04
May
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ ማስፋፊያ አደርጋለሁ አለ፡፡ ኢትዮጵያ ለውጭ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ በሯን መክፈቷን ተከትሎ ነበር ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ወደ አዲስ አበባ የመጣው፡፡ ድርጅቱ ዓለም አቀፍ አጋርነት ለኢትዮጵያ በሚል ሰኔ ወር 2013 ዓ.ም ላይ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ህጋዊ ፍቃድ ከተቀበለ ከአንድ ዓመት በኋላ ስራ ጀምሯል፡፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለአል ዐይን እንዳስታወቀው በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለኔትወርክ ማስፋፊያ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር መድቤያለሁ ብሏል፡፡ ተቋሙ አክሎም በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎችበተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ 5 ሺህ አዳዲስ የኔትወርክ ማማዎችን እንደሚተክልም አስታውቋል፡፡ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተደረገ የሁለትዮሽ ስምምነት የኔትወርክ አገልግሎቱን ለደንበኞቹ እየሰጠ መሆኑን ያሳወቀው ሳፋሪ ኮም ቀስ በቀስ የራሱን የኔትወርክ…