EthioNegari

ከ3 ሺህ በላይ የውጭ ዜጎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸው ተገለጸ

ከ3 ሺህ በላይ የውጭ ዜጎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸው ተገለጸ

የኢምግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት እንደገለጸው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ወደ አገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ ከ3 ሺህ 400 በላይ የውጭ አገር ዜጎች መያዛቸውን ጠቁሟል፡፡ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የሶት ወራት ሪፖርት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ ዳይሬክተሯ በዚህ ጊዜ እንዳሉት ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ከ3 ሺህ 400 በላይ የውጭ አገር ዜጎች ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ የነበሩት የውጭ ዜጎች ቪዛ ሳያገኙ ለመግባት ሲሞክሩ፣ ህገወጥ የጉዞ ሰነድ ይዞ መገኘት እና መሰል ህገወጥ ድርጊቶችን ለመፈጸም ሲሞክሩ እንደነበር ተገልጿል፡፡ እንዲሁም ከ1 ሺህ 500 በላይ ዜጎች ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ተይዘዋል የተባለ ሲሆን ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በሀገር ውስጥ ቆይተው…
Read More
ብሔራዊ ባንክ የባንክ አካውንት ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳሰበ

ብሔራዊ ባንክ የባንክ አካውንት ከብሔራዊ መታወቂያ ጋር እንዲያስተሳስሩ አሳሰበ

ባንኮች የከፈቷቸውን አካውንቶች በሁለት ሳምንት ውስጥ ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰር ሥራ እንዲያጠናቅቁ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ እና የብሔራዊ መታወቂያ በጋራ ባወጡት አዲስ የአተገባበር ሥርዓት መሰረት የፋይናንስ ተቋማት ብሄራዊ ኦፕሬተር በሆነው ኢት-ስዊች በኩል ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰር ሥራ መስራት መጀመራቸው ተገልጿል። እስካሁን 10 የሚሆኑ የፋይናንስ ተቋማት ከብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ጋር የማስተሳሰሩን ሥራ ጨርሰዋል ሲባል ሌሎች ባንኮች በሙከራ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይለበስ አዲስ ለኢትዮ ነጋሪ እንደገለጹት ይህ አሰራር ባንኮች አገልግሎታቸው ቀልጣፋ እንዲሆንና ማዕከላዊ የመረጃ አያያዝ እንዲኖር ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል። አክለውም ትስስሩ ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር ያላቸውን አገልግሎት ያሳልጥላቸዋል፤ ወጪንም ይቆጥብላቸዋል ብለዋል፡፡ የኢት-ስዊች ቺፍ ፖርት ፎልዮ ኦፊሰር…
Read More
ካናዳ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች

ካናዳ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች

በካናዳ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አማካኝነት የወጣው ይህ ማስጠንቀቂያ ‹‹ወሳኝ ላልሆነ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ወደ ኢትዮጵያ እንዳትሄዱ› የሚል መልእክት ያለው ሲሆን ለዚህም የሰጠው ምክንያት የእርስ በእርስ ግጭት፣ አመፅ፣ የጦር መሳሪያ ግጭት ወንጀል እና የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት ናቸው። የጉዞ ማስጠንቀቂያው የፀጥታ ሁኔታው ድንገት ሊባባስ እንደሚችል አሳስቦም ይህ ማስጠንቀቂያ አዲስ አበባን እንደማይመለከት አስታውቋል፡፡ ይሁን እንጂ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ ዜጎቹም ቢሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ገልፆ በከተማው ውስጥ የወንጀል መጠኑ ከፍተኛ መሆኑንና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እየተካሄደ ያለው የትጥቅ ትግል ያለምንም ማስጠንቀቂያ ወደ ከተማው ሊዛመት የሚችልበት እድል እንዳለ አስታውቋል፡፡ ይህ ማስጠንቀቂያ እንዳለው የካናዳ ዜጎች ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ አማራ፣ ትግራይና ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች…
Read More
ኢትዮጵያ ሶስት ዜጎቿ በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ገለጸች

ኢትዮጵያ ሶስት ዜጎቿ በማርበርግ ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን ገለጸች

በአሁኑ ሰዓት በማርበርግ ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ በሕይወት ያለ ሰዉ አለመኖሩን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። እስካሁን ድረስ የሶስት ሰዎች ህይወት በማርበርግ ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸዉን ማጣታቸውንም ሚኒስቴሩ ጠቅሷል። ጤና ሚኒስቴር የማርበርግ በሽታ አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እንደገለጹት ሚኒስቴሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ የማርበርግ በሽታ መከሰቱን ካሳወቀበት ህዳር 3 ጀምሮ የበሽታዉ ምልክት ያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸዉ የተባሉ ሰዎችን ቦታዎች ላይ የመለየት ስራ እየሰራ ይገኛል። ሚኒስቴሩ እስካሁን ድረስ 17 የላብራቶሪ ናሙና ወስዶ የመረመረ ሲሆን፤ በሶስት ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል። እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ ስድስት ሰዎች የበሽታዉን ምልክት አሳይተዉ ህይወታቸዉ ቢያልፍም በላብራቶሪ የተረጋገጠዉ ግን ሶስት ሰዎች ላይ መሆኑን…
Read More
​ሳዑዲ ዓረቢያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ድንበር ሲያቋርጡ ማሰሯን ገለጸች

