06
Aug
መንግስት 550 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አዘጋጅቷል ከሁለት ወር በፊት 970 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት አጽድቆ የነበረው የፌደራል መንግስት ግማሽ ትሪሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንዳሉት የፌደራል መንግሥት 551 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ ተናግረዋል። መንገስት ካቀረበው 550 ቢሊዮን ብር ውስጥ 240 ቢሊዮን ብሩ "ለማኅበራዊ ድጋፍ " የሚውል ነው የተባለ ሲሆን ቀሪው ደግሞ ለማህበራዊ ድጋፍ፣ ለምግብ ዋስትና፣ ለሰራተኛ ደመወዝ ጭማሪ፣ ለመድሃኒት ድጎማ፣ ለለነዳጅ ድጎማ እና ሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦች ድጎማ እንደሚውል ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ የፌደራል መንግስት የበጀት ማስተካከያ ያደረገው ከዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍ የገንዘብ ድጋፍ በብድር እና እርዳታ ማግኘቱን ተከትሎ ነው፡፡…