Business

ኢትዮጵያ በሁሉም ወረዳዎች ኢንዱስትሪ የማቋቋም እቅድ እንዳላት ተገልጸ

ኢትዮጵያ በሁሉም ወረዳዎች ኢንዱስትሪ የማቋቋም እቅድ እንዳላት ተገልጸ

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወረዳዎች ውስጥ፤ ኢንዱስትሪዎች እንዲገነቡ ያለመ ስራ መጀመሩ ተነግሯል፡፡ እቅዱ በገጠር ያሉ ዜጎች የሚፈልጓቸውን ምርቶች ለመግዛት ወደ ከተማ እንዳይጓዙ ይረዳቸዋል ተብሏል፡፡ በሀገሪቱ ያሉ ወረዳዎች በየአካቢያቸው እንደሚያገኙት የግብዓት ዓይነት፤ እያንዳንዳቸው እስከ 3 ኢንዱስትሪዎች እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታውቋል፡፡ በዚህም ባለፉት 9 ወራት 206 ኢንዱስትሪዎች በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍሎች መቋቋማቸውን የጠቀሰው ተቋሙ፤ ቁጥራቸውን ለማሳደግ እቀጥላለሁ ብሏል፡፡ በገጠር አካባቢዎች ኢንዱስትሪዎች ማስፋፋት የአካባቢው ነዋሪዎች ምርት በቀላሉ እንዲያገኙ ከማድረጉም በተጨማሪ፤ የስራ እድል በመፍጠር ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገው ፍልሰት ይቀንሳልም ተብሏል፡፡ ባለፉት ዘጠኝ ወራትም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ 151,000 ሰዎች በመካከለኛ እና በአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ስራ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አብዱልፈታ…
Read More
ኢትዮጵያ ለሱዳን የምትልከው ኤሌክትሪክ ሀይል 80 በመቶ ቀነሰ

ኢትዮጵያ ለሱዳን የምትልከው ኤሌክትሪክ ሀይል 80 በመቶ ቀነሰ

በሱዳን ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት፣ ኢትዮጵያ ወደ ሀገሪቱ የምትልከው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን በ80 ከመቶ ያህል መቀነሱን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል፡፡ የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ የሱዳን የሃይል መሰረተ ልማት በጦርነቱ በመጎዳቱ የታቀደውን ያህል መጠን ሀይል መላክ አለመቻሉን ገልፀዋል፡፡ አቶ ሞገስ መኮንን እንዳሉት “ከሱዳን ጋር የተደረገው ስምምነት እስከ 100 ሜጋዋት ድረስ ለመላክ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን በመጠን ደረጃ በጣም ቀንሷል፡፡ ከ10 እስከ 20 ሜጋዋት ድረስ ነው እየላክን ያለነው፡፡ ዝቅ ሲል እስከ 10 ሜጋዋት፣ ከፍ ሲል ደግሞ እስከ 20 ሜጋዋት ይሆናል የምንልከው፡፡ ይህ የሱዳን የኤሌክትሪክ ሃይል መሰረተልማት በጦርነት በመጎዳቱ የመጣ ችግር ነው፡፡ ግጭቱ በጣም ከፍተኛ በሆነ…
Read More
ሆላንድ ዴይሪ የሙዝ ጣዕም ያለው እርጎ ለገበያ አስተዋወቀ

ሆላንድ ዴይሪ የሙዝ ጣዕም ያለው እርጎ ለገበያ አስተዋወቀ

የሆላንድ ዴይሪ የወተት ምርት አዲስ የሙዝ ጣዕም ያለው እርጎ ለኢትዮጵያ  ገበያ ማቅረቡን ገልጿል። የሆላንድ ዴይሪ የሙዝ እርጎ አመጣጥ የኢትዮጵያውያን ሸማቾች ጣዕምን የሚያሟላ የወተት ተዋጽእዎችን ማቅረብ ላይ በማተኮር፣ የክሬም ይዘት ያለው ከተፈጥሯዊ  የሙዝ ፍሬ ጣፋጭነት ጋር በማዋሃድ የሀገሪቱን የወተት ምርታማነት መስፈርት በጠበቀ መልኩ ማዘጋጀቱን ቀጥሏል ተብሏል። ይህ አዲስ የሙዝ እርጎ ምርት አሁን ያለውን የስትሮውበሪ (ኢንጆሪ) እና የማንጎ እርጎ አቀራረብ አይነት በሚገባ እንደሚያሟላም ኩባንያው አስታውቋል። ይህም የተቋሙን አቅርቦት በሌላ ከፍተኛ ጥራት ባለው ምርት በማሳደግ በሀገር ውስጥ ምርቱ በንቃት እንዲስፋፋ ያደርጋል ነው የተባለው። የሆላንድ ዴይሪ የወተት ተዋጽኦዎችን ለማቅረብ ከ4ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን እንስሳት አርቢዎች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ላይ እንደሚገኝም ተነግሯል። ሆላንድ ዴይሪ የደች ቴክኖሎጂን…
Read More
ኢትዮጵያ 50 ቡና ላኪዎችን አገደች

