AddisAbaba

በአማራ ክልል የሚገኙ 10 ዩንቨርሲቲዎች በጦርነት ምክንያት ተማሪዎቻቸውን መጥራት አልቻሉም

በአማራ ክልል የሚገኙ 10 ዩንቨርሲቲዎች በጦርነት ምክንያት ተማሪዎቻቸውን መጥራት አልቻሉም

አማራ ክልል የሚገኙ አስር ዩኒቨርሲቲዎች በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ለነባር እንዲሁም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎቻቸው ጥሪ ሳያደርጉ ወራት መቆጠሩ ይታወቃል፡፡ ከአማራ ክልል ውጪ የሚገኙ ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን ጠርተው በማስተማር ላይ ሲሆኑ በአማራ ክልል ባሉ ዩንቨርስቲዎች የተመደቡ ተማሪዎች ግን እስካሁን አልተጠሩም። ይህንን ተከትሎም ተማሪዎቹ ለስነልቦና እና ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውን በተደጋጋሚ በማንሳት ላይ ሲሆኑ ዩኒቨርሲቲዎቹ ጥሪ ሳያደርጉ አራት ወራት በማለፉ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ መግባታቸውንም ይጠቁማሉ፡፡ "ያለ ትምህርት ቁጭ ብለን ወራት አልፈዋል፣ ፍትህ እንሻለን" የሚሉት ተማሪዎቹ፤ ወደ ሌሎች የትምህርት ተቋማት በጊዚያዊነት መዘዋወርን ጨምሮ አማራጭ መፍትሔዎች እንዲፈለግላቸው ጠይቀዋል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ በአማራ ክልል ያሉ ዩንቨርሲቲዎች በቅርቡ ለተማሪዎቻቸው ጥሪ እንዲያስተላልፉ መግባባት ላይ መደረሱን አስታውቋል፡፡ በትምህርት ሚኒስቴር…
Read More
ቢጂአይ ኢትዮጵያ በጦርነት ምክንያት ስራው መጎዳቱን ገለጸ

