17
Jun
በየአራት ዓመቱ አንዴ የሚካሄደው የመላው ስፖርታዊ ውድድር ወይም ኦሊምፒክ የዘንድሮው ውድድር በፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ ይካሄዳል። ውድድሩ ከሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያ በውድድሩ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል ናት። በአትሌቲክስ ዘርፍ ኢትዮጵያን በውድድሩ ላይ የሚወክሉ አትሌቶች ምርጫ በስፔን ኔርሀ ትናንት ምሽት ተደርጓል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በ10 ሺህ ሜትር ሁለቱም ጾታ፣ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወንዶች እንዲሁም በ800 ሜትር ወንዶች የማጣሪያ ውድድሮች ተካሂደዋል። ኢትዮጵያ ለፓሪስ ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ውድድር ለመሳተፍ የማጣሪያውን ውድድርን በትንሹ በ27 ደቂቃ ማጠናቀቅን እንደ መስፈርት አስቀምጣለች። በዚህም መሰረት በማጣሪያው ውድድር ከተሳተፉ 16 አትሌቶች ተሳትፈው ዮሚፍ ቀጄልቻ በ26፡31.01 1ኛ በሪሁ አረጋዊ 26፡31.13 2ኛ ፣ሰለሞን…