Somaliland

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ወደብ በሊዝ መግዛቷን ገለጸች

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ወደብ በሊዝ መግዛቷን ገለጸች

በቀይ ባህር ላይ ወደብ እንደሚያስፈልጋት ስትገልጽ የቆየችው ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ወደብ በሊዝ መግዛቷን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ እንደ ጽህፈት ቤቱ መግለጫ ከሆነ የባህር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሌ ላንድ ጋር ተፈራርማለች፡፡ የባህር በር ሊዝ ስምምነቱን ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሌ ላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እንደተፈራረሙ ተገልጿል። የኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ስምምነት ኢትዮጵያ የቀይ ባህር በር እንዲኖራት ለያዘችው ጥረት ጥሩ መደላደል ሊፈጥር ይችላልም ተብሏል፡፡ ይሁንና የባህር በር ሊዝ ስምምነቱ ለምን ያህል ጊዜ፣ በምን ያህል ገንዘብ እና የስምምነቱ ዝርዝር መረጃ እስካሁን በማንኛውም ወገን ይፋ አልተደረገም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከወራት በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት…
Read More
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች

ሶማሊላንድ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች ድንበር አልፈው በሶሎ ግዛት ላስአኖድ ከተማ ጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ነው ስትል ክስ አቅርባ ነበር። በፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የሚመራው የሶማሌላንድ ካቢኔ ባወጣው መግለጫ ግጭት ባለባት ላስአኖድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ኃይሎች በተጨማሪ የሶማሊያ እና የፑንትላንድ ወታደሮች ይገኛሉ ብሏል፡፡ ካቢኔው የሶማሌ ላንድን ዓለም አቀፋዊ ድንበር አልፈው ገብተዋል ያላቸው እነዚህ ኃይሎች ከአካባቢው እንዲወጡም አሳስቧል።  ለሶማሊላንድ ክስ ምላሽ የሰጠው የሶማሌ ክልል መንግስት በላሳኖድ ከተማ በሚካሄደው ጦርነት አንድም የሶማሌ ክልል ኃይል አባል የለም ያለ ሲሆን፣ መግለጫውንም ኃላፊነት የጎደለው ውንጀላ እንደሆነ ገልጿል፡፡ በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዐብዱልቃድር ረሺድ ‹‹እኛ የሌላ ሀገር ፖለቲካ ውስጥ እጅ…
Read More