አካባቢ ጥበቃ

ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ አዋጭነታቸው ያልተረጋገጡ ፕሮጀክቶችን እንዳትገነባ ኢትዮጵያ ጠየቀች

ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ አዋጭነታቸው ያልተረጋገጡ ፕሮጀክቶችን እንዳትገነባ ኢትዮጵያ ጠየቀች

ኢትዮጵያ በጸጥታው ምክር ቤት በግብጽ ለቀረበባት ክስ ምላሽ ሰጥታለች ከአንድ ሳምንት በፊት ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ አምስተኛው ዙር ውሃ ሙሌት ማከናወኗ እና ተጨማሪ ተርባይኖች ሀይል ማመንጨት መጀመራቸውን ይፋ ማድረጓ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም ግብጽ ኢትዮጵያ በግድቡ ለይ የተናጠል እርምጃ ወስዳለች በሚል ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ክስ አስገብታለች፡፡ በግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተፈረመው ይህ ደብዳቤ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2015 የተፈረመውን የመርህ ስምምነት ጥሳለች፣ ድርጊቱም ለአካባቢው ሀገራት አለመረጋጋት የሚሆን ነው፣ ግብጽ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በተመድ ቻርተር አማካኝነት እርምጃ ትወስዳለች ሲልም ያትታል፡፡ ኢትዮጵያ በግብጽ ለቀረበባት ክስ በይፋ ባሳለፍነው ቅዳሜ ለተመድ ይፋዊ ምላሽ መስጠቷን አል ዐይን ከታማኝ ምንጮች አረጋግጧል፡፡ አል ዐይን የተመለከተው ይህ ደብዳቤ…
Read More
ግብጽ በድጋሚ ኢትዮጵያን በጸጥታው ምክር ቤት ላይ ከሰሰች

ግብጽ በድጋሚ ኢትዮጵያን በጸጥታው ምክር ቤት ላይ ከሰሰች

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ተቃውሞ አለኝ የምትለው ግብጽ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ላይ ከሳለች፡፡ ግብጽ በዛሬው ዕለት ለጸጽታው ምክር ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸችው ኢትዮጵያ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ ለአምስተኛ ዓመት ውሃ ሙሌት አከናውናለች ይላል፡፡ በግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ስደተኞች እና ግብጻዊያን አርበኞች እንደተጻፈ የተገለጸው ይህ ደብዳቤ ኢትዮጵያ የግብጻዊያንን ጥቅም በሚጻረር መልኩ የውሃ ሙሌት እያካሄደች ነው ብሏል፡፡ በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደል አቲ የተፈረመው ይህ የተመድ ደብዳቤ ኢትዮጵያ፣ግብጽ እና ሱዳን በፈረንጆቹ 2015 ላይ የተፈራረሙትን ስምምነት በመጣስ የግድቡ ውሃ ሙሌት በተናጠል ተከናውኗል፣ ይህም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም የሚጎዳ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የግድቡን…
Read More
ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በኋላ ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል መሸጥ እንደምትጀምር ገለጸች

ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በኋላ ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል መሸጥ እንደምትጀምር ገለጸች

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሀይል የማመንጨት አቅም በዕጥፍ ጨምሯል ተብሏል ኢትዮጵያ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የምታመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ከእጥፍ በላይ ማሳደጓን አስታወቀች። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ሥራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች አገልግሎት በመጀመራቸዉ ከግድቡ የሚመረተዉ የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ወደ 1 ሺሕ 550 ሜጋዋት ከፍ ብሏል። ከዚሕ ቀደም ሥራ የጀመሩት ሁለት ተርባይኖች እያንዳዳቸዉ 375 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ሲያመነጩ ቆይተዋል፡፡ ሰሞኑን የተመረቁት ሁለት ተጨማሪ ተርባይኖች ደግሞ እያንዳዳቸዉ 400 ሜጋዋት ኃይል እንደሚያመነጩ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ ከግብፅና ሱዳን ጋር የሚያወዛግባትን ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ በአባይ ወንዝ ላይ መገንባት የጀመረችዉ ከመጋቢት 2003 ዓ.ም ጀምሮ ነበር። ይህ የአፍሪካ ትልቁ ግድብ በ2014 ዓ.ም ላይ…
Read More
በአዲስ አበባ ያለው ከባድ አየር ንብረት የአውሮፕላን በረራዎችን አስተጓጎለ

