New admin

1169 Posts
ሳፋሪኮም ኬንያ የደንበኞችን መረጃ ለመንግስት አሳልፎ እንዳልሰጠ ገለጸ

ሳፋሪኮም ኬንያ የደንበኞችን መረጃ ለመንግስት አሳልፎ እንዳልሰጠ ገለጸ

ዋና መቀመጫውን ናይሮቢ ያደረገው ሳፋሪኮም ኬንያ የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት እንዳልሰጠ አስታውቋል፡፡ ድርጅቱ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የአገሪቱን የመረጃ ጥበቃ ህግ መሰረት በማድረግ የደንበኞቹን ነፃነት እንደሚያከብር አስታውቋል፡፡ ተቋሙ እንዳለው በፍርድ ቤት አማካኝነት ካልታዘዘ በስተቀር ማንኛውንም የደንበኞቹን መረጃ ለሌላ ሶስተኛ አካል አሳልፎ እንደማይሰጥ ገልጿል፡፡ ድርጅቱ እስካሁን የደንበኞቹን መረጃ እንዲሰጥ ከመንግስት ጥያቄ እንዳልቀረበለት አስታውቋል፡፡ እንዲሁም የደንበኞቹን መረጃ ለመንግስት አካል አሳልፎ እንዲሰጥ የሚጠይቅ የፍርድ ቤት ትእዛዝ እንዳልደረሰውም በመግለጫው ላይ ጠቅሷል፡፡ የድርጅቱ እህት ኩባንያ የሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ አጋርነት ለኢትዮጵያ በሚል ሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ላይ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ህጋዊ ፍቃድ ከተቀበለ ከአንድ ዓመት በኋላ ስራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ከሶስት ዓመት በፊት ወደ…
Read More
በሃጅ ጉዞ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ1300 አለፈ

በሃጅ ጉዞ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ1300 አለፈ

በዘንድሮ የሃጅ ጉዞ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ1300 ተሻግሯል የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አምስቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ሳዑዲ አረቢያ ገልጻለች፡፡ በዘንድሮ የሃጅ ጉዞ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ1ሺህ 300 መሻገሩን ሳዑዲ አረቢያ አስታውቃለች። እስካሁን በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የ10 ሀገራት ዜጎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ 658ቱ ግብጻውያን ናቸው ተብሏል። 150 ሺህ ሃጃጆችን የላከችው ፓኪስታን 58 ዜጎቿ ህይወታቸው ማለፉን ይፋ አድርጋለች። ከ240 ሺህ ኢንዶኔዥያውያን ሃጃጆች መካከልም 183ቱ መሞታቸውን የሀገሪቱ የሃይማኖቶች ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። የሱዳን፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ህንድ፣ ዮርዳኖስ፣ ማሌዥያና ኢራን ዜግነት ያላቸው ሃጃጆችም ህይወታቸው ማለፉን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ከዚህ ውስጥ አምስቱ ኢትዮጵያዊን እንደሆኑ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ገልጿል፡፡ አብዛኛዎቹ ሟቾች ያለፈቃድ…
Read More
በኢትዮጵያ አራት ክልሎች ምርጫ መካሄድ ጀመረ

በኢትዮጵያ አራት ክልሎች ምርጫ መካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ቀሪ ምርጫ በሚደረግባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም ድጋሚ ምርጫ በሚደረግባቸው በጅግጅጋ 2 እና መስቃንና ማረቆ ምርጫ ክልሎች በዛሬው ዕለት ምርጫ እየተካሄደ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በ6ኛው ዙር ሀገራዊ ቀሪና ድጋሚ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል። ዛሬ እየተካሄደ ባለው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይም 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ መሆኑን ከምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ቀሪና ድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች እየተካሄደ መሆኑንም ነው ቦርዱ ያስታወቀው። ቀሪና ድጋሚ ምርጫ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች አንዱ በአፋር ክልል የሲሆን፤ በክልሉ 4 ዞኖች፣ በ9 የምርጫ ክልሎች እና በ388 የምርጫ…
Read More
በአማራ ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋረጠ

በአማራ ክልል የተወሰኑ ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋረጠ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የፋኖ ሀይሎች በተቆጣጠሯቸውና ወጣ ገባ በሚሉባቸው ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ አደራጃለሁ የሚል ውሳኔ ከወሰነበት ጀምሮ በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ አንድ ዓመት አልፎታል፡፡ በዚህ ጦርነት ምክንያት በክልሉ ለ10 ወራት የዘለቀ የአስቸኳይ አዋጅ የታወጀ ሲሆን ካሳለፍነው ሳምንት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀመሮም የአዋጁ ጊዜ ቢያበቃም ክልሉ በኮማንድ ፖስት እየተዳደረ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የተወሰኑ ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ የባንክ አገልግሎት ከተቋረጠባቸው ወረዳዎች መካከል መንዝ ላሎ፣ ግሼ ራቤል፣ አንፆኪያ ገምዛ እና ቀወት ወረዳዎች እንደሚገኙበት ዋዜማ ሬዲዮ…
Read More
ለወሎ ተርሸሪ ሆስፒታል ግንባታ በሚል የተሰራጨው የ17 ሚሊዮን ብር ኩፖን መጥፋቱ ተገለጸ

ለወሎ ተርሸሪ ሆስፒታል ግንባታ በሚል የተሰራጨው የ17 ሚሊዮን ብር ኩፖን መጥፋቱ ተገለጸ

የፌደራል ዋና ኦዲተር የ2015 በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት ተቋማትን የበጀት ኦዲት ዋና ዋና ግኝቶችን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። ዋና ኦዲተር በሪፖርቱ ላይ እንዳለው ከህዝብ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ኦዲት ካደረጋቸው ስራዎች መካከል የወሎ ተርሸሪ የህክምና እና የማስተማሪያ ሆስፒታል ግንባታ ዋነኛው ነው፡፡ በተሰራው የኦዲት ሪፖረት መሰረትም ለሆስፒታሉ ግንባታ በሚል የገቢ ማሰባሰቢያ በሀገር ውስጥ እና ውጭ ሀገራት ሲደረግ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ለዚህም ሲባል በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች እና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች፣ ክልሎች እና ሌሎች አካባቢዎች ይሸጣል ተብሎ 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ኩፖን ተሰራጭቶ እንደነበር በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል፡፡ ይሁንና ይህ 9 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር የሚያወጣው የገቢ መሰብሰቢያ ኩፖን እንደጠፋ ተገልጿል፡፡ ከዚህ…
Read More
በአማራ ክልል ጅጋ ከተማ 18 ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተገደሉ

በአማራ ክልል ጅጋ ከተማ 18 ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተገደሉ

የጸጥታ ሀይሎቹ የአዕምሮ ህመምተኛን ጨምሮ በመዝናናት ላይ የነበሩ የባንክ ሰራተኞችን እና መምህራንን ገድለዋል በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ጅጋ ከተማ፤ ቢያንስ 18 ሰዎች “በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መገደላቸውን” ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ብሔራዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፤ “በአካባቢው ጥቃት ተፈጽሟል” የሚል መረጃ እንደደረሰው ገልጾ ፤ ክስተቱን እያጣራ መሆኑን አስታውቋል። የዓይን እማኞቹ፤ የጅጋ ከተማ ነዋሪዎች የተገደሉበት ክስተት የተፈጸመው ባሳለፍነው እሁድ ሰኔ 9፤ 2016 አመሻሽ ላይ መሆኑን ገልጸዋል። በዚሁ ዕለት ምሽት 11 ሰዓት ገደማ፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን የጫኑ “ሶስት ፓትሮል” ተሽከርካሪዎች ከደንበጫ ወደ ጅጋ ከተማ እየገቡ በነበረበት ወቅት፤ “በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት” ከፊት በነበረው መኪና ላይ ጥቃት ካደረሱ በኋላ መሸሻቸውን የዓይን እማኞቹ አብራርተዋል። ጥቃት…
Read More
ኢትዮጵያ በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚወክሏትን አትሌቶች መረጠች

ኢትዮጵያ በፓሪስ ኦሎምፒክ የሚወክሏትን አትሌቶች መረጠች

በየአራት ዓመቱ አንዴ የሚካሄደው የመላው ስፖርታዊ ውድድር ወይም ኦሊምፒክ የዘንድሮው ውድድር በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ይካሄዳል። ውድድሩ ከሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያ በውድድሩ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል ናት። በአትሌቲክስ ዘርፍ ኢትዮጵያን በውድድሩ ላይ የሚወክሉ አትሌቶች ምርጫ በስፔን ኔርሀ ትናንት ምሽት ተደርጓል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በ10 ሺህ ሜትር ሁለቱም ጾታ፣ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች እንዲሁም በ800 ሜትር ወንዶች የማጣሪያ ውድድሮች ተካሂደዋል። ኢትዮጵያ ለፓሪስ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ውድድር ለመሳተፍ የማጣሪያውን ውድድርን በትንሹ በ27 ደቂቃ ማጠናቀቅን እንደ መስፈርት አስቀምጣለች። በዚህም መሰረት በማጣሪያው ውድድር ከተሳተፉ 16 አትሌቶች ተሳትፈው ዮሚፍ ቀጄልቻ በ26፡31.01 1ኛ በሪሁ አረጋዊ 26፡31.13 2ኛ ፣ሰለሞን…
Read More
ስድስተኛው የፍቅር እና ሰላም ኪነ ጥበብ ውድድር ተካሄደ

