24
Feb
በትግራይ ክልል ባለው አሁናዊ ሁኔታ የህጻናት የተጓዳኝ በሽታ መድኃኒት እና የኤች አይ ቪ መመርመሪያ ኪት እጥረት መኖሩን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አሰታወቀ፡፡ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የዘርፈ ብዙ ምላሽ የኤች አይ ቪ መከላከል እና መቆጣጠር ስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፍሥሀ ብርሃነ ለትግራይ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከሶስት አመት በፊት በኤች አይቪ ስርጭት እና መቆጣጠር የተሻለ ጤና አፈፃፀም ነበረው ብለዋል። አሁን ላይ ግን የኤችአይቪ ስርጭቱ ወደ ከፋ ሁኔታ ውስጥ ገብቷል። በፀጥታ እጦት ወቅት በርካታ ሴቶች እና እናቶች የመደፈር አደጋ ተጋላጭ በመሆናቸው እንዲሁም መድኃኒት ተጠቃሚ የነበሩ ሰዎችም በመድሀኒት እጥረት በማቋረጣቸው ለበሽታው ስርጭት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የክልሉ ጤና ቢሮ ባደረገው ጥናት…