20
Dec
በኢትዮጵያ ካሉ አልኮል አምራች ኩባንያዎች መካከል ዋነኛው የሆነው ቢጂአይ ኢትዮጵያ ስራ አስፈጻሚ ኤርቬ ሚላድ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ስራ አስፈጻሚው መግለጫ ከሰጡባቸው ጉዳዮች መካከል የድርጅቱ አዲስ እቅዶች፣ ዋና ቢሮውን ወደ ሰበታ ስለማዞሩ እና ማይጨው፣ ለፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ስለተሸጠው ዋና መስሪያ ቤት ቦታ፣ ትርፍ እና ሌሎችም ጉዳዮች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ኤርቬ ሚላድ በመግለጫቸው ቢጂአይ ከዚህ ቀደም እራሳቸዉን ችለዉ አክሲዮን ማህበር ተብለዉ ሲጠሩ የነበሩት ኩባንያዎች ወደ ቢጂአይ ይዋሃዳሉ ብለዋል፡፡ ድርጅቱ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ የቢራ ምርቱን አሁን ካለበት 5 ሚሊዮን ሄክቶሊትር ወደ 10 ሚሊዮን ሄክቶ ሊትር ማሳደግ የሚያስችሉ የምርት መሻሻያ ስራዎችን እንደሚሰራም ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡ ከሚሰሩት ስራዎች መካከልም የቢራ ፋብሪካዎችን ምርታማነትን ማሳደግ፣ አዳዲስ ደንበኞችን እና…