አካባቢ ጥበቃ

በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር የሚኖሩ ህዝቦች ከባድ የድርቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ

በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር የሚኖሩ ህዝቦች ከባድ የድርቅ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተባለ

ቦረናን ጨምሮ 85 በመቶ የሚሆነው በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር አካባቢ ያለ ህዝብ በመጪው ዓመት ከባድ የድርቅና ረሃብ ስጋት እንደተጋረጠባቸው ተገልጿል። በኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር ቦረና ኢትዮጵያ እና ማርሳቢት ኬንያ አካባቢ ዝናብ አጠር መሆኑና አልፎ አልፎ ሲዘንብም ጎርፍ የሚያስከትል መሆኑ ተነግሯል፡፡ ቮለንተሪ ሰርቪስ ኦቨር ሲስ(VSO)፣ ሆርን ኦፍ አፍሪካ ዴቨሎፕመንት ኢንሼቲቭ (HODI) ፣አውስትራሊያን ዴቨሎፕመንት ኮፕሬሽን እና  ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት ኤንድ ጉድ ገቨርነንስ  የተሰኙ የሲቪል ማህበራት በአካባቢው ሲሰሩ የቆዩትን የመጀመሪያ ዙር ፕሮጀክት መዝጊያ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። የVSO የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ተመስገን አለሙ የአትዮጵያ ኬንያ ድንበር ከግጭት፣ ከድርቅ እና ረሃብ ባለፈ አካባቢው የአደንዛዥ ዕፅ ፣ ህገ-ወጥ የሰው ዝውውር እና ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት…
Read More
ከ18 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች  አርሶ አደሮችን የሚያገለግሉት 4 ብቻ ናቸው ተባለ

ከ18 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች አርሶ አደሮችን የሚያገለግሉት 4 ብቻ ናቸው ተባለ

ኢትዮጵያ ለግብርናው ዘርፍ የምትሰጠው የኢንሹራንስ አገልግሎት ሽፋን 0 ነጥብ 04 በመቶ ብቻ እንደሆነ በግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ የገጠር ፋይናንስ ክፍል የቡድን መሪ የሥራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸው መኮንን፤ ከ80 በመቶ በላይ የግብርና መር ኢኮኖሚ ያላት ኢትዮጵያ በአርሶ አደሮቿ ምርት ላይ ለሚደርስ አደጋ የምትሰጠው የመድኅን ሽፋን ከአንድ በመቶ በታች ነው ብለዋል፡፡ "ኢትዮጵያ ለአርሶ አደሮቿ የምትሰጠው የግብርና መድኅን ሽፋን ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስተኛ ነው" ያሉት ሥራ አስፈጻሚው፤ "በኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ 18 የኢንሹንስ ኩባንያዎች መካከል ለአርሶ አደሮች የኢንሹራንስ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃድ አግኝተው በመስራት ላይ የሚገኙት 4 ብቻ ናቸው" ብለዋል። ባለፉት 10 ዓመታት በኢትዮጵያ በተለያዩ አጋር ድርጅቶች የኢንሹራንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለው ከ3…
Read More
በአፋር ክልል በተፈጠረ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ43 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቀሉ

በአፋር ክልል በተፈጠረ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ43 ሺህ በላይ ዜጎች ተፈናቀሉ

በአፋር ክልል፣ ኪልበቲ ረሱ ዞን፣ በርሃሌ ወረዳ ባሳለፍነው ቅዳሜ ምሽት በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ 43,456 ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል፡፡ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ሁሴን እንዳሉት ለተፈናቃዮቹ የሚሆን ምግብ እና መጠለያ፤ ከባድ ጉዳት ወደ ደረሰባቸው ቀበሌዎች እየተጓጓዘ ነው ብለዋል።  በክልሉ ባሳለፍነው ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ከበርሃሌ በተጨማሪ በተመሳሳይ ዞን ውስጥ በሚገኙት ኮናባ እና ዳሎል ወረዳዎችም የተከሰተ እንደነበርም የክሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል። በበርሃሌ ወረዳ የመጀመሪያው ርዕደ መሬት ከደረሰበት ከምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ለስድስት ጊዜያት ያህል የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አቶ አሊ አስረድተዋል።  በወረዳው ካሉ ቀበሌዎች በርዕደ መሬቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው፤…
Read More
ከተሽከርካሪዎች የሚወጣ በካይ ጋዝ የሚቆጣጠር መመሪያ ተዘጋጀ

