30
Mar
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ኩባንያው ከሽያጭ ማዕከል መክፈት በተጨማሪ የማምረቻ እና መገጣጠሚያ ማዕከልም እንዲከፍት ጠይቀዋል። GAC JUNTU አዲስ ዘመናዊና ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠራ የትራንስፖርት ሥርዓት በማስተዋወቅ፣ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ቀዳሚ የኤግዚቢሽን ማዕከሉን በአዲስ አበባ በይፋ መርቋል። የኩባንያው የምርት ማሳየ 2,300 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ሲሆን ከማሳያነት ባለፈ ከሽያጭ በኋላ አገልግሎት፣ መለዋወጫ እና በአምራች የተደገፈ ዋስትና የሚሰጥበት አካቷል ተብሏል። ተቋሙ የተሽከርካሪ ሽያጭን፣ የተረጋገጠ የድኅረ-ሽያጭ አገልግሎትን፣ ኦሪጅናል የመለዋወጫ ዕቃዎችን እና ከአምራቹ የሚሰጥ ዋስትናን ያካተተ የተሟላ የ4S-ደረጃ ሥርዓት (4S-standard ecosystem) በማቅረብ በኢትዮጵያ ለታማኝነትና ለደንበኞች አገልግሎት አዲስ መለኪያ ያስቀምጣል። GAC JUNTU የኢትዮጵያን ገበያ አራት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ይዞ መቅረቡን…