14
Mar
የአፍሪካ ወጣቶች የሮቦቲክስ ፈጠራ ችሎታቸውን የሚያሳዩበት 3ኛው የአፍሪካ ሮቦቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ውድድር ዛሬ በታላቅ ድምቀት በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተጀምሯል። የኢትዮ ሮቦቲክስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰናይክረም መኮንን ለሦስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ የመጀመሪያ ደረጃ፣ የሁለተኛ ደረጃ፣ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፈጠራ ችሎታቸው ይወዳደራሉ፤ ውድድሩም በዲዛይን፣ በኢንጂነሪንግ እና በአውቶኖሚ ኮዲንግ ላይ እንደሚያተኩር በመርሃግብሩ ማስጀመሪያ ላይ አስረድተዋል። አቶ ሰናይክረም የውድድሩ ዓላማ ወጣቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ክህሎት ማዳበርና ማበረታታት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። በዚህ ውድድር አሸናፊ የሚሆኑ ተማሪዎች የዋንጫ ሽልማት እና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተፈረመ የምስክር ወረቀት እንደሚያገኙ አስታውቀዋል። ለፍጻሜ የሚበቁ ተማሪዎች አገራቸውን ወክለው በአሜሪካ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ…