01
May
በኢትዮጵያ ከጠቅላላው ህዝብ ውስጥ አምስት በመቶ ያህሉ ሲጋራ አጫሾች እንደሆኑ አንድ ጥናት አመላከተ፡፡ በኢትዮጵያ ከ6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ከአጫሾች በሚወጣ የትምባሆ ጭስ እንደሚቸገሩ ከዚህ በፊት የተደረገ ጥናት ያሳያል፡፡ ጥናቱ ኢትዮጵያ የሲጋራ አጫሾችን ቁጥር በመቀነስ ስኬታማ ከሆኑ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ እንደሆነችም ጠቁሟል፡፡ ኢትዮጵያ የሲጋራ አጫሾችን ቁጥር ለመቀነስ እና የዜጎችን ጤንነት ለመጠበቅ ጠንካራ የህግ ማዕቀፍ በየጊዜው ስታዘጋጅ ቆይታለች፡፡ ከእነዚህ መካከልም ትምባሆ መግዛት የሚችሉት እድሜያቸው ከ21 ዓመት በላይ የሆኑ፣ የመዝናኛ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ውስጥ ትምባሆ ማጨስ እንደማይቻል፣ ሰው በተሰበሰበባቸው ቦታው ትምባሆ ማጨስ እና መስጨስ መከልከሉ አስገዳጅ ህግ መደረጋቸው ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ህጻናትን ከትንባሆ ነጻ የማደረግ እንቅስቃሴ (Campaign for Tobacco Free Kids )…