03
Nov
ህወሀት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝን ማጥቃቱን ተከትሎ ነበር በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተቀሰቀሰው። ለሁለት ዓመት የዘለቀው ይህ ጦርነት 800 ሺህ ገደማ ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን እንዲያጡ ሲያደርግ 26 ቢሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ኪሳራም አድርሷል። ለዚህ ጦርነት መቆም ምክንያት የሆነው የሰላም ስምምነት ከአንድ ዓመት በፊት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተፈርሟል። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ስለ ስምምነቱ እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በፌደራል መንግሥት እና ትግራይ ሀይሎች መካከል የተካሄደው የሰላም ስምምነት ለኢትዮጵያ ምን ጥቅም አስገኘ? በሚል ከጋዜጠኞች ጥያቄ ለቃል አቀባዩ ተነስቶላቸዋል። አምባሳደር መለስ በምላሻቸውም " ስምምነቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል ጦርነት እንዲቆም ከማድረግ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ላይ…