06
Aug
አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች የተሰኘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ በአውቶብስ ተጓዦችን ማመላለስ መጀመሩን አስታውቋል። ድርጅቱ ባለፈው ሳምንት እሁድ በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የድርጅቱ ዳይሬክተር ሚካኤል ጄምስ ማቺዮ ለቢቢሲ ተናግረዋል። "በአንድ ጉዞ 7 ሺህ 500 የኬንያ ሽልንግ ነው የምናስከፍለው። ለደርሶ መልስ ጉዞ ዋጋ 15 ሺህ የኬንያ ሽልንግ ወይም 16 ሺህ ብር ገደማ ያስከፍላል ተብሏል። ከኛ በፊት 'ሮያል አላይድ' የተሰኘ ከናይሮቢ ሞያሌ እና ሞምባሳ የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማራ ድርጅት አለ። ከአራት ዓመታት በፊት የተመሠረተው 'ሮያል አላይድ' እስከ ሞያሌ ከተማ ብቻ ይሠራ ነበር። በአውሮፕላን ቲኬት መወደድ ሳቢያ የአውቶብስ ትራንስፖርት ፍላጎት መኖሩን እና ይህንን ፍላጎት ሊያሟላ…