amharanews

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት ወረዳዎች በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን ተገደሉ

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት ወረዳዎች በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን ተገደሉ

አንድ ዓመት ባስቆጠረው የአማራ ክልል የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች ግጭት መቋጫ አላገኘም፡፡ በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጉሎ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡ ለደህንነቱ በመፍራት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የተሬ ቀበሌ ነዋሪ እንዳለው “ትናንት ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ላይ በመንደራችን ከባድ ፍንዳታ ተፈጥሮ ነበር፡፡ እኔን ጨምሮ የሰፈራችን ነዋሪዎች ፍንዳታው ወደ ተሰማበት ስፍራ ስንሄድ ጥቃቱ ጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ እንደተፈጸመ አየን” ሲል ተናግሯል፡፡ አስተያየት ሰጪው አክሎም “በዚህ የድሮን ጥቃት ሶስት አርሶ አደሮች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ትኖር የነበረች ሴት…
Read More
ኢትዮጵያ ትልቁን ድልድይ በአባይ ወንዝ ላይ ገነባች

ኢትዮጵያ ትልቁን ድልድይ በአባይ ወንዝ ላይ ገነባች

ከስድስት ዓመት በፊት የተጀመረው የአባይ ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል፡፡ በአማራ ክልል ጎንደርን እና ጎጃምን የሚያገናኘው የአባይ ድልድይ በቻይናው ሲሲሲሲ የስራ ተቋራጭ ድርጅት የተገነባ ሲሆን ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ወጭ ተደርጎበታል ተብሏል፡፡ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የፕሮጀክቱኢንጂነር ለሚ በቀለ አዲሱ የዓባይ ድልድይ በአይነቱም ሆነ በይዘቱ በአገራችን ከሚገኙ ድልድዮች የተለየ መሆኑን አስታውቋል። ድልድዩ 380 ሜትር ርዝመትና 43 ሜትር ስፋት ያለው ሲሆን በአንድ ጊዜም ስድስት መኪኖችን ለማስተላለፍ እንዲያስችል ተደርጎ ተገንብቷል ተብሏል። ድልድዩ በግራና ቀኝ 3 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ያለው የሳይክል መስመር እንዲሁም 5 ሜትር ስፋት ያለው የእግረኛ መንገድ አካቶ እየተሰራ ሲሆን፣ ለከተማዋ እድገትም ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በአማራ ክልል…
Read More
ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ ተጠርጣሪ ኢትዮጵያዊያን ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች

ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ ተጠርጣሪ ኢትዮጵያዊያን ተላልፈው እንዲሰጧት ጠየቀች

ኢትዮጵያ በወንጀል የምትፈልጋቸውን ሰዎች አሜሪካ አሳልፋ እንድትሰጣት ጥያቄ አቅርባለች፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ  ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአሜሪካው ኤፍ.ቢ.አይ (FBI) ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር አምባሳደሩ የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ኮሚሽነሩ በውይያታቸው ወቅት ጠይቀዋል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ በተለይም በአሜሪካን ሀገር እየኖሩ የሀገሪቱን ሰላም እያወኩ ነው በሚል የምትጠረጥራቸውን ሰዎች ተላልፈው እንዲሰጧት ለአምባሳደሩ ጥያቄ እንዳቀረቡም ተገልጿል፡፡ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በአሜሪካን መንግሥት የሚፈለጉ ወንጀለኞችን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አሳልፎ በመስጠት ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ተብሏል፡፡ አምባሳደሩ አክለውም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተመሳሳይ ድጋፎችን እንድታደርግ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል ሲል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ…
Read More
ህወሃት ታጣቂዎቹ በሱዳን ጦርነት እየተሳተፉ ነው መባሉን አስተባበለ

