03
Apr
ኢትዮጵያ ለካንሰር ህመምተኞችን ለማከም የሚውሉ መድኃኒቶችን ሙሉ በሙሉ ከውጪ በማስገባት ላይ ትገኛለች። ይሁንና እነዚህን መድኃኒቶች በሀገር ውስጥ ለማምረት የአዋጭነት ጥናት በማድረግ ላይ መሆኑ ተገልጿል። ባለሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች የካንሰር መድኃኒቶችን በሀገር ውስጥ እንዲያመርቱ የሚያስችል ፕሮጀክት በቂልንጦ ፋርማሲዩቲካል ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ገብተው በፕሮጀክት ደረጃ ይዘው ስራ መጀመራቸው ተገልጿል። በቅርብ ጊዜ እነዚህን ፕሮጀክቶች በመደገፍ የፕሮጀክት ጊዜያቸውን አጠናቀው ወደ ምርት እንዲገቡ የአርማሆር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ድጋፍ እንደሚያደርግ በአርማሆር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር መሳይ ወ/ማርያም ተናግረዋል። መድኃኒቶች በሀገር ውስጥ መመረት ከመጀመሩ በፊት በሀገር ውስጥ ቢመረቱ ነው ወይስ ከውጪ ቢገቡ የተሻለ የሚሆነው የሚለውን ጥናት ያማከለ እንደሚሆንም ተመራማሪው አክለዋል። ይሁንና በሀገር ውስጥ መመረት ሲጀምሩ ከውጪ የሚገቡትን…