14
Jun
ለስምንት ሳምንታት ያህል ማመልከቻዎችን ሲቀበል ከቆየ በኋላ፣ ሪች ፎር ቼንጅ ኢትዮጵያ (Reach for Change Ethiopia) በዛሬው ዕለት የማስተርካርድን ኤድቴክ ፕሮግራም የመጀመሪያውን ዙር የተቀላቀሉትን 12 የኤድቴክ ሥራ ፈጣሪዎች ይፋ አድርጓል። “ኤድቴክ” (EdTech) በእንግሊዝኛው ትምህርት እና ቴክኖሎጂን አጣምሮ የያዘ ቃል ሲሆን፣ ትምህርትን አሳታፊ በሆነና ምቹ መንገድ ለማቅረብ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀምን የሚገልጽ ሐሳብ ነው። ፕሮግራሙ የሪች ፎር ቼንጅ እና የማስተርካርድ ፋውንዴሽን አጋርነት አንድ አካል ሲሆን፣ የአጋርነቱ ዓላማም ለተመረጡ የኤድቴክ ድርጅቶች ቁልፍ የሆነ የቢዝነስና የፋይናንስ ድጋፍ መስጠት ነው። ከዚህ በተጨማሪ፣ ፕሮግራሙ ለድርጅቶቹ አዲስን ነገር ስለ መማር ሳይንስ፣ ስለ እድገትና መስፋፋት፣ ስለ ዘላቂነት እንዲሁም ተጽዕኖ ስለ መፍጠር ምልከታን የሚያስጨብጥ ይሆናል። “እነዚህ ፕሮግራሙን የተቀላቀሉ 12 የኤድቴክ…