​ሳዑዲ ዓረቢያ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ድንበር ሲያቋርጡ ማሰሯን ገለጸች

አንደ ገልፍ ኒውስ ዘገባ የድንበር ጠባቂዎች ባለፉት አንድ ሳምንት ውስጥ 1,924 ሰዎች ሳዑዲ ዓረቢያ ለመግባት ሲሞክሩ በሕገ-ወጥ መንገድ ተይዘዋል ብለዋል። ከእነዚህ ውስጥ 62 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን፣ 37 በመቶ የመን እና ቀሪዎቹ ደግሞ የሌሎች አገሮች ዜጎች ናቸው። በተጨማሪም 32 ሰዎች ከሀገር ለመውጣት ሲሞክሩ ተይዘዋል። ​በዘመቻው ወቅት ሕገ-ወጥ ስደተኞችን በትራንስፖርት፣ በመጠለያ ወይም በቅጥር ሥራ በማገዝ የተጠረጠሩ ተጨማሪ 31 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ​በአሁኑ ወቅት 30,236 የውጭ አገር ዜጎች የሕግ ሂደቶች እስኪጠናቀቁ ድረስ ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ ታስረው ይገኛሉ። ​የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ማጓጓዝ፣ ማኖር ወይም በምንም መንገድ መርዳት እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስራት፣ እስከ 1 ሚሊዮን ሪያል በሚደርስ ቅጣት እና ጥቅም…
Read More
ኢትዮጵያ የኤርትራ ፖሊሲዬ “ሙሉ በሙሉ ከሸፈ” አለች

ኢትዮጵያ የኤርትራ ፖሊሲዬ “ሙሉ በሙሉ ከሸፈ” አለች

ከኤርትራ ጋር በትብብር ላይ የተመሰረተ፣ አዎንታዊ እና ገንቢ የረጅም ጊዜ ግንኙነትን ለመመስረት የሚያስችል አካሄድን ወይም ፖሊሲን ስንከተል ነበር ያሉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፖሊሲው አሁን "ሙሉ በሙሉ ከሽፏል" ብለዋል። ለፖሊሲው መክሸፍ "አጋጣሚውን መጠቀም አልተቻለም" ያሉትን የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን የኤርትራ አገዛዝ ተጠያቂ አድርገዋል። አገዛዙ በኢትዮጵያ ላይ እየተከተለ ባለው 'የተሳሳተ' ፖሊሲ ምክንያት ዘላቂ ግንኙነት ለመመስረት የተደረጉ ሙከራዎች ሁሉ ሙሉ በሙሉ መክሸፋቸውንም ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ትኩረቱን በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ ባሉ ወቅታዊ የፖለቲካና የደህንነት ሁነቶች ላይአድርጎ ትናንት ሐሙስ ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ የተናገሩት። በመድረኩ ሁነቶችን…
Read More
ኢትዮጵያ የውጭ ዜጎችን ጨምሮ ከ112 ዜጎችን ከክሪፕቶ ግብይት ጋር በተያያዘ አሰረች

ኢትዮጵያ የውጭ ዜጎችን ጨምሮ ከ112 ዜጎችን ከክሪፕቶ ግብይት ጋር በተያያዘ አሰረች

በክሪፕቶ ከረንሲ መተግበሪያዎች ጭምር በመታገዝ ህገ ወጥ የምንዛሬ ዝውውር ያደርጉ ነበር የተባሉ ቻይናውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ በተቀናጀ መንገድ ሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ አሻጥሮችን ሲፈጽሙ ደረስኩባቸው ያላቸውን 112 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ያስታወቀው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት 8 ቻይናውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ለመንግሥት ብዙሀን መገናኛዎች በላከው መግለጫ ይፋ አድርጓል። በመግለጫው በተደራጀ መንገድ በስውር ሲፈጸም ነበር ያለውን ህገ ወጥ የምንዛሬ ገንዘብ ዝውውርና አሻጥር ለማምከን የሚያስችል ምስጢራዊ የመረጃ ስምሪቶችን ሲያደርግ እንደቆየ ያስታወቀው አገልግሎቱ ቻይናውያኑን ጨምሮ 112 ኢትዮጵያውያንና የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች   በቁጥጥር  ሥር  መዋላቸውን፤ ከሕገ - ወጥ ተግባሩ ጋር ትስስር የነበራቸው አምስት መቶ አስራ ዘጠኝ የባንክ አካውንቶች መታገዳቸውን እንዲሁም የተለያዩ ኤግዚቢቶች መያዛቸውን…
Read More
ኢትዮጵያ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎቿን ከውጭ ሀገራት መመለሷን ገለጸች