በአዲስ አበባ ያለው ከባድ አየር ንብረት የአውሮፕላን በረራዎችን አስተጓጎለ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ በተከሰተው ከፍተኛ ጭጋጋማ አየር ምንክንያት ወደ ሌላ አየር ማረፊያዎች እያዘዋወረ መሆኑን አስታወቀ በአዲስ አበባ በተከሰተዉ ከፍተኛ ጭጋጋማ አየር አብዛኛው በረራዎች ቦሌ አዉሮፕላን ማረፊያ ሊያርፍ ባለመቻሉ ምክንያት ወደ ሌላ አየር ማረፊያዎች እንዲቀየሩ መደረጉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል ። አየር መንገዱ እንደገለፀው ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ባለዉ ከፍተኛ ጭጋግ ( ጉም) ምክንያት የአየር ማረፊያዎችን ወደ ሌላ ቦታ እያዘዋወረ መሆኑን እና ይህም በሀገር ዉስጥ እና በአለም አቀፍ በረራዎች ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል ብሏል። በተጓዦች ላይ ለደረሰዉ መጉላላት ይቅርታ የጠየቀው አየር መንገዱ በተጓዦች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ መጉላላቶችን ለመቀነስ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አውሮፕላን ጣቢያ…
Read More
ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ያሉ የዲፕሎማሲ ተቋማት በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን እንዳያስገቡ ከለከለች

ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ያሉ የዲፕሎማሲ ተቋማት በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን እንዳያስገቡ ከለከለች

ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን እንዳያስገቡ እገዳ ጥላለች፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ዲፕሎማቲክ እና ሚሲዮኖች የነዳጅ መኪናዎችን እንዳያስገቡ እገዳ የጣለች ሲሆን በምትኩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ማስመጣት ብቻ እንዳለባቸው አሳስቧል። የዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በአዲስ አበባ ለሚገኙ የዲፕሎማቲክ እና የቆንስላ ሚስዮኖች፣ ለቀጠናው እና ለአለም አቀፍ ድርጅቶች በፃፈው ደብዳቤ " የተወሰደው እርምጃ ኢትዮጵያ የበካይ ጋዝ ልዕቀት ቅነሳና ወደ ታዳሽ ኃይል ለመሸጋገር ካላት ቁርጠኝነት የተነሳ መሆኑን" አስረድተዋል ። በዚህም የዲፕሎማሲ መብት ያላቸው ሁሉ ተሽከርካሪዎችን ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የተሰጠውን አቅጣጫ አክብረዉ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ብቻ ማስመጣት ይጠበቅባቸዋል ብሏል። ኢትዮጵያ ከመጋቢት 2016 ዓ.ም ጀምሮ በነዳጅ የሚሰሩ የግል አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ወደ…
Read More
አሚአ ኩባንያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ሀይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

አሚአ ኩባንያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ሀይል ማመንጫ ሊገነባ ነው

ኢትዮጵያ በ620 ሚሊዮን ዶላር የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለመገንባት ከአለም አቀፉ አሚአ ፓወር ኩባንያ ጋር ተስማምታለች፡፡ ስምምነቱ በዱባይ ከአራት ቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኤሌክተሪክ እና አሚአ ኩባንያ ሀላፊዎች መካከል ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል ለሚገነባዉ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ለማልማት በታዳሽ ኃይል ልማት ላይ ከተሰማራው እና መቀመጫዉን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኩባንያ ካደረገዉ ከአሚአ ፓወር ጋር ስምምነት አድርጓል። በታዳሽ ኃይል ልማት፣ ግንባታና አስተዳደር ዘርፍ የተሰማራው አሚአ ፓወር በአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል 300 ሜጋ ዋት አመንጭቶ ለኢትዮጵያ ለመሸጭ ነው ሥምምነቱን የፈረመው። በኢትዮጵያ 300 ሜጋ ዋት የንፋስ ሃይል ፕሮጀክትን ለማልማት እና ለማንቀሳቀስ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ጋር የኃይል ግዢ ስምምነት እና የትግበራ ስምምነት መፈራረሙን ያስታወቀው…
Read More
በጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ ይችላል ተባለ

በጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ ይችላል ተባለ

በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን በደረሰው ተከታታይ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ያገኘውን መረጃ መሠረት አድርጎ ባወጣው የሁኔታዎች መግለጫ ላይ በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝ እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል አመልክቷል። እሁድ ሐምሌ 14 እና ሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ተቀብረው የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ሥራ ዛሬም ለአራተኛ ቀን እየተካሄደ ነው። በአደጋው ስፍራ ዛሬን ጨምሮ በአካባቢው እየጣለ ባለው ዝናብ ውስጥ ጭምር ከተንሸራተተው መሬት ስር ለማውጣት የሚደረገው የነፍስ አድን ጥረት ቀጥሏል።…
Read More
በኢትዮጵያ በመሬት መንሸራተት አደጋ ከ260 በላይ ዜጎች ሞቱ

በኢትዮጵያ በመሬት መንሸራተት አደጋ ከ260 በላይ ዜጎች ሞቱ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ከትናንት በስቲያ በደረሰ የመሬት ናዳ አደጋ የሞቱ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ነው። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት ናዳ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የመጣ ሲሆን እስከ ትንናት ምሽት ድረስ የሟቾች ቁጥር 229 ነበር። የገዜ ጎፋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ የሟቾች ቁጥር ወደ 260 ማሻቀቡን ተናግረዋል። እስካሁን በተደረገው ፍለጋ ሴቶችና ሕፃናትን ጨምሮ በድምሩ የ260 ሰዎች አስክሬን የተገኘ ሲሆን፣ የአስክሬን ፍለጋ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችልና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን  ተናግረዋል። አደጋው መጀመሪያ ሶስት ቤተሰብ ላይ…
Read More
ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማዕቀፍን አጸደቀች

ደቡብ ሱዳን የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በፓርላማ በማጽደቅ ስድስተኛ ሀገር ሆናለች፡፡ የናይል ተፋሰስ አባል የሆኑ 11 ሀገራት በኡጋንዳ ኢንተቤ ባደረጉት ስምምነት የናይል ወንዝን ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል የጋራ ስምምነት ነው፡፡ ስምምነቱ ከ11 የናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ስድስት ሀገራት በፓርላማ ካጸደቁ ቋሚ የናይል ተፋሰስ ሀገራት ኮሚሽን ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ መግባት ይችላል ተብሏል፡፡ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ እንደገለጹት የናይል ስምምነት ማዕቀፍን በአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል ከተፈረመ ቆይቷል፡፡ አምስት ሀገራት በፓርላማቸው አጽድቀው ነበር፡፡ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ለመመስረት የሚጠበቀው ስድስተኛ ሀገር በፓርላማ እስኪያጸድቅ ድረስ ነበር፤ ደቡብ ሱዳን አጸድቃለች ብለዋል፡፡ ስድስት ሀገራት የናይል ስምምነት ማዕቀፍን ማጽደቃቸው ፋይዳው ከፍተኛ ነው ያሉት አምባሳደሩ…
Read More
ኢትዮጵያ በየዓመቱ 100 ሺህ ሔክታር መሬት በአዲስ የቡና ዝርያ እየተካች መሆኗ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በየዓመቱ 100 ሺህ ሔክታር መሬት በአዲስ የቡና ዝርያ እየተካች መሆኗ ተገለጸ

የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር ላይ ባደረሱት ጥቃት የኢትዮጵያ ቡና ንግድ ለሶስት ቀናት ተስተጓጉሎ እንደነበር ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት የውጪ ንግድ አፈጻጸም ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንዳሉት ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት ውስጥ 350 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነበር ብለዋል፡፡ ይሁንና አፈጻጸሙ 298 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ሀገራት የምትልከው ቡና በቀይ ባህር በኩል በመሆኑ እና የሀውቲ ታጣቂዎች በሚያደርሱት ጥቃት ምክንያት መስጓጎል ገጥሞት እንደነበርም ተገልጿል፡፡ እንደ ዋና…
Read More