19
Feb
በሶስት ባንኮች ላይ የ89 ሚሊዮን ብር ምዝበራ የፈጸመው ቡድን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በሐሰተኛ የባንክ ዋስትና ሰነድ በመጠቀም በገዳ ባንክ፣ በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎችን ከነግብረ-አበሮቻቸው በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። ተጠርጣሪዎቹ በተቀነባበረ ሴራ በአጠቃላይ ከ89 ሚሊዮን 296 ሺህ ብር በላይ በሀገር ኢኮኖሚ እና በባንኮች ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብሏል። ተጠርጣሪው የጎደር ዋይን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ ጌታሁን መለስ ሲሆን፣ ከገዳ ባንክ አገምሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አብዲሳ ቶሎሳ ጋር በጥቅም በመመሳጠር የቅርንጫፉን ፊርማና ማህተም ለወንጀል ተግባራቸው ሲጠቀሙበት መቆየታቸው ተገልጿል። ዋነኛው ተጠርጣሪ…