Somaliland

ኢትዮጵያ ሶማሊያ ቀጠናውን ለማተራመስ ከውጭ ሃይሎች ጋር እየተባበረች ነው ስትል ከሰሰች

ኢትዮጵያ ሶማሊያ ቀጠናውን ለማተራመስ ከውጭ ሃይሎች ጋር እየተባበረች ነው ስትል ከሰሰች

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሶማሊያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አሳሳቢ ነው ብሏል። ሚኒስቴሩ መግለጫውን ያወጣው ግብጽ ከሶስት አስርት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሶማሊያ የጦር መሳሪያ መላኳ ከተነገረ በኋላ ነው። ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት ከሶማሊያ ጋር ግንኙነቷ ሲሻክር፥ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ቅራኔ ውስጥ ያለችው ግብጽ ለሶማሊያ ድጋፏን አሳይታለች። ግብጽ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከሞቃዲሾ ጋር የወታደራዊ ደህንነት ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን በሶማሊያ ለሚሰማራው አዲስ የሰላም አስከባሪ ተልእኮ ወታደሮች ለመላክ ፈቃደኝነቷን መግለጿም ይታወሳል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ግብጽን በስም ባይጠቅስም በሶማሊያ የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ (አትሚስ) ሽግግር ሂደት ሳይጠናቀቅ በሞቃዲሾ አዲስ የሰላም አስከባሪ ተልዕኮ…
Read More
የግብፅ ወታደሮች ሶማሊያ መግባታቸው ተገለጸ

የግብፅ ወታደሮች ሶማሊያ መግባታቸው ተገለጸ

የግብፅ ወታደሮች፣ መሳሪያዎችና ወታደራዊ አውሮፕላኖችን የያዘ አውሮፕላን ወደ ሶማሊያ መጓዛቸውን የሚያሳይ ምስሎች ወጥተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ከዘጠኝ ወር በፊት በአዲስ አበባ የወደብ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ስምምነትን ተከትሎ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው የተበላሸ ሲሆን ሶማሊያ ከግብጽ እና ቱርክ ጋር ወታደራዊ ስምምነቶችን አድርጋለች፡፡ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በአፍሪካ ትልቁን ግድብ ግንባታ መጀመሯን ተከትሎ የውሃ ድርሻዬ ነካል በሚል ቅሬታ ያላት ግብጽ ይህንን እድል በመጠቀም ከሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ስምምነቶችን እያደረገች ነው፡፡ ይህን ተከትሎም ግብጽ ከሶማሊያ ጋር ባደረገቻቸው ወታደራዊ ስምምነቶች አማካኝነት በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ሞቃዲሾ ልካለች፡፡ ን የተፈራረምክንያት ይህ ሂደት 10 ሺህ የሚደርሱ የግብፅ ወታደሮችን በሶማሊያ ለማሰማራት የታቀደው…
Read More
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ብሔራዊ ጥቅሟል ለማስጠበቅ ማንኛውንም እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ገለጸች

ኢትዮጵያ በሶማሊያ ብሔራዊ ጥቅሟል ለማስጠበቅ ማንኛውንም እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል ገለጸች

