Wubetuabate

የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሀላፊነታቸው ለቀቁ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከሰሞኑ የስራ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማስገባታቸው ሲገለጽ ነበር። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በድረገጹ እንደገለጸው ከአሰልጣኝ ውበቱ ጋር በስምምነት መለያየቱን አስታውቋል። ፌዴሬሽኑ ከአሰልጣኙ የቀረበለትን የስራ መልቀቂያ ተቀብሎ ማጽደቁን ገልጾ አሰልጣኙ እስካሁን ላደረጉት ስራ ምስጋናውን አቅርቧል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ልምድ ካላቸው አንጋፋ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር በመሆን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸንፈዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከ2020 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ በኮትዲቯር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በጊኒ ብሔራዊ ቡድን ሁለት ጨዋታዎችን ተሸንፈዋል። የ45 ዓመቱ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የግብጽ ብሔራዊ ቡድንን 2 ለ 0 ማሸነፋቸውን ተከትሎ…
Read More
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተገለጸ።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የመልቀቂያ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስገብተዋል ተብሏል። የአሰልጣኙን የመልቀቂያ ጥያቄ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እየተወያዩበት እንደሆነ ትርታ ስፖርት ዘግቧል። የስራ አስፈፃሚ አባላቱ በሁለት ሀሳብ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። አንዳንዶቹ አሁኑኑ ይሰናበት ጥያቄውን እንቀበል ያሉ ሲሆን ሌሎች አባላት ደግሞ ቀሪ ሁለት የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን ይጨርስ እያሉ ይገኛሉ ተብላል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ ከአሰልጣኙ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ውሳኔውን የሚያሳውቅ ይሆናል። አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በኢትዮጵያ ልምድ ካላቸው አንጋፋ አሰልጣኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ጋር በመሆን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን አሸንፈዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ከ2020 ጀምሮ በማሰልጠን ላይ ያሉት አሰልጣኝ ውበቱ…
Read More