በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት አሳስቦኛል አለች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ጋር በስልክ መወያየታቸው ተገልጿል። “በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶች እልባት እንዲያገኙ የፖለቲካ ውይይት ወሳኝነት አለው” ሲሉ አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር አብይ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ወቅት መናገራቸው የመስሪያ ቤታቸው መግለጫ አመላክቷል። አሜሪካ “በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት ያሳስባታል” ሲሉ መናገራቸውን በመግለጫው ላይ ተገልጿል። አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በስልክ ያወሩት በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ዙሪያ እንደነበር ጸ/ቤታቸው ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። አንቶኒ ብሊንከን “ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲደረግ ለምታደርገው ጥረት ሀገራቸው እገዛ ለማድረግ ዝግጁ ናት” ሲሉ መናገራቸውን መግለጫው ጠቁሟል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር…
Read More
በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን የመንግስት ባለስልጣንን ጨምሮ ከ60 በላይ ሰዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን የመንግስት ባለስልጣንን ጨምሮ ከ60 በላይ ሰዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች ውስጥ በመንግስት የጸጽታ ሀይሎች እና የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መካከል ከባድ ውጊያ በመካሄድ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል ውጊያ ከሚካሄድባቸው ወረዳዎች መካከል አንዱ በሆነው ደራ ወረዳ በትናንትናው ዕለት  ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ባለስልጣንን ጨምሮ ንጹሃን ዜጎች ተገድለዋል፡፡ ከተገደሉት መካከል የወጫሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩን አንዱ ሲሆኑ ከአስተዳዳሪው በተጨማሪም የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ንጹሃን ዜጎችም ገኙበታል ተብሏል፡፡ የአመራሩ ግድያ የተፈጸመው አመራሩና በርካታ የጸጥታ ሃይሎች መንግስት ኦነግ ሸኔ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ሃይል ወደሚንቀሳቀስበት አካባቢ ሲያመሩ ነው ተብሏል። በደራ ወረዳ ገንዶ መስቀል አካባቢ ላለፉት ሶስት ሳምንታት የመከላከያ ሰራዊትን፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን (ወይም መንግስት ኦነግ ሸኔ የሚለውን) እና የፋኖ…
Read More
ኢትዮጵያ ሞቶ የተገኘ አስከሬንን ለምርምር መጠቀም እንዲቻል የሚፈቅድ ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ ሞቶ የተገኘ አስከሬንን ለምርምር መጠቀም እንዲቻል የሚፈቅድ ህግ አዘጋጀች

ከሁለት ሳምንት በፊት የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ይህ ረቂቅ ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የአስከሬን አያያዝ እና ዝውውር ጉዳይ አንዱ ሲሆን በርካታ ጉዳዮችን ደንግጓል፡፡ ከነዚህ መካከልም በህግ ሥልጣን ከተሰጠው አካል ካልፈቀደ በስተቀር የሰው አካል ክፍልን፣ አስክሬንን ወይም አጽምን ወደ ሐገር ውስጥ ማስገባት ወይም ከሐገር ማስወጣትን ይከለክላል፡፡ እንዲሁም አስከሬንን ለማስተማሪያነት ወይም ለምርምር ማዘጋጀት የሚችለው አግባብነት ባለው አካል የተመረጠ የጤና ተቋም ነው እንደሆነም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተጠቅሷል፡፡ ማንኛውም አስክሬንን ለማስተማሪያነት ወይም ለምርምር እንዲያዘጋጅ የተመረጠ ተቋም ያዘጋጀውን አስክሬን ከሌላ የማስተማሪያ እና የምርምር ተቋም ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሰረት አስክሬንን ለማስተማሪያነት እና ለምርምር ተግባር እንዲውልም ይፈቅዳል፡፡ አስከሬንን…
Read More
ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ዳታ ማይኒንግ ኩባያዎች 27 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

ኢትዮጵያ ከውጭ ሀገራት ዳታ ማይኒንግ ኩባያዎች 27 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አገኘች

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ለጎረቤት አገራት ከሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ከ31 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቱን አስታወቀ። ተቋሙ ለጅቡቲ ከሸጠው ከ169 ሺሕ 710 ሜጋ ዋት በላይ የሚኾን ኃይል፣ 10 ሚሊዮን 379 ዶላር እና ለኬንያ ከሸጠው ከ314 ሺሕ 931 ሜጋ ዋት በላይ የሚኾን ኃይል ከ20 ሚሊዮን 470 ሺሕ ዶላር ማግኘቱ ተገልጿል። በተመሳሳይ፣ ተቋሙ ለሱዳን ካቀረበው ከ13 ሺሕ 185 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ከ659 ሺሕ በላይ ዶላር ያገኘ ሲኾን፣ በሱዳኑ ጦርነት ሳቢያ ተቋሙ በሩብ ዓመቱ ለአገሪቱ ለማቅረብ ካቀደው ኃይል ውስጥ ያቀረበው 15 በመቶውን ብቻ እንደኾነ ተገልጧል። ኢትዮጵያ ውስጥ በዲጂታል መረጃ ማቀነባበር ከተሠማሩ የውጭ ኩባንያዎች በሩብ ዓመቱ ውስጥ ከተሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ደግሞ፣…
Read More
እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ያሉ ተማሪዎችን በውጤታቸው ደረጃ መስጠትን ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