ስድስተኛው የፍቅር እና ሰላም ኪነ ጥበብ ውድድር ተካሄደ

በዓለም አቀፉ የሴቶች ሰላም ቡድን አዘጋጅነት የተካሄደው ይህ የፍቅር እና ሰላም ኪነ ጥበብ ውድድር በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ዋናው ግቢ ውስጥ ተካሂዷል፡፡ በዚህ ውድድር ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የስዕል፣ ግጥም እና ሌሎች የስነ ጽሁፍ ይዘቶችን ለተመልካቾች አቅርበዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሰላም ሁኔታ እና ተስፋዎች ላይ ያተኮረው ይህ የኪነ ጥበብ ውድድር ህጻናት እና ታዳጊዎች የኪነ ትበብ ስራዎቻቸውን ለተመልካቾች አቅርበዋል፡፡ በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ስርዓተ ጾታ ሃላፊ ሰውዓለም ጸጋ (ዶ/ር) እንዳሉት ኢትዮጵያ ሰላም ከራቃት ዓመታትን እንዳስቆጠረች ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ላጋጠማት የሰላም ችግር ዋነኛ መንስኤው የሴቶች በግጭት አፈታት ዙሪያ ያላቸው ተሳትፎ አናሳ በመሆኑ ነው ያሉት ሰውዓለም ጸጋ…
Read More
ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ለ12 የኢትዮጵያ ጀማሪ ተቋማት 720 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረገ

ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ለ12 የኢትዮጵያ ጀማሪ ተቋማት 720 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረገ

ለስምንት ሳምንታት ያህል ማመልከቻዎችን ሲቀበል ከቆየ በኋላ፣ ሪች ፎር ቼንጅ ኢትዮጵያ (Reach for Change Ethiopia) በዛሬው ዕለት የማስተርካርድን ኤድቴክ ፕሮግራም የመጀመሪያውን ዙር የተቀላቀሉትን 12 የኤድቴክ ሥራ ፈጣሪዎች ይፋ አድርጓል። “ኤድቴክ” (EdTech) በእንግሊዝኛው ትምህርት እና ቴክኖሎጂን አጣምሮ የያዘ ቃል ሲሆን፣ ትምህርትን አሳታፊ በሆነና ምቹ መንገድ ለማቅረብ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምን የሚገልጽ ሐሳብ ነው። ፕሮግራሙ የሪች ፎር ቼንጅ እና የማስተርካርድ ፋውንዴሽን አጋርነት አንድ አካል ሲሆን፣ የአጋርነቱ ዓላማም ለተመረጡ የኤድቴክ ድርጅቶች ቁልፍ የሆነ የቢዝነስና የፋይናንስ ድጋፍ መስጠት ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ ፕሮግራሙ ለድርጅቶቹ አዲስን ነገር ስለ መማር ሳይንስ፣ ስለ እድገትና መስፋፋት፣ ስለ ዘላቂነት እንዲሁም ተጽዕኖ ስለ መፍጠር ምልከታን የሚያስጨብጥ ይሆናል። “እነዚህ ፕሮግራሙን የተቀላቀሉ 12 የኤድቴክ…
Read More
ሳፋሪኮም እና ገበያ ኩባንያ የኢትዮጵያን የሥራ ፈጠራ ሥነ ምህዳር የሚያሳድግ “ታለንት ክላውድ” ጀመሩ

ሳፋሪኮም እና ገበያ ኩባንያ የኢትዮጵያን የሥራ ፈጠራ ሥነ ምህዳር የሚያሳድግ “ታለንት ክላውድ” ጀመሩ

ሳፋሪኮም ከገበያ ኩባንያ ጋር በአጋርነት፣ እንዲሁም የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) ድጋፍ ታክሎበት “ሳፋሪኮም ታለንት ክላውድ” የተሰኘ ፕሮግራም ይፋ አድርገዋል። ፕሮግራሙ የመረጃ መረብን በመጠቀም የሥራ ዕድልን የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል። ፕሮግራሙ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነና ቀጣዩን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሁም የዲጅታሉ ዓለም መሪዎችን አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው። ይህ የተለየ አሠራርን ይዞ የመጣው ፕላትፎርም እስከ 2024 እ.ኤ.አ ማብቂያ ድረስ፣ ለ10 ሺሕ ልዩ ልዩ ክህሎት ያላቸው ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች አጠቃላይ የአቅም ግንባታ እንዲሁም የሥራ ጉዟቸውን ማሳደጊያ ዕድሎችን የሚያቀርብ ነው። ይህንን በማድረግ፣ በአገሪቱ ውስጥ የሚስተዋለውን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂውን ኢንዱስትሪ ዕድገት የገታውን የቴክኖሎጂ ክህሎት እጥረት ለመቅረፍ ፕሮግራሙ ዒላማ ያደርጋል። "የሳፋሪኮም ታለንት ክላውድ “ለመጪው ዲጂታል ዘመን የኢትዮጵያንን…
Read More