04
Oct
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሠሪ ፌዴሬሽን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመዋል፡፡ ስምምነቱ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሠሪ ፌዴሬሽን በውጭ ሀገር በሥራ የሚሰማሩ ዜጎችን መብት እና ደህንነት ለማስጠበቅ ያለመ ነው፡፡ በስምምነቱ ወቅት የፌዴሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ፣የዓለም ሥራ ድርጅት ተወካይ እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ በፊርማው ሥነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ኮንፌዴሬሽኑ በሀገር ውስጥ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች መብቶች እንዲከበሩ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡ ከሀገር ውስጥ በተጨማሪም በውጭ ሀገራት ተቀጥረው የሚሠሩ ኢትዮጵያዊን መብታቸው ተጠብቆ እዲሠሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ…