17
Jul
የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር ላይ ባደረሱት ጥቃት የኢትዮጵያ ቡና ንግድ ለሶስት ቀናት ተስተጓጉሎ እንደነበር ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት የውጪ ንግድ አፈጻጸም ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እንዳሉት ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው 2016 በጀት ዓመት ውስጥ 350 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ነበር ብለዋል፡፡ ይሁንና አፈጻጸሙ 298 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ሀገራት የምትልከው ቡና በቀይ ባህር በኩል በመሆኑ እና የሀውቲ ታጣቂዎች በሚያደርሱት ጥቃት ምክንያት መስጓጎል ገጥሞት እንደነበርም ተገልጿል፡፡ እንደ ዋና…