ኢትዮጵያ 50 ቡና ላኪዎችን አገደች

በኮንትሮባንድ ንግድ የተሳተፋ ከ50 በላይ የቡና ላኪዎች እገዳ ተጣሎባቸዋል። የቡና ምርት ለኮንትሮባንድና ለተለያዩ ህገወጥ ድርጊቶች እየተጋለጠ በመሆኑ የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት እየጎዳው ይገኛል ሲል የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል። የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር እንደተናገሩት ቡናን ለአልባሌ ነገር እንዳይውል ለማድረግ በሶፍት ዌር አማካኝነት እያንዳንዱ ምርት ከመነሻ እስከ መድረሻ መድረሱን ለማረጋገጥ የሚያስችል የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ ይገኛል። ይህም በተለይም ቡናን በአግባቡ ለውጪ ገበያ ለማቅረብ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀው ምርቱን ለኮንትሮባንድ ንግድ የሚያውሉ አካላት ላይ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሚገኙ አስረድተዋል። በዚህም መሰረት ቡናን ወደ ትክክለኛው መዳረሻ እንዲደርስ ባላደረጉት አካላት ላይ ከአስተዳደራዊ እርምጃ አንስቶ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል። በህገወጥ መልኩ ቡናን እየደበቁ ያሉትን በተመለከተ…
Read More
ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሞያሌ የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ለመጀመር ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሞያሌ የንግድ ልውውጥን በ1 ሺህ ዶላር ጣሪያ ለመጀመር ተስማሙ

ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለሁለት ዓመታት በዘለቀ ድርድር በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ማዕቀፍ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማቀላጠፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። በዚህም መሰረት በሞያሌ ድንበር ላይ ለሚደረጉ የሸቀጦች ንግድ የመጀመሪያ ጣሪያ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሆን ተወስኗል። በሞምባሳ የተጠናቀቀው ይህ ስምምነት የንግድ ሂደቶችን በማቅለል የድንበር ማህበረሰቦችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ያለመ ነው። በስምምነቱ የኢትዮጵያ የድንበር ንግድ ዞን ከሞያሌ በ50 ኪሎ ሜትር እንዲሁም የኬንያ ደግሞ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚወሰን ነው። ነጋዴዎችም በጋራ በተስማሙበት የምርት ዝርዝር መሰረት እስከ 1 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የንግድ ልውውጥ በወር እስከ አራት ጊዜ ድረስ ማካሄድ ይችላሉ ተብሏል። ይህ ስምምነት የንግድ ዋጋ ጣሪያዎችን፣ የጉዞ ድግግሞሽን እና የድንበር…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛውን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ አስመረቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛውን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ አስመረቀ

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ ከመገናኛ ወደ ቦሌ  በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ እጅግ ፈጣን ያለውን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ሁለተኛውን ጣቢያ በይፋ ሥራ አስጀምሬያለሁ ብሏል። ኩባንያው ከዚህ ቀደም ከቦሌ ወደ መገናኛ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ 16 መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል የኤሌክትሪክ መኪና መሙያዎችን የያዘ ጣቢያ ገንብቼ ወደ ስራ አስገብቻለሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም ከየካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ14 ሺህ 280 የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎት መስጠት ችሏል ተብሏል። ለዚህም 376,574.72 ኪሎዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ጥቅም ላይ ውሏል የተባለ ሲሆን በተጨማሪም 521,074.23 ኪሎግራም ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ መከላከል የተቻለ ሲሆን፣ ይህም ከ2,622 በላይ ዛፎችን ከመትከል ጋር እንደሚነጻጸር ተገልጿል። በምራፍ ሁለት…
Read More
ኢትዮጵያ በውጭ ባንኮች ላይ የአምስት ቢሊዮን ብር ግዴታ ጣለች