ከተሽከርካሪዎች የሚወጣ በካይ ጋዝ የሚቆጣጠር መመሪያ ተዘጋጀ

‎በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት የተዘጋጀው፤ ከተሽከርካሪዎች የሚወጣን ጎጂ የካይ ጋዝ ልቀት ለመቆጣጠር የሚያገለግለው አስገዳጅ መመሪያ ከመስከረም 30 ቀን 2018 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። ዋነኛ ዓላማው የትራንስፖርት ዘርፉ ለበካይ ጋዝ ልቀት የሁለት ሦስተኛ ድርሻ ያለው በመሆኑ በጎጂ በካይ ጋዞች ምክንያት የሚከሰትን የአየር ብክለት መቀነስ ሲሆን፤ አዲሱ መመሪያ ሙሉ ለሙሉ ሲተገበር ተሽከርካሪዎች ወደ አየር የሚለቁትን የበካይ ጋዝ መጠን የሚቆጣጠር መሳሪያ እንዲገጥሙ ይገደዳሉ ተብሏል። የተቋሙ የትራንስፖርት ዘርፍ የአየር ንብረት ክትትል እና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ ግርማ ሳሙኤል፤ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ መመሪያው ከጸደቀበት መጋቢት 2017 ጀምሮ ውይይቶች ሲካሄዱበት እንደነበርም ተናግረዋል። በዚህም አስገዳጅ መመሪያው ከጸደቀ በኋላ ከታክሲ ማኅበራት፣ ከክልል ከተማ አስተዳደሮች…
Read More
ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመረቀች

ኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመረቀች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኬንያው ፕሬዚዳንት ውሊያም ሩቶ፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኢል ኦማር ጊሌ፣ የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር በተገኙበት የዓባይ ግድብ መርቀዋል። የኢትዮጵያ የዓባይ ግድብ የምረቃ ሥነስርዓት ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓም ሲካሄድ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች፣ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል። የዓባይ ግድብ ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ 233 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደገ ሲሆን፤ ቦንድ በመግዛት፤ ስጦታ በመስጠት እና በሌሎች መንገዶች ህዝብ ትልቅ ተሳትፎ እንዳደረገ በስፋት ተግልጿል፡፡ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት የህዳሴ ግድቡ መጠናቀቅም የኢትዮጵያን አቅም በሁሉም ዘርፍ የሚያሳግ እንደሆነም የተለያዩ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ዓባይ ግድብ የሚገኘው በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ…
Read More
የኢትዮጵያ ሙቀት በየዓመቱ ከአንድ ድግሪ ሴልሺየስ በላይ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሙቀት በየዓመቱ ከአንድ ድግሪ ሴልሺየስ በላይ እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በኢትዮጵያ የሙቀት መጠን በየዓመቱ በአማካይ ከ1 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እየጨመረ ነው ተብሏል ኢትዮጵያ ለአለም ሀገራት የሙቀት መጨመር ያላት የበካይ ጋዝ ልቀት ድርሻ ግን 0.04 በመቶ ነው ተብሏል፡፡ ያደጉት ሀገራት ለአፍሪካ በየጉባኤው ቃል የሚገቡትን የአየር ንብረት ለውጥ መደገፊያ የፋይናንስ ድጋፍ እየሰጡ ስላልሆነ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የሚሰራው ስራ የሚፈለገውን ያህል መሆን አልቻለም ተብሏል፡፡ ይህ የተነገረው በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የሚመክረውና ኢትዮጵያ ከጳጉሜ 3 እስከ 5 ከምታሰናዳው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አስቀድሞ በተሰናዳ ዝግጅት ላይ ነው፡፡ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዛሬ ያሰናዳውና ነገም የሚቀጥለው ጉባኤና ኢግዚብሽን ከዋናው ጉባኤ በፊት የሚደረግ ቅድመ ጉባኤ ስለመሆኑ ተናግሯል፡፡ በዝግጅቱ መክፈቻ…
Read More
በአረብ ሀገራት የሚገኙት አቦሸማኔዎች ከኢትዮጵያ የተሰረቁ ናቸው ተባለ

