Football

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ የበለጠ አጓጊ ሆኗል

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ የበለጠ አጓጊ ሆኗል

የፕሪሚየር ሊጉ መሪ አርሰናል ነጥብ ጣለ። በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ 31ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከ ዌስትሀም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። የአርሰናልን ግቦች ጋብሬል ጄሱስ እና ማርቲን ኦዴጋርድ ሲያስቆጥሩ የዌስትሀምን የአቻነት ግቦች ቤንራህማ እና ጃርድ ቦውን አግብተዋል። የአርሰናል የመሀል ሜዳ ተጨዋች ማርቲን ኦዴጋርድ በውድድር አመቱ አስራ አንደኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ከሜዳው ውጪ የተጫወተው አርሰናል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቡን ሰባ አራት ያደረሰ ሲሆን ቀሪ ጨዋታ ካለው ተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ ብሏል። ዌስትሀም በበኩሉ በ31 ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል። በቀጣይ የእንግሊዝ መርሀ ግብር አርሰናል ከ ሳውዝሀምፕተን እንዲሁም ዌስትሀም ከ በርንማውዝ…
Read More
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተገለጸ።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስገብተዋል ተብሏል። የአሰልጣኙን የመልቀቂያ ጥያቄ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እየተወያዩበት እንደሆነ ትርታ ስፖርት ዘግቧል። የስራ አስፈፃሚ አባላቱ በሁለት ሀሳብ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። አንዳንዶቹ አሁኑኑ ይሰናበት ጥያቄውን እንቀበል ያሉ ሲሆን ሌሎች አባላት ደግሞ ቀሪ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ይጨርስ እያሉ ይገኛሉ ተብላል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ ከአሰልጣኙ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ውሳኔውን የሚያሳውቅ ይሆናል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ልምድ ካላቸው አንጋፋ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር በመሆን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸንፈዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከ2020 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ…
Read More
ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ 800ኛ ጎሉን አስቆጠረ

ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ 800ኛ ጎሉን አስቆጠረ

አርጀንቲናዊው የዓለም ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ 800ኛ ጎሉን ከመረብ አገናኝቷል። በኳታር አዘጋጅነት የተካሄደው የዓለም ዋንጫን ያሸነፈው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ በህይወት ዘመኑ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ወደ 800 ከፍ አድርጓል። የሰባት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ሜሲ ሀገሩ አርጀንቲና ከፓናማ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ተጫውታ 2ለ0 አሸንፋለች። የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ጎሎች ቲያጎ አልማዳ በ11ኛው ደቂቃ እንዲሁም ሊዮኔል ሜሲ ደግሞ በ89ኛው ደቂቃ አስቆጥራል። ሊዮኔል ሜሲ ለአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ወደ 99 ከፍ ሲያደርግ በቀጣይ የማጣሪያ ጨዋታቆች 100ኛ ግቡን እንደሚያስቆጥር ይጠበቃል። የቀድሞው የባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ ለባርሳ 672 እንዲሁም አሁን እየተጫወተበት ላለው ፒኤስጂ ደግሞ 29 ጎሎችን አስቆጥሯል። ሊዮኔል ሜሲ…
Read More
ዋሊያዎቹ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቀኑ

ዋሊያዎቹ ከጊኒ ጋር ለሚያደርጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቀኑ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ሞሮኮ አቅንቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በኮትዲቯር አስተናጋጅነት በሚካሄደው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ከጊኒ ብሔራዊ ቡድን ጋር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን መጋቢት 15 እና 18 ቀን 2015 ዓ.ም በሞሮኮ ያደርጋል። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ከመጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ልምምዳቸውን ሲያደርጉ ቆይተዋል። ዋልያዎቹ ከትናንት በስቲያ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከሩዋንዳ አቻቸው ጋር ባደረጉት የአቋም መለኪያ ጨዋታ በከነዓን ማርክነህ ግብ 1 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወቃል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አራት ከግብጽ፣ ከማላዊና ከጊኒ ጋር ተደልድሏል፡፡ እስከአሁን…
Read More