ኢትዮጵያ በውጭ ባንኮች ላይ የአምስት ቢሊዮን ብር ግዴታ ጣለች

ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የውጪ ባንኮች አምስት ቢሊዮን ብር ዝቅተኛ ካፒታል ሟሟላት እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያወጣው አዲስ መመሪያ ጥብቅ ቅደመ ሁኔታዎችን ያስቀመጠ ነው ተብሏል። መመሪያው በባንኩ ዘርፍ የውጭ ሀገራት ተሳትፎን የውጭ ባንክ ተቀጥላ፣ የውጭ ባንክ ቅርንጫፍ እና የእንደራሴ ቢሮ ብሎ የሚከፍል ሲሆን ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት የወንጀል እና የታክስ ማጣራትን ጨምሮ ጥብቅ ምርምራዎችን ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው አስቀምጧል። የውጭ ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ብቻ ለማስቀመጥ እና ለመጠቀም ይገደዳሉ የተባለ ሲሆን ክፍያን በተመለከተ ከውጭ የሚገቡ ባንኮች ለምርመራ 200 ሺህ፣ ለፈቃድ 400 ሺህ እና ለእድሳት 400 ሺህ ብር መክፈል እንዳለባቸው ተቀምጧል። መመሪያው የሀገር ውስጥ ባንኮች ካፒታላቸውን መጨመር፣ የመረጃ አጠቃቀም ሕጋቸውን ከሀገሪቱ…
Read More
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ32 ቢሊዮን ብር ገንዘብ ድጋፍ አደረገ

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ32 ቢሊዮን ብር ገንዘብ ድጋፍ አደረገ

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ለስድሰት የልማት ፕሮጀክቶች የሚውል የ32 ቢሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት ለስድሰት ዋና ዋና የልማት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል የ240 ሚሊየን ዩሮ ወይም የ32.3 ቢሊየን ብር የልማት ድጋፍ ስምምነት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል። ከፕሮጀክቶቹ መካከል በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችን አስተዳደርና አካታችነትን በማሻሻል መረጋጋትን ማስፈን የሚለው ይገኝበታል። በተጨማሪም በግጭት የተጉዱ የጤና ተቋማትን ወደ አገልግሎት ለመመለስና እንዲሁም ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል፡፡ የስራ ዕድል የሚፈጥሩ የግብርና ስራዎችን፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በመጠቀም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ልማትን በማሳደግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ማምጣት፣ የዴሞክራሲ ተቋማትን ማጠናከር ደግሞ ሌሎቹ የድጋፍ ስምምነቱ ፕሮጀክቶች አካል መሆናቸው ተጠቁሟል። በፊርማ ስነ…
Read More
ኢትዮጵያ ለቤት ሰራተኞች የጡረታ ክፍያ ልትጀምር ነው

ኢትዮጵያ ለቤት ሰራተኞች የጡረታ ክፍያ ልትጀምር ነው

የቤት ሠራተኞችን የጡረታ ተጠቃሚ የሚያደርግ የሥራ ቅጥር ውልና አጠቃላይ ደንብ በ6 ወር ውስጥ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ የቤት ሠራተኞች ጡረታን ጨምሮ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል የሥራ ቅጥር ውልና አጠቃላይ የቤት ሠራተኞች ደንብ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አንድነት የኢትዮጵያ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ማህበራት ሕብረት አስታውቋል። የሕብረቱ ፕሬዚዳንት ሂሩት አበራ የቤት ሠራተኞችን ሕግ በሚመለከት በዓለም አቀፉ ኮንቬንሽን 189 በተቀመጠው ሕግ መሠረት በቀጥታ ለመተግበር አስቻይ ሁኔታ ባለመኖሩ፤ ከኢትዮጵያ ጋር እንዲስማማ ተደርጎ ደንቡና የሥራ ቅጥር ውሉ እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል፡፡ ይኸው ደንብ በረቂቅ ደረጃ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል እየተዘጋጀ እንደሚገኝም ጨምረው አስታውቀዋል። ለአብነትም በቋሚነት የሚሰሩ ሠራተኞች በሥራ ቦታቸው ላይ የመኖር፣ ተመላላሽ…
Read More
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ጣለች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ጣለች

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ ታሪፍ እንዲጣል ያዘዙ ሲሆን ኢትዮጵያም ወደ አሜሪካ በምትልካቸው ምርቶች ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ ተጥሎባታል። ፕሬዚዳንቱ በነጩ ቤተ መንግሥት በሰጡት መግለጫ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ አዲስ የታሪፍ መጠኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል። እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ እርምጃው አሜሪካን ቀዳሚ ለማድረግ እና የንግድ ጉድለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። በአብዛኛዎቹ ሀገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ10% እስከ 49% የሚደርስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም 10% ታሪፍ ተጥሎባታል። ኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ከተሞች አበባ፣ ቡና፣ የቆዳ እና አልባሳት ምርቶችን በመላክ ላይ ስትሆን ተጨማሪ 10 በመቶ ቀረጥ ለመክፈል ትገደዳለች። አሜሪካ የንግድ ጉድለቷን ለመቀነስ እና የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ ይህን እርምጃ እንደወሰደች የገለፁት…
Read More