በአረብ ሀገራት የሚገኙት አቦሸማኔዎች ከኢትዮጵያ የተሰረቁ ናቸው ተባለ

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ሀብት ላይ ከተደቀኑ በርካታ ችግሮች መካከል ህገወጥ የእንስሳት ዝውውር አንዱ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል። በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ህገወጥ ዝውውር ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጳውሎስ  እንደተናገሩት ለተለያዩ አላማዎች ሲባል በኢትዮጵያ የሚገኙ የዱር እንስሳት ከነህይወታቸው በህገወጥ መንገድ ይዘዋወራሉ። በዚህ መልኩ ከሀገር የሚወጡ እንስሳቶች በርካታ ቢሆኑም  በቀዳሚነት አቦሸማኔ ይጠቀሳል ። አቦሸማኔ በተለይም በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በሱማሌ ክልል መኖሪያውን በማድረጉ የአካባቢው ማህበረሰቦች ባካበቱት ተፈጥሮአዊ ዘዴ የአቦ ሸማኔ ቡችላዎችን በመያዝ ሶማሌላንድ አካባቢ ለሽያጭ እንደሚያቀርቡ ተጠቁሟል። በዚህ መልኩ ይህ እንስሳ ወደ መካከለኛው የአረብ ሀገራት ጭምር ላሉ ባለሀብቶች የሚሸጥበት ሁኔታ መኖሩን የገለፁት አቶ ዳንኤል ግለሰቦቹ የራሳቸው የሆነ መካነ አራዊት…
Read More
ኢትዮጵያ የጣና ደሴት እና ገዳማትን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ዘመቻ ጀመረች

ኢትዮጵያ የጣና ደሴት እና ገዳማትን በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ዘመቻ ጀመረች

የጣና ሀይቅ ደሴትና ገዳማት በአለም አቀፍ የቅርስ መዝገብ እንዲሰፍሩ የሚያስችለዉ ሰነድ ለዮኔስኮ ተልኳል። በአማራ ክልል የሚገኙ የመስህብ ሀብቶችን በማልማትና በማስተዋወቅ የባህልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪውን በማሳደግ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ  አስታውቋል። የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ እምቢአለ እንደተናገሩት በክልሉ የሚገኙ በርካታ የመስህብ ቦታዎች እንደመኖራቸው የጣና ሀይቅ እና አካባቢውን በዮኔስኮ አለም አቀፍ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል። ከዚህ ቀደም  የጣና ሀይቅ ደሴቶች በብዛ ህይወት ቅርስነት የተመዘገበ መሆኑን ገልፀው በአሁኑ ወቅት ይህ ስፍራ በአለም አቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ ለማድረግ በተዘጋጀዉ ሰነድ ዙሪያ ማስተካከያ መደረጉን ተናግረዋል። ሰነዱን አስመልክቶ አስተያየት የመስጠትና ተጨማሪ ግብዓቶችና ማስተካከያዎችን የማዘጋጀት ስራ ሲሰራ እንደቆየ የገለፁት…
Read More
ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛውን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ አስመረቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ሁለተኛውን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ጣቢያ አስመረቀ

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ ከመገናኛ ወደ ቦሌ  በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ እጅግ ፈጣን ያለውን የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ ሁለተኛውን ጣቢያ በይፋ ሥራ አስጀምሬያለሁ ብሏል። ኩባንያው ከዚህ ቀደም ከቦሌ ወደ መገናኛ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ 16 መኪኖችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል የኤሌክትሪክ መኪና መሙያዎችን የያዘ ጣቢያ ገንብቼ ወደ ስራ አስገብቻለሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡ በዚህም ከየካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ14 ሺህ 280 የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎት መስጠት ችሏል ተብሏል። ለዚህም 376,574.72 ኪሎዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ጥቅም ላይ ውሏል የተባለ ሲሆን በተጨማሪም 521,074.23 ኪሎግራም ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይለቀቅ መከላከል የተቻለ ሲሆን፣ ይህም ከ2,622 በላይ ዛፎችን ከመትከል ጋር እንደሚነጻጸር ተገልጿል። በምራፍ ሁለት…
Read More
ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቃል ተባለ

ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቃል ተባለ

ከ15 ዓመት በፊት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴው ግድብ በያዝነው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ከህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ በሰጡበት ውቅት እንዳሉት ህዳሴ ግድብን ከ6 ወር በኋላ እንመርቃለን ብለዋል፡፡ መንግስት ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብፅ መንግስት ጋር በተለይም ከደህንነት መስሪያ ቤት ጋር ህዳሴን በተመለከተ ውይይት አድርገናል የተለያዩ ሃሳቦችም በህዳሴ ግድብ ዙሪያ አቅርበናል ብለዋል፡፡ መንግስት በህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከግብፅ ጋር ለመነጋገርና ለመወያየት ዝግጁ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል:: የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ 15 ዓመታት ሊሞሉት አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል።…
Read More