28
Feb
በኢትዮጵያ እያሻቀበ ላለው የተረጂዎች ቁጥር ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ መንግስት አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች የምግብ ርዳታ ለማቅረብ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ ባወጡት ሪፖርት ላይ አስታውቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ አታለለ አቡሃይ፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ያለው የተረጅዎች ብዛት 6 ነጥብ6 ሚሊዮን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የተፈጥሮ አደጋዎች፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ጦርነት እና ሌሎች አደጋዎች ምክንያት የተፈናቃዮች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል፡፡ የብሪታንያ የአፍሪካ ልማት ዳይሬክተር በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ካደረጉ በኋላ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የ125 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም አሳሳቢ የምግብ…