18
Apr
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ጉዳይ፣ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ስለተደረገው የወደብ መግባቢያ ስምምነት እና ሌሎቹም ተጠቃሽ ናቸው። አቶ ነብዩ እንዳሉት የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ጉዳይ በድንበር አካባቢ ያሉ ማህበረሰብ ክፍሎችን ባሳተፈ መንገድ በሁለቱ ሀገራት በሚዋቀር ኮሚቴ ይፈታል ብለዋል። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር ሊቀየር በማይችል ኹኔታ ለመጨረሻ ጊዜ ተሠምሯል ማለቱ አይዘነጋም። የኤርትራ ጦር በርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎችን እንደተቆጣጠር እና አካባቢዎቹን ወደ ኤርትራ ማካለሉን እንዴት ኢትዮጵያ እንዴት ታየዋለች? በሚል ለቃል አቀባዩ ለቀረበላቸው ጥያቄም "ጥያቄው…