ቢጂአይ ኢትዮጵያ በጦርነት ምክንያት ስራው መጎዳቱን ገለጸ

በኢትዮጵያ ካሉ አልኮል አምራች ኩባንያዎች መካከል ዋነኛው የሆነው ቢጂአይ ኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ ኤርቬ ሚላድ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ስራ አስፈጻሚው መግለጫ ከሰጡባቸው ጉዳዮች መካከል የድርጅቱ አዲስ እቅዶች፣ ዋና ቢሮውን ወደ ሰበታ ስለማዞሩ እና ማይጨው፣ ለፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ስለተሸጠው ዋና መስሪያ ቤት ቦታ፣ ትርፍ እና ሌሎችም ጉዳዮች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ኤርቬ ሚላድ በመግለጫቸው ቢጂአይ ከዚህ ቀደም እራሳቸዉን ችለዉ አክሲዮን ማህበር ተብለዉ ሲጠሩ የነበሩት ኩባንያዎች ወደ ቢጂአይ ይዋሃዳሉ ብለዋል፡፡ ድርጅቱ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ የቢራ ምርቱን አሁን ካለበት 5 ሚሊዮን ሄክቶሊትር ወደ 10 ሚሊዮን ሄክቶ ሊትር ማሳደግ የሚያስችሉ የምርት መሻሻያ ስራዎችን እንደሚሰራም ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡ ከሚሰሩት ስራዎች መካከልም የቢራ ፋብሪካዎችን ምርታማነትን ማሳደግ፣ አዳዲስ ደንበኞችን እና…
Read More
የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ቢሮውን ሊዘጋ እንደሚችል አስጠነቀቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ቢሮውን ሊዘጋ እንደሚችል አስጠነቀቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ከአንድ ወር በፊት በአዲስ አበባ ያሉ ሁለት የባንኩ ሰራተኞች በኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች ድብደባ፣ እስር እና እንግልት እንደደረሰባቸው አስታውቆ ነበር። ባንኩ እንዳለው ሁለት ሰራተኞቹ የቬና የዲልሎማሲ ጥበቃ ስምምነትን እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ቢሮ አስተናጋጅ ሀገራት ስምምነትን የጣሰ ክስተት በኢትዮጵያ መፈጸሙንም ገልጿል። የተፈጠረውን ክስተት ለኢትዮጵያ መንግሥት በይፋ ማመልከቱን የሚገልጸው የአፍሪካ ልማት ባንክ ጉዳዩ መፈጸም እንደሌለበት፣ ህግ መጣሱን እና ጉዳዩ ተመርምሮ እርምጃ እንደሚወሰድ በኢትዮጵያ በኩል ቃል ተገብቶልኛል ሲልም በወቅቱ አስታውቆ ነበር፡፡ ባንኩ አሁን ላይ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ቃል በገባው መሰረት በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዳልወሰደ እና ጉዳዩን ስለመመርመሩ መረጃ እንዳልሰጠው ገልጿል፡፡ ይህን ተከትሎም ባንኩ የኢትዮጵያ ቢሮውን ሊዘጋ እና…
Read More
ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር እየተነጋገረች መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር እየተነጋገረች መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ላለችው የኢኮኖሚ ሪፎርም እና ችግር ላይ የሚገኘውን የፋይናንስ ሁኔታዋን ለመቅረፍ ያግዛት ዘንድ ከአለም አቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር እየተነጋገረች መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። በሀገሪቱ የሚታየውን አመታዊ የበጀት ጉድለቷን ለሞሙላት ያግዛት ዘንድ በልዩ ሁኔታ ከአይኤም ኤፍ ብድር መጠየቋን ዘገባው አመላክቷል። የመንግሥት ባለስለጣናት  ባለፈው ሳምንት ከአለም አቀፍ ቦንድ ገዢዎች ጋር በነበራቸው ስብሰባ በቀጣዩ የፈረንጆች አመት 2024 መጀመሪያ ሶስት ወራት ከአይ ኤም ኤፍ ጋር የብድር ስምምነት ላይ እደርሳለን ብለው እንድደሚያምኑ ተናግረዋል። ሀገሪቱ ያለት የገቢ ንግድ ማስኬጃ የውጭ ምንዛሬ መጠን ክምችት ዜሮ ነጥብ ሁለት በመቶ ብቻ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል። ኢትዮጵያ የገጠማትን የበጀት ጉድለት ለመሙላት…
Read More
በቢሾፍቱ ከተማ በአምስት ቢሊዮን ዶላር አዲስ የኤርፖርት ከተማ ሊገነባ ነው

በቢሾፍቱ ከተማ በአምስት ቢሊዮን ዶላር አዲስ የኤርፖርት ከተማ ሊገነባ ነው

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ አዲሱን 5 ቢሊየን ዶላር ሚያወጣ ‘የኢትዮጵያ አየር  መንገድ ከተማ’ ግንባታ በአራት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡ አየር መንገዱ “ኤርፖርት ሲቲ” ብሎ የሚጠራውን ግንባታ ለመጀመር ከጫፍ የደረሰው እየጨመረ የመጣውን የደንበኞች ፍላጎት ለማርካት መሆኑን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የንግድ ሥራ ዘርፍ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ለማ ያደቻ ተናግረዋል፡፡ የ ‘ዓየር መንገድ ከተማው’ ካልተገነባ ዓየር መንገዱ በዘርፉ እያስመዘገበ ካለው ፈጣን ዕድገት አንጻር እንደሚፈተን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፕሮጀክቱ መታቀዱን አብራርተዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በአጠቃላይ 5 ቢሊየን ዶላር በጀት የተያዘለት ሲሆን፥ በዓመት 100 ሚሊየን መንገደኞችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል። አሁን ላይ ዓየር መንገዱ በኦሮሚያ ክልል ከቢሾፍቱ ከተማ ጥቂት ወጣ ብሎ በሚገኝ ሥፍራ የመጀመሪያውን የ ‘ዓየር መንገድ…
Read More
ብሔራዊ ሎተሪ የ8 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እድለኛ እንደጠፋበት ገለጸ

ብሔራዊ ሎተሪ የ8 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እድለኛ እንደጠፋበት ገለጸ

ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር በየጊዜው ለሽፓጭ ከሚያውላቸው የእድል ሎተሪዎች መካከል የእንቁጣጣሽ ሎተሪ አንዱ ነው። 20 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ይህ እጣ ባሳለፍነው ጷግሜ 2015 ዓም እጣው የወጣ ሲሆን 1820259 ደግሞ የመጀመሪያ እድለኛ ቁጥር እንደሆነ በወቅቱ ተገልጿል። የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድር ኮሙንኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴድሮስ ንዋይ ለዓልዐይን እንዳሉት "ባሳለፍነው ጷግሜ ላይ ከወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ከሶስት እጣ አሸናፊ በስተቀር የሁለት እጣ አሸናፊዎች እስካሁን አልመጡም" ብለዋል። ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳድሩ የሁለት እጣ እድለኞች ማለትም የስምንት ሚሊዮን ብር አሸናፊዎች እስከ ቀጣዩ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ካልመጡ ገንዘቡ ለመንግሥት ገቢ ይሆናልም ብለዋል። 20 ሚሊዮን ብር ከሚያሸልመው እጣ ቁጥር ውስጥ እስካሁን በመተሀራ ከተማ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ በወዛደርነት…
Read More
ኤምፔሳ ሳፋሪኮም ከ1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞቼን ልሸልም ነው አለ

ኤምፔሳ ሳፋሪኮም ከ1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞቼን ልሸልም ነው አለ

ኤምፔሳ ሳፋሪኮም አዲስ ተጠቃሚ እና ግብይታቸውን በM-PESA የሚያካሒዱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን፣ ወኪሎችን እና ነጋዴዎችን የሚሸልምበት ከታህሳስ 1 ቀን እስከ መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የ9ዐ ቀናት የሽልማት መርኃ ግብር ትናንት ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ በይፋ አስጀምሯል። ተረክ በኤምፔሳ ደንበኞች እና ድርጅቶች የኤምፔሳ አዲስ ተጠቃሚ በመሆናቸው እና ግብይታቸውን በኤምፔሳ በማካሔዳቸው የእጣ ቁጥሮችን በመሸለም ስለ ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎቱ የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር እና አጠቃቀሙን ለማጎልበት ያለመ መርኃ ግብር ነው። በእጣዎቹ የሚገኙ ሽልማቶች አራት መኪኖች፣ 12 ባጃጆች፣ 2160 የስልክ ቀፎዎች እና የአየር ሰዓት ስጦታዎች ይሆናሉ፡፡ እያንዳንዳቸው ደንበኞች በአንድ ቀን የሚደርሳቸው ከፍተኛ የእጣ ብዛት 10 ሲሆን ይህም በየእለቱ፣ በሁለት…
Read More
ኢትዮጵያ ብድራቸዉን መክፈል ከማይችሉ ሀገራት ተርታ ተመደበች

