Football

ናይጄሪያ አውስትራሊያን በማሸነፍ በዓለም ዋንጫው ቆይታዋን አለመለመች

ናይጄሪያ አውስትራሊያን በማሸነፍ በዓለም ዋንጫው ቆይታዋን አለመለመች

ናይጄሪያ አውስትራሊያን በማሸነፍ በዓለም ዋንጫ ውድድር ያላትን ቆይታ አለምልማለች። በአውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የፊፋ ሴቶች ዓለም ዋንጫ ከተጀመረ ስምንተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል። አፍሪካ በዚህ ውድድር በናይጀሪያ፣ ዛምቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሞሮኮ ተወክላለች። ናይጀሪያ በዛሬው ዕለት ከአውስትራሊያ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ ከመመራት ተነስታ 3ለ2 ማሸነፍ ችላለች። ናይጀሪያ ማሸነፏን ተከትሎ ምድቧን በአራት ነጥብ መምራት የጀመረች ሲሆን ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ አንድ ነጥብ ብቻ በቂዋ ይሆናል። አፍሪካን በዚህ ውድድር የወከሉት ሌሎቹ ብሔራዊ ቡድኖች ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድላቸው የመነመነ ሲሆን ሞሮኮ አስቀድማ ከውድድሩ ተሰናብታለች። የሴቶች ዓለም ዋንጫ ውድድር እስከ ነሀሴ 20 ቀን 2023 ውስጥ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ይካሄዳል። ከዚህ በፊት የሴቶች…
Read More
የሴቶች ዓለም ዋንጫ ነገ ይጀመራል

የሴቶች ዓለም ዋንጫ ነገ ይጀመራል

እንደ ወንዶች የዓለም ዋንጫ ሁሉ በየ አራት አመቱ የሚካሄደው የሴቶች እግር ኳስ ዓለም ዋንጫ ነገ ይጀመራል። አውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ በጋራ የሚያስተናገዱት የ2023 የፊፋ ሴቶች ዓለም ዋንጫ አዘጋጆቹ አውስትራልያ እና ኒውዝላንድ የመክፈቻ ውድድር ጨዋታን ያደርጋሉ። ውድድሩ ከፈረንጆቹ ሀምሌ 20 እስከ ነሀሴ 20 ቀን 2023 ውስጥ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ ይካሄዳል ተብሏብ። ከዚህ በፊት የሴቶች ዓለም ዋንጫ በ24 ብሔራዊ ቡድኖች አማካኝነት ይካሄድ የነበረ ሲሆን በዘንድሮው ግን ፊፋ የተሳታፊ ሀገራትን ቁጥር ወደ 32 ከፍ አድርጎታል። አፍሪካ በዚህ ውድድር ላይ በአራት ሀገራት የሚወከሉ ሲሆን ናይጀሪያ ፣ ዛምቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሞሮኮ ተሳታፊ ሀገራት ናቸው። የናይጀሪያዋ አሲሳት ኦሾላ በውድድሩ ትደምቃለች ተብሎ ከወዲሁ ትኩረት የተሰጣት ተጫዋች…
Read More
ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን ቀዳሚ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆነ

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዓለማችን ቀዳሚ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆነ

የአልናስር አጥቂ የሆነው ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልድ የ2023 ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆኖ ተመዝግቧል። እንደ ፎርብስ ዘገባ ከሆነ የአምስት ጊዜ ባሎንዶር ተሸላሚው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በተያዘው ዓመት ብቻ 136 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቷል። የዓለም ዋንጫ አሸናፊው አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ በ2022 ዓመት 130 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ተከፍሎታል። ክርስቲያኖ ካገኘው የ136 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ ገቢ ውስጥ 90 ሚሊዮን ዶላሩን ከሜዳ ውጪ ማለትም ከማስታወቂያ እና ስፖንሰር ስራዎች ማግኘቱ ተገልጿል። በማንችስተር ዩናይትድን ባለ መግባባት ወደ ሳውዲ አረቢያው አልናስር ያመራው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ደመወዙ እጥፍ እንዳደገለትም ተገልጿል። በአጠቃላይ በስፖርቱ ዘርፍ ሊዮኔል ሜሲ እና ክሊያን ምባፔ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ በመቀጠል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዱረጃን ይዘዋል። የቅርጫት ኳስ ኮኮቡ ለቦርን 119 ሚሊዮን…
Read More
ተጠባቂው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቡና ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

