መነሻ ገፅ

ጌዲዮን ጥሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ

ጌዲዮን ጥሞቲዮስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለተለያዩ ተቋማት አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾመዋል። በዚህም መሰረት ጌዲዮን ጥሞቲዮስ (ዶ/ር) በቅርቡ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ተደርገው በተሾሙት ታዬ አጽቀስላሴ ምትክ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት በተጨማሪም ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የፍትህ  ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል። ወ/ሮ ሃና አርዓያሥላሴ ፍትህ ሚኒስትር ተደርገው ከመሾማቸው በፊት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም ከዚያ በፊት የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ እንዲሁም የመንግስት ኮሙንኬሽን ምክትል ሚኒስትር የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የቱርዝም ሚንስትር ተደርገው መሾማቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ በመሆን በማገልገል ላይ የነበሩት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፤…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቀረበ

ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቀረበ

የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻ ሽያጩን በይፋ አስጀምሯል፡፡ 100 ቢሊየን ብር ጠቅላላ ሀብት ያለው ኢትዮ ቴሌኮም የ30 ቢሊዮን ብር አክስዮኑን ለሽያጭ አቅርቧል፡፡ አንዱን የድርጅቱን አክስዮን ዋጋ በ300 ብር እንደሚሸጥ ያስታወቀው ኢትዮ ቴሌኮም አንድ ግለሰብ መግዛት የሚችለው 33 አክስዮን ወይም 9 ሺህ 900 ብር ነው ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮ ቴሌኮም 3 ሺህ 333 አክስዮኖቹን ለሽጭ ያቀረበ ሲሆን 30 ቢሊዮን ብር ከአክስዮን ሽያጭ ለማግኘት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች አክስዮን መግዛት ይችላሉ የተባለ ሲሆን ተቋማት ግን አክሲዮንን መግዛት እንደማይችሉ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡ የአክሲዮን ሽያጩ ከዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይጠናቀቃልም…
Read More
የኢትዮጵያ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫን እንዲያጠቡ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫን እንዲያጠቡ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከውጭ ምንዛሪ ግብይት ጋር በተያያዘ ስለሚፈጸሙ ክፍያዎች የማሻሻያ ፖሊሲ ይፋ አድርጓል:: ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በዚህም ባንኮች በየእለቱ በሚያወጡት የውጭ ምንዛሬ የዋጋ ተመን ላይ በመግዣ እና በመሸጫው መካከል ከ10 በላይ ልዩነት ሲታይበት ቆይቷል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫው፤ አዲሱ የምንዛሬ ተመን አሰራር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ያሉ ሂደቶችን ሲከታተል መቆየቱን አስታውቋል። ብሔራዊ ባንክ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል። በመሆኑም የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት…
Read More
የኢትዮጵያ ብርቅዬ የዱር እንስሳ የሆነው ዋልያ የመጥፋት አደጋ ተደቅኖበታል ተባለ

የኢትዮጵያ ብርቅዬ የዱር እንስሳ የሆነው ዋልያ የመጥፋት አደጋ ተደቅኖበታል ተባለ

በኢትዮጵያ ካሉ የዱር እንስሳት መጠለያዎች ውስጥ አንዱ በሆነው በ ሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ከ900 በላይ ዋልያዎች የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ ቁጥራቸው ወደ 300 ዝቅ ብሏል፡፡ በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ መኖሪያቸውን ያደረጉና ከዚህ ቀደም ቁጥራቸው ከ900 በላይ የነበሩ ዋልያዎች ወደ 306 ዝቅ ማለታቸውን የፓርኩ ፅህፈት ቤት አስታውቋል:: የፓርኩ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ማሩ ቢያድግልኝ እንደተናገሩት በክልሉ በነበረው የፀጥታ ችግር በተሰማው የተኩስ ድምፅ በፓርኩ ውስጥ የነበሩ ብርቅዬ እንስሳቶች በመረበሻቸው በአሁኑ ሰአት ቁጥራቸው ቀንሷል ብለዋል:: አለመረጋጋቱን ተከትሎ በዋና ዋና የዱር እንስሳቶች መናሃሪያ ቦታዎች ላይ የጦር መሳሪያዎች የነበሩ በመሆናቸው በርካታ የዱር እንስሳቶች ከአካባቢዉ መራቃቸውን  የገለፁት ኃላፊው ከእነዚህም መካከል ዋልያዎች ተጠቃሽ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል። በሚመለከተው አካል በኩል…
Read More
ሀይኒከን ኩባንያ አራዳ ቢራን ጠቀለለ