ህወሃት ታጣቂዎቹ በሱዳን ጦርነት እየተሳተፉ ነው መባሉን አስተባበለ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዛሬ ባወጣው መግለጫ "የህወሓት ኃይሎች" ከሱዳን ጦር ጎን በቅጥረኝነት ተሰልፈው ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጋር እየተዋጉ ነው መባሉን አስተባብሏል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ይህን ያለው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች በትናትናው እለት ባወጣው መግለጫ የህወሓት ኃይሎች ከሱዳን ጦር እና ተባባሪ ሚሊሻዎች ጋር ሆነው እየተዋጉት እንደሆነ ማረጋገጡን መግለጹን ተከትሎ ነው። የሱዳን ጦርነት ከተጀመረበት ከሚያዝያ 2023 ወዲህ የሱዳን ጦር የውጭ ቅጥረኞችን እርዳታ እየፈለገ ነው የሚል ክስ ያቀረበው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ጦር፣ በጦርነት ወቅት ተገድለው የተገኙ ቅጥረኞችን መመዝገቡን ጠቅሷል። የህወሓት ኃይሎች ከሱዳን ጦር ጎን ተሰልፈው  እየተዋጉ ነው የሚለውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች "መሰረተ ቢስ ክስ" በጽኑ እንደሚያወግዝ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል። ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደገለጸው ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች…
Read More
ከአላማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ50 ሺህ አለፈ

ከአላማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ50 ሺህ አለፈ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት 50 ሺህ ዜጎች ከራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡ እንደ ድርጅቱ ሪፖርት ከሆነ ከሰሞኑ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ባገረሸው ግጭት ምክንያት ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል ብሏል፡፡ ተፈናቃዮቹ በቆቦ፣ ወልደያ እና ሰቆጣ ከተሞች በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ላይ እንደተጠለሉም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ተጨማሪ ዜጎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የገለጸው ድርጅቱ ለተፈናቃዮች ውሃ፣ ምግብ እና ሌሎች ህይወት ማቆያ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡ አሁን ላይ ከለጋሽ ተቋማት እና ሀገራት የሚገኘው ድጋፍ እየተሟጠጠ በመሆኑ በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ የሚችለውን ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ለተፈናቃዮቹ መጠለያ፣ የሕክምና አገልግሎት እና ሌሎች መሰረታዊ ድጋፎችን ማድረግ ይገባል…
Read More
ከአላማጣ እና አካባቢው 29 ሺህ ህዝብ መፈናቀሉ ተገለጸ፡፡

ከአላማጣ እና አካባቢው 29 ሺህ ህዝብ መፈናቀሉ ተገለጸ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት 29 ሺህ ዜጎች ከራያ እና አላማጣ አካባቢዎች መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡ እንደ ድርጅቱ ሪፖርት ከሆነ ከሰሞኑ በትግራይ እና አማራ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ባገረሸው ግጭት ምክንያት ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል ብሏል፡፡ ተፈናቃዮቹ በቆቦ፣ ሰሜን ወሎ እና ሰቆጣ ከተማ በሚገኙ መጠለያዎች ላይ እንደተጠለሉም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ተጨማሪ ዜጎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የገለጸው ድርጅቱ ለተፈናቃዮች ውሃ፣ ምግብ እና ሌሎች ህይወት ማቆያ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡ አሁን ላይ ከለጋሽ ተቋማት እና ሀገራት የሚገኘው ድጋፍ እየተሟጠጠ በመሆኑ በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ የሚችለውን ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ ለተፈናቃዮቹ መጠለያ፣ የሕክምና አገልግሎት እና ሌሎች መሰረታዊ ድጋፎችን ማድረግ ይገባል…
Read More
በኢትዮጵያ 9 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ 9 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ በፀጥታ ችግር ምክንያት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 8.8 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት 8,977 ትምህርት ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 6,483 ሙሉ በሙሉ ዝግ መሆናቸውን በሚኒስቴሩ 'ትምህርትን በአደጋ ማስቀጠል' ባለሙያ ንጋቱ አበበ ተናግረዋል፡፡ ሚኒስቴሩ እና የክልል ትምህርት ቢሮዎች በጋራ በመሆን የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል ጥረት ቢያደርጉም፤ አሁንም በተለያዩ ቦታዎች በቀጠሉት ግጭቶች ምክንያት ችግሩን ለመፍታት አስቸጋሪ እንደሆነ ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉም ባለሙያው ጥሪ አቅርበዋል። ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል ጦርነት እየተካሄደ ባለበት የአማራ ክልል ውስጥ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን…
Read More
የባህር ሀይል ወታደሮች በአማራ ክልል ውጊያ እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለጸ

የባህር ሀይል ወታደሮች በአማራ ክልል ውጊያ እየተሳተፉ መሆኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለጸ

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳለው "የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ተሰማርቷል" ብሏል። ተቋሙ የባህር ሀይል ዋና አዛዥ ተወካይ ሬር አድሚራል ናስር አባዲጋን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው "ጽንፈኛ" ባላቸው ቡድን አባላት ላይ እርምጃ እንደወሰደ ገልጿል። የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ማሪን ኮማንዶዎች በሰሜን ሸዋ ዞን ባሉ ወረዳዎች እንደተሰማሩ እና ግዳጃቸውን እየተወጡ እንደሆነም አዛዡ መናገራቸው ተገልጿል። እንዲሁም ማሪን ኮማንዶ በመርከብ ላይ በባህር ከሚሰጠው ተልዕኮ በተጨማሪ በማንኛውም ጊዜ ግዳጁን የሚወጣ ሀይል እንደሆነም ሬር አድሚራል ናስር አባድጋ ተናግረዋል ተብሏል። ማሪን ኮማንዶ ከአማራ ክልል የጸጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን በወሰዳቸው እርምጃዎች የክልሉ ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱንም በዚሁ ዘገባ ላይ ተጠቅሷል። የፌደራል መንግሥት…
Read More
አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ለምን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ላለው ጦርነት ትኩረት ነፈጉ?

አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ለምን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ላለው ጦርነት ትኩረት ነፈጉ?

በፌደራል መንግስት እና የትግራይ ታጣቂዎች መካከል የተካሄደው እና ለሁለት ዓመት የዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ መዲና ፕሪቶሪያ በተፈረመ የሰላም ስምምነት መቆሙ ይታወሳል፡፡ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 2015 ዓ.ም የተካሄደው ይህ ጦርነት ተፋላሚዎች ወደ ተኩስ አቁም እንዲሄዱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት ቡድን ሰባት፣ ብሪታንያ እና ሌሎችም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገራት በጋራ እና በተናጠል የተለያዩ ጫናዎችን ሲያደርጉ ነበር፡፡ ጦርነቱ በፍጥነት ባለመቆሙ ምክንያትም ሀገራት በኢትዮጵያ ያላቸውን ፕሮግራሞች ማቋረጥ፣ ቢሮ መዝጋት፣ እንደ አግዋ ኤነት ለኢትዮጵያ ተሰጥተው የነበሩ የገበያ እድሎችን መከልከል፣ ተፈቅደው የነበሩ ብድሮችን መከልከል  እና የቀጥታ በጀት ድጋፎችን ማቋረጥ በኢትዮጵያ ላይ ከተደረጉ ጫናዎች ዋነኞቹ ነበሩ፡፡…
Read More
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከአንድ ዓመት በኋላ ዳግም ተቀሰቀሰ

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከአንድ ዓመት በኋላ ዳግም ተቀሰቀሰ

የትግራይ ታጣቂዎች ወደ አማራ ክልል ዘልቀው ወረዳዎን እና ቀበሌዎችን በሀይል እንደተቆጣጠሩ ተገልጿል፡፡ የአማራ ክልል መንግስት ባወጣው መግለጫ ህወሓት በፕሪቶሪያ የተፈረመውን የዘላቂ የሰላም ስምምነት በመጣስ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ ፈጽሞብኛል ሲል ከሷል። በፌደራል መንግስት በኩል ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት ለማድረግ መጣሩን የገለጸው ክልሉ፣ ህወሓት የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው በስምምነት አወዛጋቢ ተብለው የተለዩትን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ የኦፍላ፣ የኮረም እና ዛታ አካባቢዎችን ወርሯል ብሏል። የክልሉ መንግስት እንዳለው ህወሓት ለአራተኛ ዙር ወረራ በመፈጸም በህወሓት እና በፌደራል መንግስት መካከል ከተካሄዱት "ከባለፉት ሶስት ዙር ደም አፋሳሽ ጦርነቶች" አለመማሩን የሚያሳይ ነው። የአማራ ክልል ወረራ ተፈጽሞባቸዋል ያላቸው ቦታዎች እና የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ጠለምት በ2013 ጦርነት ከመቀስቀሱ…
Read More