Blog

ኢትዮጵያ የጉበት በሽታ እየተስፋፋባቸው ካሉ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ ተገለጸ

ኢትዮጵያ የጉበት በሽታ እየተስፋፋባቸው ካሉ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗ ተገለጸ

የዓለም ጉበት በሽታ ጉባኤ በፖርቹጋል ተካሂዷል፡፡ በዚህ ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው በዓለማችን በየዕለቱ 3 ሺህ 500 ሰዎች በጉበት በሽታ እየሞቱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት የኤችአይቪ፣ ሄፓ ታይተስ እና ተላላፊ በሽታዎች ፕሮግራም ሃላፊ ሜግ ዶሂርቴ እንዳሉት በጉበት በሽታ ከሚሞቱት ውስጥ 83 በመቶዎቹ በሄፓታይተስ ቢ በተሰኘው የጉበት በሽታ የሚሞቱ ናቸው ብለዋል፡፡ በጉበት በሽታ የሚጠቁ ዜጎች እየጨመረ ነው ያሉት ሃላፊው 63 በመቶ ያህሉ ተጠቂዎች በአፍሪካ የሚገኙ ዜጎች እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡ በየዕለቱ ስድስት ሺህ ሰዎች በጉበት በሽታ እየተጠቁ ነው ያለው የዓለም ጤና ድርጅት ተጠቂዎች በቂ ህክምና እያገኙ እንዳልሆነም አስታውቋል፡፡ በሽታው ከተስፋፋባቸው ሀገራት መካከል 75 በመቶ ያህሉ ሽታው እየተስፋፋባቸው ካሉ የዓለማችን ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ቻይና፣ ባንግላዲሽ፣ ናይጀሪያ፣ሕንድ…
Read More
ኢትዮጵያ ከ6 ሺህ በላይ የስፖርት ውርርድ ቤቶችን ዘጋች

ኢትዮጵያ ከ6 ሺህ በላይ የስፖርት ውርርድ ቤቶችን ዘጋች

በአዲስ አበባ ባለፉት 9 ወራት ውስጥ ከ6 ሺህ በላይ የስፖርታዊ ውርርድ ቤቶች መታሸጋቸው ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ባለፉት 9 ወራት የህብረተሰቡን ሰላም አውከዋል ባላቸው የተለያዩ ስራዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡ የቢሮው ሀላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ የውርርድ ቤቶችን ጨምሮ ጫት ማስቃም፣ ሽሻ ማስጨስና የመሳሰሉ ጉዳዮች ይፈፀሙባቸው የነበሩና የወንጀል ድርጊት የሚታይባቸው ተግባራት ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ትምህርት ቤቶች አካባቢ የመማር ማስተማር ሂደትን እያስተጓጉሉ የነበሩ ናቸውም ተብሏል። የከተማዋ አስተዳድር ከዘጋቸው ተቋማት መካከል 6 ሺህ 726 የሚሆኑ የስፖርታዊ ውርርድ  ቤቶች መታሸጋቸውን አስታውቋል፡፡ በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው የነበሩ የንግድ ድርጅቶች ወደ ሌላ የስራ ዘርፍ እንዲቀይሩ እየተደረገ መሆኑን ሃላፊዋ አክለው ተናግረዋል፡፡ ፍርድ…
Read More
ኢትዮጵያ የትምባሆ አጫሾችን ቁጥር ለመቀነስ ከአፍሪካ ስኬታማዋ ሀገር መሆኗ ተገለጸ

ኢትዮጵያ የትምባሆ አጫሾችን ቁጥር ለመቀነስ ከአፍሪካ ስኬታማዋ ሀገር መሆኗ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከጠቅላላው ህዝብ ውስጥ አምስት በመቶ ያህሉ ሲጋራ አጫሾች እንደሆኑ አንድ ጥናት አመላከተ፡፡ በኢትዮጵያ ከ6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከአጫሾች በሚወጣ የትምባሆ ጭስ እንደሚቸገሩ ከዚህ በፊት የተደረገ ጥናት ያሳያል፡፡ ጥናቱ ኢትዮጵያ የሲጋራ አጫሾችን ቁጥር በመቀነስ ስኬታማ ከሆኑ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ እንደሆነችም ጠቁሟል፡፡ ኢትዮጵያ የሲጋራ አጫሾችን ቁጥር ለመቀነስ እና የዜጎችን ጤንነት ለመጠበቅ ጠንካራ የህግ ማዕቀፍ በየጊዜው ስታዘጋጅ ቆይታለች፡፡ ከእነዚህ መካከልም ትምባሆ መግዛት የሚችሉት እድሜያቸው ከ21 ዓመት በላይ የሆኑ፣ የመዝናኛ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ውስጥ ትምባሆ ማጨስ እንደማይቻል፣ ሰው በተሰበሰበባቸው ቦታው ትምባሆ ማጨስ እና መስጨስ መከልከሉ አስገዳጅ ህግ መደረጋቸው ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ህጻናትን ከትንባሆ ነጻ የማደረግ እንቅስቃሴ (Campaign for Tobacco Free Kids )…
Read More
አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ እንዲያነሳ ተጠየቀ

አውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ እንዲያነሳ ተጠየቀ

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ የመስጠት ሂደት ላይ ጊዜያዊ ገደቦች ማስቀመጡን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። ህብረቱ ውሳነውን ያሳለፈው የኢትዮጵያ መንግስት በአውሮፓ ህጋዊ መኖሪያ ያላገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተባባሪ አልሆነም በሚል የቪዛ ገደብ ጥያለሁ ብሏል፡፡ በህብረቱ አዲስ ውሳኔ መሰረትም ኢትዮጵያዊያን ከዚህ በፊት ወደ አውሮፓ ሀገራት በ15 ቀናት ውስጥ ለቪዛ ጥያቄቸው ምላሽ ያገኙ የነበረ ሲሆን በአዲሱ ውሳኔ መሰረት ይህንን ወደ 45 ቀናት ከፍ አድርጓል፡፡ ውሳኔው የአገልግሎት እና ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የያዙ የቪዛ አመልካች ኢትዮጵያዊያንንም እንደሚጨምር በወቅቱ ተገልጾ ነበር፡፡ በአውሮፓ ህብረት ዋና ከተማ ብራስልስ ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ የአውሮፓ ህብረት ውሳኔ የሚያበሳጭ ነው ብሏል፡፡ ኢምባሲው በመግለጫው…
Read More
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያዊያን በሚሰጠው ቪዛ ዙሪያ አዲስ ገደብ ጣለ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያዊያን በሚሰጠው ቪዛ ዙሪያ አዲስ ገደብ ጣለ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያዊያን የቪዛ መጠየቂያ ጊዜን ከ15 ቀናት ወደ 45 ቀናት ከፍ አድርጓል፡፡ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ የመስጠትን ሂደት ላይ ጊዜያው ገደቦችን ማስቀመጡን አስታውቋል። ህብረቱ በሳለፈው ውሳኔ የህብረቱ ለአባል ሃገራት ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ ሊያሟሉ ይገባቸዋል ያላቸውን መስፈርቶችም አስቀምጧል። በዚህም ኢትዮጵያውያን የአውሮፓ ሀገራት ቪዛን ለማግኘት አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ ይገደዳሉ ተብሏል። በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ከሁለት ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት አይችሉም ሲልም ከልክሏል። ለዲፕሎማቲክ እና ለአገልግሎት ፓስፖርቶች የቪዛ ክፍያን በተመለከተም ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛውን የቪዛ ክፍያ ለመክፈል ይገደዳሉ ብሏል ህብረቱ።…
Read More
የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ አስገኘ

የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ አስገኘ

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተጓዦችና የጭነት አገልግሎት ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። ማኅበሩ በየቀኑ ከ7 መቶ እስከ 1ሺህ ሰዎችን የማጓጓዝ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከ155 ሺህ በላይ ተጓዦችን እና 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ቶን የጭነት አገልግሎት በማጓጓዝ የዕቅዱን 98 በመቶ ማሳካት መቻሉን የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ከ13 እስከ 15 በመቶ የወጪና ገቢ ምርት የሚያጓጉዘውን ማኅበር ከፈረንጆቹ 2024 ጥር ወር ጀምሮ ኢትዮጵያ የማስተዳደር ኃላፊነት ወስዳ እየሰራች መሆኗን ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡ በባቡር ትራንስፖርት ምቹ ምኅዳር በመፍጠርም በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የገቢና ወጪ ምርት የማጓጓዝ አቅም የበለጠ ለማሳደግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር…
Read More
የአፍሪካ ህብረት በራያ እና አላማጣ የተከሰተው አዲስ ግጭት እንደሚያሳስበው ገለጸ

