24
Mar
አርጀንቲናዊው የዓለም ኮኮብ ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ 800ኛ ጎሉን ከመረብ አገናኝቷል። በኳታር አዘጋጅነት የተካሄደው የዓለም ዋንጫን ያሸነፈው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ በህይወት ዘመኑ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ወደ 800 ከፍ አድርጓል። የሰባት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ሜሲ ሀገሩ አርጀንቲና ከፓናማ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ተጫውታ 2ለ0 አሸንፋለች። የአርጀንቲናን የማሸነፊያ ጎሎች ቲያጎ አልማዳ በ11ኛው ደቂቃ እንዲሁም ሊዮኔል ሜሲ ደግሞ በ89ኛው ደቂቃ አስቆጥራል። ሊዮኔል ሜሲ ለአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተሰልፎ ያስቆጠራቸውን ጎሎች ወደ 99 ከፍ ሲያደርግ በቀጣይ የማጣሪያ ጨዋታቆች 100ኛ ግቡን እንደሚያስቆጥር ይጠበቃል። የቀድሞው የባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ ለባርሳ 672 እንዲሁም አሁን እየተጫወተበት ላለው ፒኤስጂ ደግሞ 29 ጎሎችን አስቆጥሯል። ሊዮኔል ሜሲ…