19
Sep
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ እንዳስታወቀው በመንግስት የጸጥታ ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በየጊዜው የተኩስ ልውውጥ የሚስተዋልበት አማራ ክልል በ2017 የትምህርት ዘመን ከ7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዘገብ አቅዶ ነበር፡፡ ይሁንና ከነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ የተመዘገቡት ተማሪዎች 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ተማሪዎች ብቻ መሆናቸውን ገልጿል፡፡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ፣ " ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 292 ሺሕ በላይ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 1.2 ሚሊዮን በላይ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ 180 ሺሕ ተማሪዎች ተመዝግበዋል " ብሏል፡፡ " በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምዝገባው እየተካሄደ ነው፡፡ ትንሽ እሱ ላይ መዘግየት ይታያል፡፡ እስካሁን በጠቅላላ ወደ 1.7 ሚሊዮን ተማሪዎች ናቸው የተመዘገቡት የእቅዱን ወደ 24 ፐርሰንት…