Blog

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሀንስ አያሌው ከኃላፊነት ለቀቁ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሀንስ አያሌው ከኃላፊነት ለቀቁ

የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሀንስ አያሌው ስራቸውን የለቀቁት "በፈቃዳቸውና በግል ምክንያት" መሆኑን ተናግረዋል። በተጠባባቂነት የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳን ጌታቸው ዋቄ ሀለፊነቱን እንደተረከቡ ተገልጿል። ዮሀንስ አያሌው በስራ ዘመናቸው ባንኩ ከነበረበት ውስብስብ ችግርና ክስረት  ወደ ተሻለ አቋም እንዲመለስ ማስቻላቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች ይመስክሩላቸዋል። በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ጠለቅ ያለ እውቀት እንዳላቸው የሚነገርላቸው ዶክተር ዮሀንስ አያሌው ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክን በምክትል ገዥነት እና በዋና ኢኮኖሚስትነት አገልግለዋል። በዚህም በገንዘብ ኢኮኖሚስትነታቸው ብዙዎች የሚያደንቋቸው ሲሆን ከአምስት አመት በፊት የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በቦርድ አባልነት አገልግለዋል፡፡ የቀድሞው የልማት ባንኩ ፕሬዝዳንት ሀይለኢየሱስ በቀለ ሲለቁ የተኩት ዮሃንስ የባንኩ ፕሬዝዳንት በመሆን ለአራት አመታት የባንኩን ፖሊሲ  መርተዋል ሲል ዋዜማ ሬዲዮ ዘግቧል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ዶክተር…
Read More
ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ በኩል እስከ ጅቡቲ የሚዘልቅ የነዳጅ መስመር ልገነባ ነው አለች

ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ በኩል እስከ ጅቡቲ የሚዘልቅ የነዳጅ መስመር ልገነባ ነው አለች

የተትረፈረፈ የነዳጅ ሀብት ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ደቡብ ሱዳን ከዚህ በፊት ነዳጇን በሱዳን በኩል አድርጋ ለዓለም ገበያ ስታቀርብ ቆይታለች፡፡ ሱዳን በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ መሆኗን ተከትሎ እስከ ፖርት ሱዳን የተዘረጋው የደቡብ ሱዳን ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር በጦርነቱ ወድሞባታል፡፡ በዚህም ምክንያት ሀገሪቱ በኢትዮጵያ በኩል እስከ ጅቡቲ ወደብ ድረስ የተዘረጋ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመገንባት ማቀዷ ተገልጿል፡፡ በቻይና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ሲሳተፉ የነበሩት ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በኢትዮጵያ በኩል እስከ ጅቡቲ ወደብ ድረስ የሚዘረጋ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ግንባታ ዙሪያ መክረዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ከቻይና ብሔራዊ ነዳጅ ኮርፖሬሽን ሃላፊ ዳይ ሁሊያንግ ጋር በቤጂንግ መምከራቸውን የደቡብ ሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡ እንደ ዘገባው ከሆነ የቻይናው ነዳጅ ኮርፖሬሽን…
Read More
ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና የዲጂታል ጉብኝት እያደረጉ ነው

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና የዲጂታል ጉብኝት እያደረጉ ነው

ሶስት ኢትዮጵያውያን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሁዋዌ አዘጋጅነት ለስምንት ቀናት በሚቆይ የዲጂታል ጉብኝት እየተሳተፉ ሲሆን ጉብኝቱ በቻይና ሼንዘን ተጀምሮ ቤጂንግ ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል። ለተመረጡ የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ “Huawei Seeds for the Future (SFTF) Tech 4 Good” ያለፈው ዓመት ሰልጣኞች የተዘጋጀው ጉብኝቱ ነሐሴ 26 ተጀምሮ እስከ ጳጉሜ 3, 2016 ዓ.ም ድረስ ይቀጥላል። ጉብኝቱ ለተማሪዎች የቻይናን ዲጂታል መልከዓ ምድር ለመቃኘት፣ የአይሲቲ ክህሎት እና የቴክኖሎጂ ጅምሮችን ለማዳበር፣ እንዲሁም ተማሪዎቹ ስለሚሰሯቸው ስራዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ከኢንዱስትሪ ኃላፊዎች ጋርም ውይይት እንዲያደርጉ ልዩ እድል ይሰጣል። ተማሪዎች በዚህ ስልጠና እንዲሳተፉ ለማድረግ የማጣራት ሂደትን ያለፉ ሲሆን ከ2023 የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ፕሮግራም ተሳታፊዎች…
Read More
ኢትዮጵያ በሶማሊያ በኩል ጦሯን ዝግጁ ማድረጓን ገለጸች