እስከ 6ኛ ክፍል ድረስ ያሉ ተማሪዎችን በውጤታቸው ደረጃ መስጠትን ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

በሳሙኤል አባተ ኢትዮጵያ የአጠቃላይ ትምህርት አዋጅን ለማሻሻል ያለመ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅታለች፡፡ ይህ ረቂ አዋጅ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ በትናንትናው ዕለት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም ይህን ረቂቅ አዋጅ ተጨማሪ ውይይቶች እና ሌሎች ግብዓቶች እንዲታከሉበት በሚል ለዝርዝር እይታ ወደ ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡ ይህ ረቂቅ አዋጅ እንደሚለው ከሆነ ተማሪዎች ስለ ሚማሯቸው ቋንቋዎች፣ ስርዓት ትምህርት ዝግጅት፣ መምህራን ቅጥር፣ ተማሪዎች ምዘና፣ ትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ መንገዶች እና ሌሎችንም ጉዳዮች ይዟል፡፡ ቋንቋዎችን አስመልክቶ በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተቀመጠው የአፍ መፍቻ ቋንቋ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የሚሰጥ ሆኖ እንደ ትምህርት አይነትነት እና እንደ ማስተማሪያ ቋንቋነት መሰጠቱ የሚያበቃበትን የክፍል ደረጃ ክልሎች ይወስናሉ ብሏል፡፡…
Read More
የአቦል አዳዲስ ይዘቶች ማስተዋወቂያ እና የአፋፍ ቴሌኖቬላ ማጠናቀቂያ ልዩ ዝግጅት ተካሄደ

የአቦል አዳዲስ ይዘቶች ማስተዋወቂያ እና የአፋፍ ቴሌኖቬላ ማጠናቀቂያ ልዩ ዝግጅት ተካሄደ

ሕንድ ለ20 የፊልም ሙያተኞች የስኮላርሽፕ እድል ሰጥታለች “የአቦል አዳዲስ ይዘቶች ማስተዋወቂያና የአፋፍ ቴሌኖቬላ ማጠናቀቂያ” ልዩ በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት አዳራሽ (ወመዘክር) ተካሂዷል፡፡ በዚህ መድረክ ላይ ታዋቂ የፊልም ባለሙያዎች፣ ተወናዮች፣ የመንግስት ተቋማት ሃለፊዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልመህዲ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር "ዲኤስቲቪ በኢትዮጵያ የፊልም ጥበብ እንዲጎለብት በፋይናንስና በስርጭት እያደረገ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው። በርካቶች የፊልም ጥበብ ባለሙያዎች ይህንን በመጠቀም እየተንቀሳቀሱ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ለዚህ ማሳያ የሆነው " አፋፍ ተከታታይ ድራማ በፕሮዳክሽን ጥራትም በይዘትም ምሳሌ በሚሆን መልኩ ተዘጋጅቶ ሲቀርብ ነበር" ብለዋል። በስኬት በመጠናቀቁም የይዘት ባለቤቱን ዲኤስቲቪ አቦል ቴሌቪዥንና አዘጋጁን ሚካኤል…
Read More
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሹመት ተቃውሞ ገጠመው

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሹመት ተቃውሞ ገጠመው

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ጉባኤ የአምስት ሚንስትሮችን ሹመት ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ውሳኔ አሳልፏል። ለምክር ቤቱ ከቀረቡ አጀንዳዎች መካከል የአምስት ሚንስትሮች ሹመት አንዱ ሲሆን የምክር ቤት አባላት እና የመንግስት ተጠሪ ክርክር አድርገዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከሁለት ሳምንታት በፊት የሾሟቸው አምስት ሚንስትሮች በዛሬው የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ የቀረበ ሲሆን የምክር ቤት አባላት በሹመቱ ዙሪያ ጥያቄ አንስተዋል። ከተነሱ ጥያቄዎች መካከልም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ተደርገው የተሾሙት እና ስራ የጀመሩት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) አንዱ ነበር። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ወክለው የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ጥያቄ ካነሱት መካከል አንዱ ነበሩ። ሹመቱን አስመልክቶ ካነሱት ጥያቄ መካከልም "የፍትህ…
Read More