ሀይኒከን ኩባንያ አራዳ ቢራን ጠቀለለ

የአራዳ መጠጥ ምርቶች አቅራቢ የሆነው ኮማሪ ቤቭሬጅ ለሃይኒከን መሸጡ ተገልጿል፡፡ በአጭር ጊዜ በተጠቃሚዎች ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘው የአራዳ መጠጦች አምራች ኮማሪ ፋብሪካውን ለሃይኒከን ለመሸጥ ሲያደርግ የነበረው ድርድር ከሳምንት በፊት አጠናቋል ተብሏል፡፡ የሽያጩ ድርድር ለበርካታ ወራት ሲደረግ ነበር የተባለ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች በሀምሌ ወር ወደ መጨረሻ የድርድር ምእራፍ ቢሸጋገሩም ሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓም ወደ ትግበራ የገባውን የምንዛሬ ገበያ ለውጥ ተከትሎ ድርድሩ በድጋሚ ሲደረግ እንደነበር ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ የሽያጩ ዋጋ በዚህ ወር መጨረሻ በይፋ ይገለጻል የተባለ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች በዚሁ ወቅት በይፋ ፋብሪካውን እንደሚረካከቡ ተገልጿል፡፡ ኮማሪ ከአዲስ አበባ በሰሜን ምስራቅ 96 ኪሜ ርቀት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጨኬ አካባቢ በገነባው ፋብሪካ…
Read More
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ መንገድ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ሰዎች አዲስ ህግ አዘጋጀች

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ መንገድ ልጅ መውለድ ላልቻሉ ሰዎች አዲስ ህግ አዘጋጀች

የዘር ፍሬ ልገሳን የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ “የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ” በሚል ርዕስ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ አስራ ሁለት ክፍሎች ያሉት ረቂቅ አዋጁ ስለ አጠቃላይ የጤና አገልግሎት፣ ስለ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ፣ ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች፤ ስለ ጤና ዘርፍ የሰው ኃብት ልማት እና አስተዳደር፤ ስለ ጤና እና ጤና ነክ ተቋማት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ቁጥጥርን የሚመለከቱ 60 አንቀጾች አሉት። ስለ ልዩ የጤና አገልግሎቶች የሚያወሳው የአዋጁ አራተኛ ክፍል ከዘረዘራቸው የጤና አገልግሎቶች መካከል አንዱ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ ሕክምና አገልግሎት ነው። በዚህ ንዑስ ክፍል ሥር የተካተተው አንቀጽ “ፈቃድ የተሰጠው የጤና ተቋም በቴክኖሎጂ የታገዘ የሥነ ተዋልዶ የሕክምና አገልገሎት ሊሰጥ ይችላል” ሲል ሕክምናው…
Read More
እንግሊዝ ለትግራይ ታጣቂዎች መልሶ ማቋቋሚያ 16 ሚሊዮን ፓውንድ እንደምትሰጥ ገለጸች

