25
Jun
28ኛው ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ጨዋታ የሊጉ መሪ የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስን ከኢትዮጵያ ቡና አገናኝቷል። በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። እስማኤል ኦሮ አጎሮ ቅዱስ ጊዮርጊስን ቀዳሚ ያደረገች ጎል ሲያስቆጥር ብሩክ በየነ ደግሞ የኢትዮጵያ ቡናን አቻ ያደረገች ጎል አስቆጥሯል። ኢትዮጵያ ቡና በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ከመቻል ጋር እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር የሚጫወቱ ይሆናል ተብሏል። ከአራት ቀናት በኋላም ባህር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና፣ አርባምንጭ ከተማ ከድሬዳዋ፣ ወላይታ ዲቻ ከወልቂጤ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ መድህን እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ። ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን በ59 ነጥቦች ሲመራ ባህርዳር በ54 እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ደግሞ በ48 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።…