Tigray

ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከሰሞኑ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር በአዲስ አበባ የነበሩት ጌታቸው ረዳ በትግራይ አዲስ የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ በሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ መመረጣቸው ተነግሯል። የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ቪኦኤ) የትግርኛው አገልግሎት ክፍል እንደዘገበው፣ ጌታቸው የማዕከላዊ ኮሚቴውን አብላጫ ድምጽ አግኝተዋል። የቀድሞው የሕግ መምህር ጌታቸው ረዳ፣ በመንግሥት እና በሕወሓት መካከል በፕሪቶሪያ የሕወሓት  ዋንኛ ተደራዳሪ የነበሩ ናቸው። የሽግግር ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም እየተንቀሳቀሰች የምትገኘው ትግራይ ክልል፣ ከጦርነቱ አስቀድሞ በዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ስትመራ ነበር። ከሰሞኑ በወጡ ዘገባዎች የፌዴራሉ መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትግራይ በደብረጽዮን መሪነት እንድትቀጥል አይፈልጉም። ዋሺንግተን ፖስት ይዞት በወጣው ዘገባ ዐቢይ ለትግራዩ ጦርነት መጀመር ደብረጽዮንን ይወቅሳሉ። የሕወሓት ሰዎች ከሰላም ስምምነቱ በኋላ…
Read More