Cameroon

ኢትዮጵያ በመላው አፍሪካ አትሌቲክስ ውድድር አራተኛ ሆና አጠናቀቀች

ኢትዮጵያ በመላው አፍሪካ አትሌቲክስ ውድድር አራተኛ ሆና አጠናቀቀች

በካሜሩን አስተናጋጅነት የተካሄደው የመላው አፍሪካ አትሌቲክስ ውድድር ተጠናቋል፡፡ በካሜሩን ዋና ከተማ ዱዋላ አስተናጋጅነት ከ27 ሃገራት በላይ የተውጣጡ 2500 አትሌቶች ላለፉበት 6 ቀናት ሲሳተፉበት የነበረው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቋል። በዚህ ውድድር ለይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አራተኛ ሆኖ አጠናቋል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5 ወርቅ፣ 4 የብር እና አንድ የነሐስ በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን አግኝቷል፡፡ ኢትዮጵያጵያ በውድድሩ ላይ 68 አትሌቶችን በ19 የአትሌቲክስ የውድድር አይነቶች ላይ የተሳተፈች ሲሆን ከናይጀሪያ በመቀጠል አራተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡ የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች ፋንታዬ በላይነህ በ5ሺ ሜትር ሴቶች ፣ንብረት መላክ በ10ሺ ሜትር ወንዶች ፣ምስጋና ዋቁማ በወንዶች በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ፣    ስንታየሁ ማስሬ በሴቶች በ20 ኪሎ ሜትር…
Read More