የአፍሪካ ህብረት በራያ እና አላማጣ የተከሰተው አዲስ ግጭት እንደሚያሳስበው ገለጸ

የአማራ እና የትግራይ ክልል የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱባቸው የራያ አላማጣ እና አካባቢዋ ግጭቶች መከሰታቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት በአወዛጋቢዎቹ ራያ አላማጣ፣ ዛታ እና ኦፎላ "በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል ያሉ ውጥረቶችን" በትኩረት እየተከታተሉት መሆኑን ገልጿል። በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በተደረሰው የፌደራል መንግስት እና የህወሓት የዘላቂ ሰላም ስምምነት፣ ሁለቱ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱባቸው "አወዛጋቢ ቦታዎች" በህገመንግስቱ መሰረት እልባት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ይጠቅሳል። ሊቀመንበሩ ሁለቱም ወገኖች ግጭት ከማባባስ እንዲታቀቡ እና የአካባቢውን ንጹሃን መፈናቀል እንዲያስቆሙ ጥሪ አቅርቧል። ከአፍሪካ ህብረት በተጨማሪም መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች በአማራ እና ትግራይ ከልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ያጋጠመው አዲስ ግጭት እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል፡፡ የካናዳ፣…
Read More
ኢትዮጵያ ከ18 ሺህ በላይ የውጭ ሀገራት ዜጎችን አባረረች

ኢትዮጵያ ከ18 ሺህ በላይ የውጭ ሀገራት ዜጎችን አባረረች

የተባረሩት የውጭ ሀገራት ዜጎች ህጋዊ የነዋሪነት ፈቃድ የሌላቸው እንደሆኑ የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡ የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡ ዳይሬክተሯ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በሐሰተኛ የመኖሪያ ፍቃድ በአገር ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ18 ሺህ በላይ የውጭ አገር ዜጎችን ከአገር እንዲባረሩ ተደርጓል፡፡ ከአገር ከተባረሩት የውጭ ሀገራት ዜጎች መካከል የተወሰኑት ሐሰተኛ የመኖሪያ ፍቃድ አዘጋጅተው በገንዘብ ሲሸጡ የነበሩ እንደሚገኙበት ተቋሙ አስታውቋል፡፡ በኢንቨስትመንት ፍቃድ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የውጭ ዜጎች ለበርካታ ዓመታት በሕገወጥ ሥራዎች ላይ ተሳታፊ ኾነው እንደተገኙም ዳይሬክተሯ በሪፖርታቸው ላይ ጠቅሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ከዚህ በፊት በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች ሀሰተኛ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ፣…
Read More
ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት እቅድ እንዳላት ገለጸች

ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት እቅድ እንዳላት ገለጸች

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ተናግረዋል። የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለእቅዱ መሳካትም ቢያንስ ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ካፍ ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ መስፈርቶችን በማስቀመጡ ኢትዮጵያ አንድም ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም እንዳይኖራት አድርጓል ሲሉም አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ የካፍን ደረጃ የሚመጥኑ ስታዲየሞች የሌላት በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዘም ላሉ ጊዜያት ከሀገሩ ዉጪ ለመጫወት ተገድዶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል። የዉድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ቢያንስ ስድስት ስታዲየሞችን እንዲያዘጋጁ ካፍ ቢያዝም ኢትዮጵያ እስካሁን የካፍን ደረጃ ያሟላ ስታዲየም የሌላት ሲሆን ውድድሩን ለማዘጋጀት እያደረገች ስላለው ዝግጅት የተባለ…
Read More
ከአላማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ50 ሺህ አለፈ

ከአላማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ50 ሺህ አለፈ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት 50 ሺህ ዜጎች ከራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡ እንደ ድርጅቱ ሪፖርት ከሆነ ከሰሞኑ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ባገረሸው ግጭት ምክንያት ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል ብሏል፡፡ ተፈናቃዮቹ በቆቦ፣ ወልደያ እና ሰቆጣ ከተሞች በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ እንደተጠለሉም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ተጨማሪ ዜጎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የገለጸው ድርጅቱ ለተፈናቃዮች ውሃ፣ ምግብ እና ሌሎች ህይወት ማቆያ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡ አሁን ላይ ከለጋሽ ተቋማት እና ሀገራት የሚገኘው ድጋፍ እየተሟጠጠ በመሆኑ በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ የሚችለውን ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ለተፈናቃዮቹ መጠለያ፣ የሕክምና አገልግሎት እና ሌሎች መሰረታዊ ድጋፎችን ማድረግ ይገባል…
Read More