28
Apr
በኢትዮጵያ የካንሰር ታማሚዎች ወደ ጤና ተቋማት የሚሄዱት የህመሙ ደረጃ ሶስት እና አራት ከደረሰ በኋላ መሆኑ ተገልጿ። ይህንን ለማዳን ከባድ እንዲሆን የሚያደርግ መሆኑም በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር ዴኤታ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ ሌሊሳ አማኑኤል ተናግረዋል። የካንሰር ህመም ቀድሞ ማከም እና መከታተል ከተቻለ መዳን የሚቻል ህመም መሆኑን አማካሪው ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የካንሰር ህመም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዛ መምጣቱን እና በዓመት ከ83 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በካንሰር በሽታ እንደሚያዙም አክለዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓመት 19 ሚሊዮን ሰዎች በካንሰር የሚያዙ ሲሆን 10 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ተነግሯል። ከእነዚህም መካካል 75 በመቶ የሚሆነው ዝቅተኛ የሆነ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ሀገራት ላይ የሚከሰት መሆኑ ተገልጿል ። በሌላ በኩል የህጻናት የካንሰር…