ኢትዮጵያ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎቿን ከውጭ ሀገራት መመለሷን ገለጸች

ከመስከረም ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ከ17 ሺሕ በላይ ዜጎች ወደ ሀገር መመለሳቸው ተገልጿል። በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ዜጎችን ከ17 ሺሕ በላይ ዜጎችን ከመስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በተሰራ ሥራ መመለስ መቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ በተለያዩ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል፡፡ "ከውጭ ግንኙነት ቁልፍ ሥራዎች አንዱ የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ነው" ያለው ሚኒስቴሩ ፖሊሲውን በአግባቡ ለመተግበር በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎችን መብት ማስከበር፣ ለዜጎች ተገቢ የቆንስላ አገልግሎት መስጠት፣ በሄዱበት ሀገር ሕጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውና የሀገሩ መንግሥት ዜጎቻችን ሀገራቸውን እንዲለቁ ሲወስን መብታቸው፣ ክብራቸውና…
Read More
በኢትዮጵያ ታግቶ የነበረው ኬንያዊ ዜጋ መለቀቁ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ታግቶ የነበረው ኬንያዊ ዜጋ መለቀቁ ተገለጸ

በኢትዮጵያ በአጋቾች ታግቶ የቆየው ኬንያዊ ዜጋ 3 ሚሊየን ሽልንግ ከተከፈለ በኋላ መለቀቁን ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አስታወቁ። የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር እና በአዲስ አበባ ያሉት አምባሳደራቸው ባደረጉት ጥረት 3 ሚሊየን የኬንያ ሽልንግ ለአጋቾች ከተከፈለ በኋላ ሳሙኤል ንጃጊ የተባለው ዜጋቸው መለቀቁን ገልፀዋል። ሳሙኤል ከሳምንት በፊት በደብረ ብርሃን ከተማ ተቀጥሮ ከሚሰራበት ድርጅት ታግቶ የተወሰደ ሲሆን የኬንያ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ካሳወቀ በኋላ ድርድሮች መደረጋቸው ተዘግቧል። ዊሊያም ሩቶ 3 ሚሊየን የኬንያ ሽልንግ በአጋቾች መጠየቁን ገልፀው ሳሙኤል ይሰራበት የነበረው ድርጅት ክፍያውን መክፈሉን ገልጸዋል። ሳሙኤል ከተለቀቀ በኋላ አዲስ አበባ በሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ መቆየቱንና ወደ ኬንያ ሄዶ ከቤተሰቦቹ ጋር መቀላቀሉ ሲነገር ሩቶ ዜጎች…
Read More
ኢትዮጵያና ጅቡቲ ሁለተኛውን የኃይል መስመር ዝርጋታ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያና ጅቡቲ ሁለተኛውን የኃይል መስመር ዝርጋታ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያን ጋላፊ ማከፋፈያ ጣቢያ ከጅቡቲው ናጋድ ማከፋፈያ ጣቢያ ጋር በሚያገናኘው በዚህ ፕሮጀክት፤ የ230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ እንደሚከናወን በጅቡቲ በተካሄደው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገልጿል፡፡ በጅቡቲ ግዛት የሚዘረጋውን 190 ኪሎ ሜትር ጨምሮ በአጠቃላይ 292 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን የኃይል መስመር ፕሮጀክት በ18 ወራት ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙ ተዘግቧል፡፡ ዓለም ባንክ ዝርጋታውን በ55 ሚሊዮን ዶላር ብድር የሚደግፈው ሲሆን፤ የግንባታ ውሉ ትራንስሬይል ሊሚትድ ለተሰኘ የህንድ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ መሰጠቱን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡ የጅቡቲ የኢነርጂ እና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ጉዲ፤ “ፕሮጀክቱ ታዳሽ የኃይል ሀብቶችን በመጠቀም ላይ የተመሠረተ ብሔራዊ የኃይል ፖሊሲ እንድንተገብር ይረዳናል፣ ይህም 100 በመቶ የንጹህ ኃይል ግባችንን እንድናሳካ ያስችለናል” ሲሉ ተናግረዋል። የኃይል መስመር…
Read More