15
Jan
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከሶስት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል። ስምምነቱ ኢትዮጵያ በኤደን ባህረ ሰላጤ 20 ኪሎሜትሮች የሚረዝም የባህር ጠረፍ እንድትከራይ እና በምትኩ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና እንድትሰጥ የሚያስችል ነው። ይህ ስምምነት ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ በምታያት ሶማሊያ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። ይህን ተከትሎም የአረብ ሊግ እና ግብጽን ጨምሮ በርካታ ሀገራት እና ተቋማት የሱማሊያ ሉዓላዊነትን እንደሚያከብሩ ስምምነቱን እንደማይደግፉት ተናግረዋል። የአረብ ሊግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የሊጉ አባል ሀገራት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጉዳይ እንደሚመክር አስታውቋል፡፡ በበይነ መረብ እንደሚካሄድ የተገለጸው ይህ የሚኒስትሮች አስቸኳይ ስብሰባ የፊታችን ረቡዕ እንደሚካሄድ የሊጉ…