tayeatskeselassie

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

ላለፉት ዘጠኝ ወራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ የኢትዮጵያ ስድስተኛው ፕሬዝዳንት ሆነዋል 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ ሁለቱ ምር ቤቶች በጋራ ባካሄዱት የመክፈቻ ስነ ስርዓትም አምባሳደር ታዬ አስጸቀስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል። የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል። አምባሳደር ፕሬዚዳንት ታዬም በምክር ቤቶቹ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን ከቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ሣለወርቅ ዘውዴ ጋር ሥራ እርክክብ አድርገዋል፡፡ አምባሳደር ታዬ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ መምሪያ የሥራ ክፍል ፣የምዕራብ አውሮፓ ዋና ክፍል ኃላፊ፣የኢንፎርሜሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር፣ስቶክሆልም የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት፣በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት እንዲሁም…
Read More