24
Feb
በትግራይ ክልል ጦርነት የቆመ ቢሆንም ከጫፍ ጫፍ ተንቀሳቅሶ መስራት አደጋች ሆኗል ተብሏል፡፡ በክልሉ ከመልካም አስተዳድር ጥያቄዎች ይልቅ የምግብ ጉዳይ ዋነኛው ችግር እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት በቆየው ጦርነት ምክንት ስራ አቁሞ ከነበሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠበቃ ተቋም መቀሌ ቀርንጫፍ አንዱ ነበር፡፡ ይህ ጦርነት በደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በተደረገው የፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ጦርነቱ የቆመ ሲሆን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ዳግም ስራ ጀምረዋል፡፡ ከታህሳስ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሥራውን በአዲስ መልክ የጀመረው የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም መቀሌ ቅርንጫፍ በበጀት እጥረት ምክንያት ጉዳዮችን ለመመልከት አዳጋች እየሆነበት እንደመጣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ደጋፊት ረዳ ለኢትዮ ነጋሪ ተናግረዋል። ተወካይዋ እንዳሉት…