24
Jun
በአንድ ዓመት ውስጥ ደግሞ ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰላም ጥናት ማዕከል አስታውቋል የኢትዮጵያ ፒስ ኢብዘርቫቶሪ የተሰኘው ተቋም ባወጣው ሪፖርት መሰረት በአንድ ሳምንት ውስጥ 100 ኢትዮጵያዊያን ተገድለዋል ብሏል። ከሰኔ 3 ቀን እስከ 9 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በተፈጠሩ የፖለቲካ ግጭቶች ምክንያት 100 ሰዎች መገደላቸውን የግጭት ሁኔታ መረጃዎችን የሚያቀርበው “ኢትዮጵያ ፒስ ኦብዘርቫቶሪ” አስታውቋል። ዓለም አቀፍ የግጭት ሁኔታ እና የክስተት የመረጃ በመሰብሰብና በመተንተን የሚታወቀው “The Armed Conflict Location & Event Data Project” የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ይህንኑ ሥራ በኢትዮጵያ እንዲሠራ በፕሮጀክት ደረጃ ያቋቋመው፣ “Ethiopia Peace Observatory” የተባለው ተቋም ባወጣው ሳምታዊ ሪፖርት፤ በሳምንቱ ከተገደሉት 100…