08
Sep
በሕገ ወጥ የወርቅ፣ የገንዘብና የጦር መሣሪያ ዝውውር ተሳትፈዋል የተባሉ 76 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡ ፋና እንደዘገበው ከሆነ በተጠቀሱት የወንጀል ድርጊቶች ተሰማርተው በነበሩ የውጭ ሀገር ዜጎችና ኢትዮጵያውያን ላይ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሲዳማ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ክትትል ሲደረግ ቆይቷል ተብሏል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የወርቅ ማዕድን በሕገ ወጥ መንገድ በማምረት፣ በመሰወርና በማዘዋወር፣ የሀገራችንን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችን እንዲሁም ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን በማዘዋወር ወንጀሎች ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ መግለጫው ጠቁሟል፡፡ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስና ከየክልሎቹ የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባካሄደው ልዩ ኦፕሬሽን እስካሁን 45 የውጪ ሀገር ዜጎች እና 31 የሀገር ውስጥ በድምሩ…