20
Jun
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የፋኖ ሀይሎች በተቆጣጠሯቸውና ወጣ ገባ በሚሉባቸው ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ የፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ሀይሎችን መልሼ አደራጃለሁ የሚል ውሳኔ ከወሰነበት ጀምሮ በአማራ ክልል በፋኖ ታጣቂዎች እና የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ አንድ ዓመት አልፎታል፡፡ በዚህ ጦርነት ምክንያት በክልሉ ለ10 ወራት የዘለቀ የአስቸኳይ አዋጅ የታወጀ ሲሆን ካሳለፍነው ሳምንት ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀመሮም የአዋጁ ጊዜ ቢያበቃም ክልሉ በኮማንድ ፖስት እየተዳደረ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለም ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የተወሰኑ ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ የባንክ አገልግሎት ከተቋረጠባቸው ወረዳዎች መካከል መንዝ ላሎ፣ ግሼ ራቤል፣ አንፆኪያ ገምዛ እና ቀወት ወረዳዎች እንደሚገኙበት ዋዜማ ሬዲዮ…