እንግሊዝ ለትግራይ ታጣቂዎች መልሶ ማቋቋሚያ 16 ሚሊዮን ፓውንድ እንደምትሰጥ ገለጸች

የብሪታኒያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ብሪታንያ መንግሥት ለኢትዮጵያ የ23 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቃለች፡፡ ከዚህ ውስጥ 16 ሚሊዮን ፓውንዱ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት ከተሳተፉት ውስጥ የትግራይ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የእንግሊዝ መንግስት በኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ዘርፍን ለመደገፍ የሚውል እና ለሶስት አመታት የሚቆይ የ6 ነጥብ 9 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡ ድጋፉ ትግራይን ጨምሮ ለተለያዩ ክልሎች የሚውል ሲሆን 7000 የሚሆኑ ሴት ሰራተኞችን ህይወት ለማሻሻል እና የወጭ ንግድን 20 በመቶ ለማሳደግ ያለመ ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት በተካሄደው በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የተሳተፉ ተዋጊዎችን ወደ ቀድሞ ህይወታቸው ለመመለስ በጀት በማሰባሰብ ለይ ስትሆን የአውሮፓ ህብረት 12 ሚሊዮን…
Read More
ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ መደበኛ የስልክ አገልግሎት ተቋረጠ

ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ መደበኛ የስልክ አገልግሎት ተቋረጠ

በ2010 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ነበር ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ለ20 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት ያደሱት፡፡ ሁለቱ ሀገራት የመደበኛ የስልክ አገልግሎትን ዳግም ካስጀመሩ ከሰባት ዓመታት በኋላ ተቋርጧል፡፡ ይህን ተከትሎም ከሐምሌ 2010 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ የስልክ አገልግሎት ሲሰራ የነበረ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ማለትም ከመስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደተቋረጠ በኢትዮጵያ ከሚኖሩ ኤርትራዊያን ሰምተናል፡፡ ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ኤርትራዊ ለአል-ዐይን እንዳሉት “ከማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መደበኛ ስልክ መደወል አልቻልኩም” ብለዋል፡፡ በኤርትራ ኢንተርኔት አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት ቤተሰቦቻችንን የምናገኘው በመደበኛ ስልክ ብቻ ነበር የሚሉት እኝህ አስተያየት ሰጩ አገልግሎቱ መቋረጡ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ “ቀስ በቀስ የኢትዮጵያ እና…
Read More
የጣና ፎረም ጉባኤ ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ

የጣና ፎረም ጉባኤ ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ

በባህር ዳር ከተማ ሊካሄድ የነበረው 11ኛው የጣና ፎረም ለሶስተኛ ጊዜ ተራዝሟል፡፡ የአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ የሚመክረው እና በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚካሄደው ዓመታዊው የጣና ፎረም ጉባኤ ለሶስተኛ ጊዜ ተራዘመ። 11ኛው ጉባኤ መጀመሪያ ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ባለፈው ዓመት ከጥቅምት 2-4 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር። ሆኖም ጉባኤው “ባልተጠበቁ ሁኔታዎች ምክንያት” እንደተራዘመ የፎረሙ ጽህፈት ቤት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላም እና ደህንነት ጥናቶች ተቋም አስታውቆ ነበር። ጉባኤው ሚያዚያ ወር 2016 ዓ.ም. እንደሚካሄድ ጽህፈት ቤቱ በጊዜው አስታውቆ የነበረ ቢሆንም በተባለው ጊዜ ሳይካሄድ ለሁለተኛ ጊዜ ተራዝሟል። “አፍሪካ እየተሻሸለ በመጣው የዓለም ሥርዓት ውስጥ” የሚል መሪ ቃል የያዘው 11ኛው ጉባኤ ከጥቅምት 15-17 2017 ይካሄዳል…
Read More
አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

ላለፉት ዘጠኝ ወራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ የኢትዮጵያ ስድስተኛው ፕሬዝዳንት ሆነዋል 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ ሁለቱ ምር ቤቶች በጋራ ባካሄዱት የመክፈቻ ስነ ስርዓትም አምባሳደር ታዬ አስጸቀስላሴ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል። የፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ አምባሳደር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል። አምባሳደር ፕሬዚዳንት ታዬም በምክር ቤቶቹ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሲሆን ከቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ሣለወርቅ ዘውዴ ጋር ሥራ እርክክብ አድርገዋል፡፡ አምባሳደር ታዬ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ መምሪያ የሥራ ክፍል ፣የምዕራብ አውሮፓ ዋና ክፍል ኃላፊ፣የኢንፎርሜሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር፣ስቶክሆልም የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት፣በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት እንዲሁም…
Read More