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ወቅት ከጋዜጠኞች ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል የግብጽ እና ሶማሊያ ወታደራዊ ስምምነቶች በኢትዮጵያ ላይ ምን አይነት አንድምታ ይኖረዋል? የሚለው ዋነኛው ነበር። እንዲሁም የሶማሊያን ጸጥታ እና ደህንነት ለማስጠበቅ በሚል በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የተሰማራው ሰላም አስከባሪ ጦር (አትሚስ) ተልዕኮ የፊታችን ታህሳስ ያልቃል። የሶማሊያ ጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት አሁንም የሚፈለገውን አቅም አለመገንባታቸውን ተከትሎ አትሚስን ተክቶ እንደ አዲስ በሚዋቀረው ሰላም አስከባሪ ስር ግብጽ ጦር ለማዋጣት ፍላጎት ማሳየቷ እና የሶማሊያ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጦር በአዲሱ ተልዕኮ ስር እንዳይካተት መፈለጋቸውስ በኢትዮጵያ ላይ ምን አይነት አስተዋጽኦ ይኖረዋል? የሚለው ጥያቄም ለአምባሳደር ነብዩ ተነስቶላቸዋል።…
Read More
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁለተኛውን ዙር ድርድር በአንካራ ጀመሩ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁለተኛውን ዙር ድርድር በአንካራ ጀመሩ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከወደብ ጋር በተያያዘ በመካከላቸው የተፈጠረዉን ዉጥረት ለመፍታት ሁለተኛ ዙር ድርድራቸውን በአንካራ ጀምረዋል፡፡ የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶሃን በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ንትርክ ዙሪያ ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ጋር በስልክ መምከራቸውም ተሰምቷል፡፡ የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶሃን ከሶማሊያ አቻቸዉ ሀሰን ሼክ ማህሙድ ጋር በስልክ መምከራቸዉ ተዘግቧል። በቱርክ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ትብብር አስፈላጊነት በማጉላት አንካራ ፥ በሞቃዲሾ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ጥረቷን እንደምትቀጥል የቱርክ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በኤክስ ገጹ ላይ ጽፏል። በዛሬዉ እለት በቱርኪዬ ርዕሰ መዲና አንካራ ከሚካሄደው ሁለተኛ ዙር የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ ድርድር ውጥረቱን ለማርገብ ተጨባጭ ውጤት ይጠበቃል ብሏል። መሪዎቹ በስልክ ዉይይታቸዊ በሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በአህጉራዊ እና…
Read More
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት “ኢትዮጵያ ለዲፕሎማሲ ዝግጁ አይደለችም” ሲሉ ከሰሱ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት “ኢትዮጵያ ለዲፕሎማሲ ዝግጁ አይደለችም” ሲሉ ከሰሱ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሰሞኑ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ከመነጋገር ይልቅ ወደ ሌሎች ሀገራት ሽምግልና ይልካሉ ሲሉ መክሰሳቸው ይታወሳል፡፡ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ የገቡበትን ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት በንግግር ለመፍታት ኢትዮጵያ ዝግጁ አይደለችም ሲሉ ተናገሩ። የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ቅዳሜ ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም በአገሪቱ ምክር ቤት የመክፈቻ ንግግራቸው ላይ መንግሥታቸው ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቱን ለማርገብ ፍላጎት ቢኖረውም፤ ኢትዮጵያ ግን ለውይይት ዝግጁ አይደለችም ብለዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጥቂት ቀናት በፊት “የሶማሊያ መንግሥት እኛን ከማናገር፣ በየሰፈሩ እየዞረ እኛን መክሰስ መርጧል” ብለው ከተናገሩ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሳለፍነው ሳምንት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር…
Read More
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከወደብ ስምምነት ውጪ በሌሎች ጉዳዮችም እየተደራደሩ መሆኑን ገለጹ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከወደብ ስምምነት ውጪ በሌሎች ጉዳዮችም እየተደራደሩ መሆኑን ገለጹ

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ላይ ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጉዳይ ዋነኛው ነው። በቱርክ አደራዳሪነት በአንካራ የተጀመረው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ድርድር ሁለተኛው ዙር የፊታችን ነሀሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ይቀጥላል የተባለ ሲሆን ይህ ድርድር ምን ያህል ከውጭ ጣልቃ ገብነት የተጠበቀ ነው?  የሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ተከታዩን ብለዋል። "ኢትዮጵያ በታሪኳ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ስትደራደር ቆይታለች፣ አንድም ጊዜ በውጭ ጣልቃ ገብነቶች ጥቅሟን አሳልፋ ሰጥታ አታውቅም" ብለዋል። "በአንካራ እየተካሄደ ያለው የሁለትዮሽ ድርድርም ብሔራዊ ጥቅማችንን ባስጠበቀ መንገድ ይቀጥላል" ያሉት አምባሳደር ነብዩ በድርድሩ ላይ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደሌለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ…
Read More
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ድርድር ጀመሩ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ድርድር ጀመሩ

ቱርክ ግንኙነታቸው የሻከረውን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ማደራደር መጀመሯ ተገልጿል። ሬውተርስ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳስነበበው ድርድሩ በቱርክ መዲና አንካራ በመካሄድ ለይ ይገኛል። ይሁን እንጂ አደራዳሪዋ ቱርክም ሆነች ተደራዳሪዎቹ እስካሁን ማረጋገጫ አልሰጡም። የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሙአሊም ፊቂ የመሩት ልኡክ በትናንትናው እለት ወደ ቱርክ ማቅናቱን ቢዘግቡም የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማረጋገጫ አልሰጠም። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣንም በአንካራ ተጀምሯል ስለተባለው ድርድር ምንም መናገር አንፈልግም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሊላንድ መንግስት ቃል አቀባይ በበኩላቸው በድርድሩ ላይ እየተሳተፉ እንዳልሆነ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በጥር ወር ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር በደረሰችው የወደብ ስምምነት ምክንያት የአዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ ግንኙነት መሻከሩ ይታወቃል።…
Read More
በርበራ ወደብ በዓለም ባንክ የጥራት መመዘኛ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተመረጠ

በርበራ ወደብ በዓለም ባንክ የጥራት መመዘኛ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተመረጠ

የዓለም ባንክ በመላው ዓለም ያሉ ወደቦች እቃ የመጫን አቅማቸውን የተመለከተ አሁናዊ ያሉበትን ሁኔታ አስመልክቶ ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የእቃ ጫኝ ኮንቴይነር የመያዝ አቅማቸውን መሰረት በማድረግ የወደቦችን ደረጃ ያወጣው ባንኩ ኢትዮጵያ የባህር ሀይሏን ልታቋቁምበት ያሰበችበት በርበራ የተሻለ ደረጃን አግኝቷል፡፡ በባንኩ ሪፖርት መሰረት የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ንብረት የሆነው በርበራ ወደብ ከሰሃራ በረሃ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ የመጀመሪያው ወደብ ተብሏል፡፡ በርበራ ወደብ በዓለም ካሉ ወደቦች በ103ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ከሰሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ደግሞ ቀዳሚው ሆኗል፡፡ ሞቃዲሾ ወደብ ከበርበራ ወደብ በመቀጠል በሁለተኝነት ሲጠቀስ የጊኒው ኮናክሪ በሶስተኝነት ሲቀመጥ  የኢኳቶሪያል ጊኒው ማለቡ ወደብ ደግሞ በአራተኝነት ተቀምጧል፡፡ ከመላው ዓለም ደግሞ የቻይናው ያንግሻህ ወደብ በአንደኝነት ሲቀመጥ…
Read More
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ያለው ሰላም አስከባሪ ጦሯን ልታስወጣ ነው

ኢትዮጵያ በሶማሊያ ያለው ሰላም አስከባሪ ጦሯን ልታስወጣ ነው

በሶማሊያ የሰፈረው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በቀጣይ ታህሳስ ወር ሀገሪቱን ለቆ ይወጣል ብሎ እንደሚጠብቅ ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ሰላም አስከባሪ ጦር ወደ ሶማሊ ከላኩ ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡ ከኢትዮጵያ በተጨማሪም ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ቡሩንዲ ጦራቸውን ወደ ሶማሊያ የላኩ ሀገራት ናቸው፡፡ ሶማሊያ በሀገሯ በሰላም ማስከበር ተልእኮ ላይ የሚገኙ ሁሉም የኢትዮጵያ ወታደሮች በመጪው ታህሳስ ወር ላይ ሙሉ ለሙሉ ጠቅልለው ይወጣሉ ብላ እንደምትጠብቅ አስታውቃለች። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሁሴን ሼክ አሊ ለቪኦኤ እንዳሉት የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (ATMIS) በቀጣይ አመት ታህሳስ ወር ተልዕኮው ካበቃ በኋላ “የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ሃይል አባል አይሆኑም” ብሏል። የፕሬዚዳንቱ የደህንነት አማካሪው አክለውም…
Read More
ኢትዮጵያ በሀርጌሳ ያለው የቆንስላ ጽህፈት ቤቷን ወደ ኤምባሲ አሳደገች

ኢትዮጵያ በሀርጌሳ ያለው የቆንስላ ጽህፈት ቤቷን ወደ ኤምባሲ አሳደገች

ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ፣ ሃርጌሳ የሚገኘውን የቆንስላ ጽህፈት ቤቷን ሙሉ አገልግሎት ወደሚሰጥ ኤምባሲ ማሳደጓን የሶማሊላንድ ሚኒስትር ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከአራት ወራት በፊት በወደብ ጉዳይ በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት እንድትሆን ሶማሊላንድ ደግሞ የሀገርነት እውቅና እንድታገኝ የሚያደርግ በመሆኑ ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ በምታያት ሶማሊያ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣንና እና ተቃውሞን አስከትሏል። ከአንድ ወር በፊት ሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደርን በ72 ሰዓት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ እና በሀርጌሳ እና ጋሮዌ ያሉ የቆንሱላ ጽህፈት ቤቶች እንዲዘጉ ሰራተኞቹም በሁለት ሳምንት ውስጥ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ መወሰኗን አስታውቃ ነበር፡፡ በወቅቱም ራስ ገዟ ሶማላንድ…
Read More