ተጠባቂው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቡና ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

28ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ጨዋታ የሊጉ መሪ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስን ከኢትዮጵያ ቡና አገናኝቷል። በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። እስማኤል ኦሮ አጎሮ ቅዱስ ጊዮርጊስን ቀዳሚ ያደረገች ጎል ሲያስቆጥር ብሩክ በየነ ደግሞ የኢትዮጵያ ቡናን አቻ ያደረገች ጎል አስቆጥሯል። ኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ከመቻል ጋር እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር የሚጫወቱ ይሆናል ተብሏል። ከአራት ቀናት በኋላም ባህር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና፣ አርባምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ፣ ወላይታ ዲቻ ከወልቂጤ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ መድህን እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ። ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን በ59 ነጥቦች ሲመራ ባህርዳር በ54 እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ደግሞ በ48 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።…
Read More
ኢትዮጵያ ከኮቲዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆነች

ኢትዮጵያ ከኮቲዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆነች

በኮቲዲቯር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች በመካሄድ ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዚህ ማጣሪያ ጨዋታ አንድ አካል የሆነው ጨዋታ ከማላዊ አቻው ጋር አድርጓል። ይህ ጨዋታ ዜሮ ለዜሮ በሆነ አቻ ውጤት የተጠናቀቀ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኮቲዲቫሩ የአፍሪካ ዋንጫ መውደቁን አረጋግጧል። ምድቡን እየመራች ያለችው ግብጽ አስቀድማ ማለፏን ያረጋገጠች ሲሆን ጊኒ ደግሞ ሁለተኛ በመሆን ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፏን አረጋግጣለች። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት ውበቱ አባተ በውጤት ማጣት መሰናበታቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከአሰልጣኝ ውበቱ ጋር በስምምነት እንደተለያየ ከዚህ በፊት አስታውቋል። በያዝነው ዓመት ለሚካሄደው የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ኮቲዲቯርን ጨምሮ ከ15 በላይ ሀገራት ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ኮቲዲቯር፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ደቡብ አፍሪካ፣…
Read More
ሊድስ ዩናይትድ እና ሌቺስተር ሲቲ ሳውዛምፕተንን ተከትለው መውረዳቸው አረጋገጡ

ሊድስ ዩናይትድ እና ሌቺስተር ሲቲ ሳውዛምፕተንን ተከትለው መውረዳቸው አረጋገጡ

የ2022/23 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ፍፃሜውን አግኝቷል። የዘንድሮው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ማንችስተር ሲቲ የዋንጫ አሸናፊ ሲሆን አርሰናል፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ኒውካስትል ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል። ሊቨርፑል እና ብራይተን በቀጣይ አመት የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊ ክለቦች ሲያልፉ አስቶን ቪላ የአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ ተሳታፊ ሆኗል። የማንችስተር ሲቲው አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ በ36 ግቦች የውድድሩ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ማጠናቀቅ ችሏል። አርሊንግ ሀላንድ ከኮኮብ ግብ አግቢነት በተጨማሪ የእንግሊዝ ኮኮብ ተጫዋች እና ወጣት ተጫዋች ሽልማትንም አሸንፏል። ሳውዝሀምፕተን ፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ሌስተር ሲቲ ወደ እንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፕ መውረዳቸውን ያረጋገጡ ክለቦች ሆነዋል። በቀጣይ የውድድር አመት ሉተን ታውን ፣ ሼፍልድ ዩናይትድ እና በርንሌይ ወራጅ ክለቦችን…
Read More
ማንችስተር ሲቲ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን አሸነፈ