ኢትዮጵያ በሶማሊያ በኩል ጦሯን ዝግጁ ማድረጓን ገለጸች

የኢትዮጵያ አየር ሀይል ከሶማሊያ ጋር የምትዋሰንበት ምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ አስታውቋል ከሰሞኑ ግብፅ እና ሶማልያ በቀጠናው እያረጉት ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር ሀይል የምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ ገልጿል። በኢትዮጵያ አየር ሃይል የ3ኛው አየር ምድብ የተሰጠውን ሃገራዊ ግዳጅና ተልዕኮ ለመወጣት በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የአየር ምድቡ አዛዥ ኮሎኔል ደረጀ ቡሽሬ ገልፀዋል፡፡ አዛዡ የ3ኛው አየር ምድብ የሃገራችንን ብሎም የምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ የሚገኝ የሃገር መከታና መመኪያ የሆነ ምድብ ነው ያሉ ሲሆን "ወደፊትም ኢትዮጵያን ከውስጥም ይሁን ከውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ለመጠበቅ በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል" ብለዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር የምስራቅ ዕዝ በተሟላ…
Read More
በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ተጠያቂነት እንዲሰፍን ተጠየቀ

በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ተጠያቂነት እንዲሰፍን ተጠየቀ

በሁለት አመቱ የትግራይ ጦርነት የተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ጥሪ አቀረበ። የያለፈው ጦርነት እና ጥፋት ተጠያቂነት ባለመረጋገጡ በጦርነቱ ተሳታፊ የነበሩ ሐይሎች ለሌላ ጥፋት እየተዘጋጁ ነው በማለት አረና ከሷል። በወቅታዊ የትግራይ ፖለቲካዊ ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዮች ዙርያ መግለጫ የሰጠው በትግራይ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ህወሓት ውስጥ የተፈጠረው መከፋፈል ለትግራይ አደጋ ይዞ የሚመጣ እና ሐላፊነት የጎደለው አካሄድ እየተከተለ ያለ ሲል ገልፆታል። የዓረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ "አሁንም ወደ ጦርነት የሚወስዱ መንገዶች እየታዩ ያሉት እና የጦርነት ነጋሪት የሚጎሰመው ባለፈው 2 ዓመት ለነበረው ጦርነት ከሁሉም ወገን ተጠያቂነት ባለመረጋገጡ ነው፤ ከህወሓት ይሁን ከሻዕብያ እንዲሁም ብልፅግና ወገን የጦርነቱ…
Read More
በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የዜጎች እገታ መባባሱን ኢሰመኮ ገለጸ

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የዜጎች እገታ መባባሱን ኢሰመኮ ገለጸ

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በተራዘሙ ግጭቶች ምክንያት የሚፈጸሙ እገታዎች ተባብሰው መቀጠላቸውን  የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል። በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ከተራዘሙ የትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረው የሕግ ማስከበር እና የመንግሥት መዋቅር መላላት ሳቢያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ እገታዎች መባባሳቸውን ብሏል ኢሰመኮ፡፡ ኢሰመኮ አደረኩት ባለው ማጣራት ለዘረፋ "በተደራጁ ቡድኖች እንዲሁም በአንዳንድ የመንግሥት የጸጥታ አካላት አባሎች" እገታዎች እንደሚፈጸሙ ደርሸበታለሁ ብሏል፡፡  አጋቾች ሰላማዊ ሰዎችን በአብዛኛው በጉዞ (ትራንስፖርት) ላይ እያሉ አንዳንዴም ከመኖሪያ ቤታቸው ወይም ከሥራ ቦታቸው አግተው ወዳልታወቀ ቦታ በመውሰድ ከፍተኛ የማስለቀቂያ ገንዘብ ክፍያ እንደሚጠይቁ ፤ ገንዘብ መክፈል ያልቻሉ በርካታ ታጋቾች ግድያን ጨምሮ በርካታ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተፈጸሙ እንደሚገኙ በሪፖርቱ…
Read More
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ መብረር አቆመ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ መብረር አቆመ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው መግለጫ ከነገ ነሀሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንደሚያቆም አስታውቋል፡፡ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ እና ከአስመራ ወደ አዲ አበባ የሚደረጉ በረራዎችን አቋርጫለሁ ያለው አየር መንገዱ በኤርትራ ያለው አሰራር አስቸጋሪ እና ከቁጥጥሩ ውጪ መሆኑ ለበረራው መቋረጥ በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡ ጉዞ ለማድረግ ቲኬት የገዙ መንገደኞችም በመረጡት አየር መንገዶች እንዲበሩ እንደሚያደርግ እና የዋጋ ጭማሪ እንደማያደርግም አየር መንገዱ ገልጿል፡፡ ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ከመስከረም 30 በኋላ ወደ አስመራ እንዳይበር መከልከሏ ይታወሳል፡፡ የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ከአንድ ወር በፊት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በሚጓዙ ተጋዦች ላይ “የተደራጀ እና ስልታዊ የሻንጣ ስርቆት፣ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ፣…
Read More
ኢትዮጵያ በዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር አራት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

ኢትዮጵያ በዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር አራት የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

በደቡብ አሜሪካዋ ፔሩ ሊማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ትናንት ጠናቋል፡፡ በዚህ የአትሌቲክ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች፡፡ ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ብሔራዊ ቡድን በ6 ወርቅ፣ 2 ብር እና 2 ነሐስ በአጠቃላይ 10 ሜዳሊያዎችን ማሸነፍ ችሏል። በዚህ ኢትዮጵያ ከዓለም አሜሪካን በመከተል 2ኛ እንዲሁም ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ያጠናቀቀች ሲሆን፤ ውድድሩን 1ኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቀች አሜሪካ በ8 ወርቅ፣ 4 ብር እና 4 ነሃስ በድምሩ 16 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶች በአትሌት መዲና ኢሳ በ5000 ሜትር፣ በአትሌት ሲምቦ አለማየሁ በ3000 ሜትር መሰናክል በአትሌት ጀነራል ብርሃኑ በ800 ሜትር፣ በአትሌት…
Read More
ግብጽ በድጋሚ ኢትዮጵያን በጸጥታው ምክር ቤት ላይ ከሰሰች

ግብጽ በድጋሚ ኢትዮጵያን በጸጥታው ምክር ቤት ላይ ከሰሰች

በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ተቃውሞ አለኝ የምትለው ግብጽ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ላይ ከሳለች፡፡ ግብጽ በዛሬው ዕለት ለጸጽታው ምክር ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸችው ኢትዮጵያ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ላይ ለአምስተኛ ዓመት ውሃ ሙሌት አከናውናለች ይላል፡፡ በግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ስደተኞች እና ግብጻዊያን አርበኞች እንደተጻፈ የተገለጸው ይህ ደብዳቤ ኢትዮጵያ የግብጻዊያንን ጥቅም በሚጻረር መልኩ የውሃ ሙሌት እያካሄደች ነው ብሏል፡፡ በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደል አቲ የተፈረመው ይህ የተመድ ደብዳቤ ኢትዮጵያ፣ግብጽ እና ሱዳን በፈረንጆቹ 2015 ላይ የተፈራረሙትን ስምምነት በመጣስ የግድቡ ውሃ ሙሌት በተናጠል ተከናውኗል፣ ይህም የታችኛው ተፋሰስ ሀገራትን ጥቅም የሚጎዳ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የግድቡን…
Read More
ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ “የእልል ያልኩ ሐበሻ” የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ

ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ “የእልል ያልኩ ሐበሻ” የብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ

ወጣቱ ድምፂዊ የሀበሻን ባህላዊ እሴቶችን እንዲሁም ሐበሻ ቢራን እንዲያስተዋውቅ የተመረጠው በሐበሻ ቢራ ፉብሪካ  ነው። በአንድ አልበም እና በተለያዮ ነጠላ ዜማዎች  ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው  ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ በመመረጡ የሀበሻ መገለጫ የሆኑ እሴቶች በዓለም አደባባይ ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል። "እልል ያልኩ ሀበሻ " በሐበሻ ቢራ አዘጋጅነት የደመቀ ዝግጅት ተካሄዷል። በቃና ዌርሀውስ በተዘጋጀው በአይነቱ ለየት ያለ ፐሮግራም  የኢትዮያዊያን ባሀል፤ ዕሴት፤ማንነት እና ወግ በተለያዩ ክዋኔዎች ባህላዊውን ከዘመነኛው ጋር ያሰናሰኑ ዝግጅቶች ቀርበዋል። በዚህም በምግብ አዘገጃጀት፤በፋሽን ትርዒት፤ በሙዚቃ እና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ባሀላዊው ከዘመናዊ ጋር በማሠናሠል ስራ የበረቱ  ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል። የዝግጅቱ ዓላማም የሀበሻ መገለጫ የሆኑ አለባበሰ፣ምግብ ዝግጅት ፣ሙዚቃ እና የመሳሰሉትን በተለያዩ ሀገረኛ መድረኮች…
Read More