09
Mar
ቱርክ ከሶማሊያ ጋር በውቅያኖስ ውስጥ ጋዝ እና ነዳጅ ለማልማት በትናንትናው እለት ስምምነት ማድረጓን የቱርክ የኢነርጂ ሚኒስትር ተናግረዋል። ይህ ስምምነት ሁለቱ ሀገራት ባለፈው ወር ከተፈራረሙት ወታደራዊ ስምምነት የቀጠለ እና የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር ነው ተብሏል። ስምምነቱ በሁለቱ መንግስታት መካከል የተፈረመ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ በሶማሊያ መሬት እና ውሃማ አካላት ውስጥ ነዳጅ መፈለግን እና ማምረትን የሚያካትት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። በስምምነቱ መሰረት የሶማሊያ ሀብት ለሶማሊያውያን ለማዋል እና በአፍሪካ ቀንድ የቱርክን ተጽዕኖ ከፍ ለማድረግ አላማ እንዳላቸው ሚኒስትሩ አልፓርስላን ባይራክታር ገልጸዋል። በሌላ በኩል የሶማሊያ ድንበር በሙሉ ለቱርክ መሸጡ ያስቆጣቸው ሶማሊያዊያን በሞቃዲሾ የተቃውሞ ሰልፍ መውጣታቸውን የሶማሊያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ከሁለት ወር በፊት…