ማንችስተር ሲቲ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን አሸነፈ

አጓጊው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሊጠናቀቅ አንድ ጨዋታ ብቻ ቀርቶታል። ማንችስተር ሲቲ ቀሪ ሁለት ጨዋታ እየቀረው የ2022/23 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን አሸንፏል። የዘንድሮውን ውድድር ሳይጠበቅ ለረጅም ወራት ሲመራ የቆየው አርሰናል ሁለተኛ ሆኖ ማጠናቀቁ እርግጥ ሆኗል። አርሰናል በትናንትናው ዕለት ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረገውን ጨዋታ መሸነፉን ተከትሎ በፔፔ ጋርዲዮላ የሚሰለጥነው ማንችስተር ሲቲ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት ዋንጫ መብላቱን አረጋግጧል። ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ለማለፍ የሚደረገው ትንቅንቅ እንደቀጠለ ሲሆን ሊቨርፑል በአስተንቪላ መሸነፉ የተሳትፎ ተስፋውን አክስሟል። ከቦርንማውዝ የተጫወተው ማንችስተር ዩናይትድ በካዝሚሮ ብቸኛ ጎል ማሸነፉን ተከትሎ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ተስፋውን የበለጠ አለምልሟል። ከፕሪሚየር ሊጉ ላለመውረድ እየተደረገ ያለው ትንቅንቅ የቀጠለ ሲሆን ሳውዛምፕተን ወደ ታችኛው ሊግ መውረዱን አረጋግጧል። ሊድስ ዩናይትድ፣…
Read More
ማንችስተር ሲቲ እና ኢንተርሚላን ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አለፉ

ማንችስተር ሲቲ እና ኢንተርሚላን ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አለፉ

በአውሮፓ ምርጥ እግር ኳስ ክለቦች ሙካከል ሲካሄድ የቆየው የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ተፋላሚዎች ታውቀዋል። ትናንት ምሽት በእንግሊዝ ማንችስተር ከተማ በሪያል ማድሪድ እና ማንችስተር ሲቲ መካከል የተካሄደው ውድድር በሲቲ የበላይነት ተጠናቋል። በርናርዶ ሲልቫ ሁለት ጎል፣ አልቫሬዝ እና ሚሊታኦ በራሱ ግብ ላይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሲቲ በቱርክ ኢስታምቡል ከተማ ለሚካሄደው የፍጻሜ ውድድር ማለፍ ችሏል። የጣልያኑ ኢንተር ሚላን በፍጻሜው ማንችስተር ሲቲን የሚገጥም ሲሆን ጨዋታው ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 4:00 ላይ ይካሄዳል ተብሏል። የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድርን የስፔኑ ሪያል ማድሪድ 14 ጊዜ በማሸነፍ ቀድሚው ክለብ ሆኖ ተመዝግቧል። የፍጻሜ ተፋላሚው ማንችስተር ሲቲ እስካሁን አንድም ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግን ያላሸነፈ ሲሆን ሌላኛው የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተርሚላን ሶስት…
Read More
ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በመቻል ተሸነፈ

ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በመቻል ተሸነፈ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። የመቻልን የማሸነፊያ ግብ የቀድሞ የፈረሰኞቹ ተጨዋች ከነዓን ማርክነህ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ፈረሰኞቹ በዛሬው ጨዋታ ሙሸነፋቸውን ተከትሎ በውድድር አመቱ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል። የቀድሞው መከላከያ እግር ኳስ ክለብ የአሁኑ መቻል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 33 በማድረስ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሽንፈት ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ51 ነጥብ ሊጉን እየመራ ይገኛል። የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ ከተከታዩ ባህርዳር ከተማ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ጠቧል። በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም መቻል ከ ሲዳማ…
Read More
ሻሸመኔ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ፕሪሜር ሊግ አደገ

ሻሸመኔ ከነማ እግር ኳስ ክለብ ወደ ፕሪሜር ሊግ አደገ

በሳሙኤል አባተ በምድብ ለ ሀዋሳ ላይ እየተከናወነ በሚገኜው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ሻሸመኔ ከነማ ቀሪ 4 ጨዋታ እያለው ወደ ቤቲኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል ። በዕለተ ማክሰኞ ሚያዚያ 24 አዲስ አበባ ከነማ በቦዲቲ ከነማ 2ለ1 መሸነፉን ተከትሎ ሻሸመኔ ቀሪ 4 ጨዋታዎች እያሉት በ 47 ነጥብ ፕሪሜር ሊጉን ተቀላቅሏል ። አዲስ አበባ ከነማ በ35 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በቀጣይ ቀሪ 2 ክለቦች ሊጉን ይቀላቀላሉ ። በምድብ ሐ  ሀምበርቾ ዱራሜ በ 42 ነጥብ ገላን ከተማ በ 40 ነጥብ የምድቡ አንደኛ ሁኖ ለማለፍ የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል ። በተመሳሳይ በምድብ ሀ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ 50 ነጥብ ምድቡን ሲመራ ቤንቺ ማጅ በ…
Read More