28
May
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት 9 ወራት 14.5 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙን አስታውቋል፡፡ ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ13 በመቶ እድገት እንዳለው ዋና ስራ አስፈፃሚው መስፍን ጣሰው ተናግረዋል፡፡ አየር መንገዱ በዘጠኝ ወር ውስጥ ያገኘው ገቢ 5.6 ቢሊዮን ዶላር መሆኑንን የተናገሩት አቶ መስፍን ጣሰው ገቢውም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲተያይ የ8 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ብለዋል፡፡ በጊዜ ማዕቀፍ 10 አዳዲስ አውሮፕላኖች የኢትዮጵያ አየር መንገድን መቀላቀላቸው የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሶስቱ ኤርባስ A350-1000 መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ በዘጠኝ ወሩ ውስጥ አራት አዳዲስ የበረራ መዳረሻዎችንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ መክፈቱን ጠቅሷል፡፡ አየር መንገዱ የፊታችን እሁድ ጁን 1, 2025 ከአዲስ አበባ ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬት ሻርጃህ ከተማ…