ኢትዮጵያ ብድራቸዉን መክፈል ከማይችሉ ሀገራት ተርታ ተመደበች

መንግስት ከወሰደዉ የረጅም ጊዜ ብድር እና ወለድ አከፋፈል ዙሪያ ከአበዳሪዎች ጋር በዚህ ሳምንት ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ ማቀዱ ተገልጿል የኢትዮጵያ መንግስት እ.ኤ.አ በ2014 በዩሮ ቦንድ ከተበደረዉ የ1 ቢሊዮን ዩሮ እና ወለዱን 33 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የመክፈል አቅም ስለመኖሩ አበዳሪዎች ከጥርጣሬ ዉስጥ መገባታቸዉን ብሉምበርግ አስነብቧል። በዘገባዉ ኢትዮጵያ ዛምቢያንና ጋናን በመከተል በአፍሪካ የከሰሩ ሀገራት ተርታን ልትቀላቀል ከጫፍ የደረሰች መሆኑን ዘገባዉ ጠቅሷል። በተያዘዉ ሳምንት ሐሙስ መንግስት ከአበዳሪ አካላት ጋር ዉይይት የማድረግ እቅድ ስለመኖሩ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡ መንግስት ከአንዳንድ አበዳሪ አካላት ጋር ባሳለፍነዉ ሳምንት የተገደበ ዉይይት አድርጎ አበዳሪዎች ኢትዮጵያ ያለባትን የ33 ሚሊዮን ዶላር የወለድ እዳ የመክፈል አቅም እንደሌላት ተገንዝበዋል ብሏል። ለዚህም ኢትዮጵያ የዉጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ…
Read More
ፕሮፌሰር ሙላቱ ለማ የዓመቱ ምርጡ ፕሮፌሰር ተባሉ

ፕሮፌሰር ሙላቱ ለማ የዓመቱ ምርጡ ፕሮፌሰር ተባሉ

ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው ዓለም አቀፉ የፕሮፌሰሮች ማህበር ኢትዮጵያዊውን ፕሮፌሰር ሙላቱ ተሰማ የዓመቱ ምርጥ ምሁር በሚል እውቅና ሰጥቷል፡፡ ማህበሩ በየዓመቱ በመላው ዓለም ላሉ ፕሮፌሰሮች እውቅና የሚሰጥ ሲሆን የ2023 ዓመት እውቅናን ለኢትዮጵያዊው የሂሳብ ፕሮፌሰር ማድረጉ ተገልጿል፡፡ በመላው ዓለም ያሉ ፕሮፌሰሮች ባስገኙት ስኬት፣ የትምህርት አመራር፣ በሙያው ላይ ባደረጉት ቆይታ እና ሌሎች ጥረቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በየዓመቱ በዚህ ማህበር ይሸለማሉ፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መረጃ መሰረት ፕሮፌሰር ሙላቱ ተሰማ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡ የሶስተኛ ድግሪያቸውን ደግሞ በአሜሪካው ኬንት ስቴት ዩንቨርሲቲ እንዳገኙ የተገለጸው ፕሮፌሰር ሙላቱ ላለፉት 28 ዓመታት ደግሞ በዚያው በአሜሪካ ሳቫና ስቴት ዩንቨርሲቲ በማስተማር ላይ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ ፕሮፌሰር…
Read More
አማራ ባንክ ፕሬዝዳንቱን ከሀላፊነት አነሳ

አማራ ባንክ ፕሬዝዳንቱን ከሀላፊነት አነሳ

የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኄኖክ ከበደ ከሓላፊነታቸው ተነሱ የአማራ ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ ፕሬዝዳንቱ አቶ ሔኖክ ከበደ ባንኩን ለ460 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ዳርገዋል በሚል ከሀላፊነት አንስቷል፡፡ ባንኩ ከዋና ሥራ አስፈጻሚው በተጨማሪም የኮርፖሬት አገልግሎት ዋና መኰንኑን አቶ ክንዴ አበበን፣ የአፈጻጸም ድክመት አሳይተዋል በሚል በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር  መላኩ ፈንታ ፊርማ ከሓላፊነታቸው አንሥቷል። የባንኩ ቦርድ ውሳኔውን ያሳለፈው፣ ኹለቱም ከፍተኛ ሓላፊዎች፣ ከተሾሙበት ዕለት ጀምሮ፣ በየጊዜው በሚሳዩት የሥራ አፈጻጸም ድክመት፣ የባንኩን ስትራቴጂያዊ ግቦች እና ቁልፍ የአፈጻጸም መመዘኛዎችን ማሳካት አልቻሉም ተብሏል፡፡ ባንኩ በ2014/15 ዓ.ም. ከ306 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ለማስመዝገብ ዐቅዶ የነበረ ቢኾንም፣ ብር 460,286,000 ኪሳራ አስመዝግቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ በሌላቸው ሥልጣን ባሳለፉት አስተዳደራዊ…
Read More