04
Jul
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ላይ ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጉዳይ ዋነኛው ነው። በቱርክ አደራዳሪነት በአንካራ የተጀመረው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ድርድር ሁለተኛው ዙር የፊታችን ነሀሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ይቀጥላል የተባለ ሲሆን ይህ ድርድር ምን ያህል ከውጭ ጣልቃ ገብነት የተጠበቀ ነው? የሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ተከታዩን ብለዋል። "ኢትዮጵያ በታሪኳ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ስትደራደር ቆይታለች፣ አንድም ጊዜ በውጭ ጣልቃ ገብነቶች ጥቅሟን አሳልፋ ሰጥታ አታውቅም" ብለዋል። "በአንካራ እየተካሄደ ያለው የሁለትዮሽ ድርድርም ብሔራዊ ጥቅማችንን ባስጠበቀ መንገድ ይቀጥላል" ያሉት አምባሳደር ነብዩ በድርድሩ ላይ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደሌለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ…